ሕዳሴ ግድብ የስውሩ ግድብ ስራ፡ የፖለቲካ አላማ ወይስ ያገር ልማት? (በዘውገ ፋንታ)

dam 4የጥናቱ ዋና ነጥቦች

ይህ ጥናት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (ሕዳሴ ግድብ) ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነው። የሕዳሴ ግድብ የሀገር የልማት ዕቅድ የፈጠረው ‘ስትራተጂ’ አለመሆኑን ይህ ምርምር ያመለክታል። የሕዳሴውን ግድብ መመስረቻ ቦታ ምርጫ ጀምሮ ብዙ ልምዳዊ ያልሆኑ ፖሊሲዎች እንደተካሄዱ ጥናቱ በጉልህ ያሳያል። ለልማት ተጻራሪ የሆኑ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች እየወጡ፣ እነሱም እንደገና እየተቀለበሱ፣ የታሰበው የአንድ ግድብ ስራ ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊት የሀገሪቱ ልማቶች እና ብልጽግና እንቅፋት ተቀምጦባቸዋል። ጥናቱ ይህንን ተንትኖ ያስረዳል። የአባይ ወንዝ ልማት የተጠና “ከራስጌ ወደ ግርጌ” ስትራተጂ፣ መለስ ዜናዊ፣ የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ትሕነግ)መሪ፣ “ከግርጌ ወደ ራስጌ” በሚል እጉል ስልት ተክተውታል። ይህ ለትውልድ-ዘላቂ ጥፋት እንጂ ዘላቂ ልማት እንደማይሆን ምርምሩ ያረጋግጣል። በመለስ ዜናዊ በድብቅ አንዳንዴም በይፋ የተፈጸሙት መሰረተቢስ ፖለሲዎች በመመሪያ አዋጅ እየወጡ፣ ተጨባጭ ግንባታ እንዲካሄድ መደረጉን ምርምሩ የሕዳሴውን አባዜ በዋናነት ማስረጃ ያረጋግጣል። የግድቡ ዕቅድ በሚስጢር ተወጥኖ፣ ሊቀለበስ አስከማይችልበት ደረጃ ድረስ በሚስጢር ተጠናቋል። መለስ ዜናዊ የግድቡን መሰረተ ድንጋይ እስካስቀመጡበት ቀን ድረስ ግድቡ በከባድ ሚስጢር ተይዞ ቆይቷል።

[ሙሉ ጥናቱን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]


 

 

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.