ኮዳ ትራሱ ሌ/ጄነራል አማን ሚካዔል ዓንዶም

118540402 314231943364924 7059828930632776047 oሌ/ጄነራል አማን ሚካዔል ዓንዶም የተወለዱት በ 1916 ዓ.ም ነው ፤ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ጸአዘጋ ተወላጅ ናቸው። የአንደኛ እና የሁለተኛ ትምህርታቸውን አስመራ በሚገኘው ኮምቦኒና ካርቱም ኢቫንጀሊካል ሚሲዮን ፤ በተጨማሪም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና በአሜሪካን ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ። በወታደራዊ ትምህርትም በእንግሊዝ ሀገር በካምበርሊ ስታፍ ኮሌጅ የአዛዥነት ትምህርት የወሰዱ የመጀመሪያው መኮንን ናቸው ።

ጄነራል አማን በ 1932 ዓ.ም መጨረሻ ካርቱም ሶባ በተባለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጦር ትምህርት ቤት ከነ ጄነራል ከበደ ገብሬና ጄነራል አብይ አበበ ጋር በአንደኛ ኮርስ በእንግሊዞች ይሰጥ የነበረውን ወታደራዊ ትምህርት ወስደዋል ፤ ጄነራል አማን በታህሳስ ወር 1933 ዓ.ም በእንግሊዝ ጦር መሪነት በጎጃም በኩል በተካሄደው የነጻነት ዘመቻ በጀነራል ዊንጌት ከሚመራው ጦር ጋር በዘመቻው ተካፍለዋል ፤ በ 1939 ዓ.ም የሌተናል ኮሎኔልነት ማዕረግ አግኝተው በትግራይ እና በወሎ ይገኙ የነበሩትን 8ኛ እና 17ኛ ሻለቆችን በአዛዥነት መርተዋል ። በ 1943 ዓ.ም ጀነራል አማን በወታደራዊ አመራር ብቃታቸው እና በላቀ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው ተመርጠው የአንጀኛው ቃኘው ሻለቃ ጦርን በመምራት ኮሪያ ዘምተዋል ።

ጀነራል አማን በሠራዊቱ የተለያዩ ክፍሎች በአዛዥነትና በመምሪያ መኮንነት ያገለገሉ ሲሆን በተለይ የሦስተኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆነው ከተሾሙበት ከታህሳስ 1953 ዓ.ም ጀምሮ ” አማን የበረሃው አንበሳ ፣ ኮዳ ትራሱ ፣አሸዋ ልብሱ ፤ እንኳን ለጠላት አይሳሳም ለነብሱ ” የተባለ ቅጽል ስም የወጣላቸው ተወዳጅና ዝናን ያተረፋ አዛዥ ነበሩ ።

ጀናራል አማን በነበራቸው የረጅም ጊዜ ልምድ እና ችሎታ የኤርትራ ችግር በጦርነት ሳይሆን በሠላም መፈታት አለበት በሚል በቅንነት ደክመዋል ። ነገር ግን የደርግ አባላት ኮ/ል መንግስቱን ጨምሮ ስለ ኤርትራ በነበራቸው አነስተኛ ግንዛቤ ፣ ከፓለቲካ ልምድ ማነስና ኤርትራዊ ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ የኃላ ኃላ ለመወንጀል ዳረጋቸው እንጅ ጄነራል አማን ኮ/ል መንግስቱ እንደሚስሏቸው ሳይሆን ፍፁም አገር ወዳድና እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነበሩ ።

ሌ/ጀነራል አማን ሚካዔል አምዶም በተገጣይ ቡድኖቹ በኩል ዓላማችንን ሊያከሽፍብን ነው በሚል ፍራቻ ተቀባይነት ሳይኖራቸው በደርግም ተአማኒነት ሳያገኙ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው በአድናቂያቸው ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ትዕዛዝ ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም ተገደሉ ፤ አንዳንድ ስዎች ” መንግስቱ ያጠፋዋታልና ይጠንቀቁ ” ብለው ይነግሯቸው ነበር ፤ እሳቸው ግን ” መንግስቱ እኮ ያሳደኩት ልጄ ነው” እያሉ ምላሽ ይሰጡ ነበር።

ምንጭ ፦ አብዮቱና ትዝታዬ ፦ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ

 

3 Comments

  1. ታሪኩ በጣም መሳጭ ነው ብዙ ያልተነገረላቸው ጀነራል ናቸው ነገር ግን የተጻፈው ዘምን ይጣረዛል በድጋሚ እዩት

  2. መንግስቱ ስለገደለው ትክክለኛ ሰው አገር ወዳድ ነበር ማለት ደካማ አስተሳሰብ ነው፤ በተለይ እጅ አውጥቶ አብሮ ከወሰነ ሰው ይህን መስማት ያሳፍራል፡ መንግስቱ የገደላቸው ሁሉ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ቅን እውነታኛ ናችው?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.