ባህር ዳር፣ መቐለና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠኗቸውን ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቁ

118636858 3294946450596071 5088806922501742601 nባህር ዳር፣ መቐለ እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠኗቸውን ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቁ፡፡

ከዚህ ውስጥ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 780 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስመርቋል፡፡

ተማሪዎቹ ከአንደኛ ዲግሪ እስከ ፒ.ኤች.ዲ ድረስ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ሲሆን የምረቃ ስነ ስርአቱም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

የዩኒቨሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አያኖ በራሶ ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተው ፈተና የመፍትሄ አካል ለመሆን ሃገራዊ አንድነታችሁን እና
ወንድማማችነታችሁን አስጠብቃችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 520 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

የምረቃ ሥነ ስርዓቱ ጥቂት ተማሪዎችን ፊት ለፊትና አብዛኛዎቹን ባሉበት በተለያዩ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት በመታገዝ ተከናውኗል።

118615017 3295009420589774 5163763117758045028 nተመራቂዎቹ በህክምናና ጤና ሳይንስ፣ በስነ-ህንጻ እና በአውቶሞቲቭ ምህንድስና በመደበኛውና በሌሎች ተከታታይ መርሀ ግብሮች የሰለጠኑ 4 ሺህ 543 ተማሪዎች ናቸው።

በድኅረ መርቃ መርሀ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛውና በተከታታይ መርሀ ግብር ደግሞ 2 ሺህ 254 ተማሪዎች፣ በሦስተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር 40 ተማሪዎች፣ እንዲሁም በስፔሻሊቲ መርሀ ግብር 41 ተማሪዎች፣ በሰርቲፊኬት መርሀ ግብር 642 ተማሪዎች በድምሩ 7 ሺህ 520 ተማሪዎችን በበይነ መረብ በመታገዝ አስመርቋል።

118522825 3294946513929398 179219408946080555 n

በተያያዘ ዜና የመቐለ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ4 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎቹን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የምረቃ ሥነ ስርዓቱ ጥቂት ተማሪዎችን ፊት ለፊትና አብዛኛዎቹን ባሉበት ሆነው በቪዲዮ አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት በመታገዝ ተከናውኗል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፥ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸው አክለውም፥ የትግራይ ክልል የምትማሩበት ብቻ ሳይሆን ሁሌም የምትመላለሱበት ቤታችሁ እንዲሆን አናክረን እንሰራለን ብለዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.