‹‹አንድ ከብት ለማስተማር ሰባት ከብቶች መሸጥ አይገባም ነበር!!!›› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

43 ‹‹አንድ ከብት ለማስተማር ሰባት ከብቶች መሸጥ አይገባም ነበር!!!››  ሚሊዮን ዘአማኑኤልየኦነግ አረመኔዊ የዘርና የኃይማኖት ሽብር (ጆኖሳይድ) ቀስቃሾች፣ 100ዎቹ ከብቶች በስመ-ዴሞክራሲ !!!

‹‹አንድ ከብት ለማስተማር ሰባት ከብቶች መሸጥ አይገባም ነበር!!!”!›› መለስ ዜናዊ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ምሁርነት የተቹበት አስገራሚ ንግግር ነው ይባላል፣ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡ ቁምነገሩ ግን እነዚህን ምሁራን ለማስተማር ወላጆቻቸው ብዙ ከብቶች ሸጠው እንዳስተማሮቸው ይታወቃል፡፡ ሃገርና ወላጆች ግብር እየከፈሉ ያስተማሩት ትውልድ ምሁራን ሆነው የሃገሪቱን ኢኮኖሚ አላሳደጉም፣ ግብርናውን አላዘመኑም፣ ፋብሪካ አልገነቡም፣ ሆስፒታል አልሠሩም፣ ውኃ፣ መብራት፣ ስልክ  ወዘተ አገልግሎቶች አላደረሱም፡፡ የሃገራችን ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንዲበላ እናደርጋለን ብለው ቃል ገብተው ቃላቸውን አልጠበቁም፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ቁማርተኞች ያስፋፉት ግለኝነት፣ሌብነት፣ ሙስና፣ ህገወጥነትና ህዝቡን በዘርና በኃይማኖት ከፋፍለው በማያባራ ጦርነት ውስጥ ከተዋል፣ትላንት በቀይሽብርና በነጭ ሽብር፣ ዛሬ ደግሞ በዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ)፣ ዘርፈ ብዙ ሽብርተኛነትን ስፖንሰር ማድረግ የአገዛዝ ስልታቸው አድርገው ቀጥለዋል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት የምሁራኑን ህሊና ሲለውጥና ለሃገርና ህዝብ ሲሰሩ አልታየም፡፡ እነዚህን ሽህ ከብቶች ወደ በረታቸው ብንከታቸው ሃገር ሠላም ይሆናል፣ ወገን በፍቅር ይኖራል፣ ህዝብ በሃገሩ ተዘዋውሮ መስራት ይችላል፣ ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር ነፃነቱ ይጠበቅለታል፣ የህግ ሉዓላዊነት ይከበራል፣ እነዚህ ፖለቲከኞች ወደ ሃገር ሲገቡ ህዝብ እልል ብሎ እንደተቀበላቸው ከመቼው እረስተውት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፖለቲካ ሴራ ሲነድፉ ይስተዋላሉ፡፡

ከውጭ የተቀዳ የሶሻል ሳይንስ እውቀት ዴሞክራሲን የማያውቅ ምሁር ዴሞክራሲን ለመገንባት ያደረገው ጥረት ከጅምሩ የተቀጨው ዴሞክራሲን በአፍ እንጅ በተግባር መገንዘብ አለመቻላቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሃገራችን በስመ-ዴሞክራሲ የግራ ፖለቲካን መመሪያቸው አድርገው ሳይንሳዊ ሶሻሊዝምን የማራምድ ፓርቲ እኔ ነኝ፣ አንተ አይደለህም በመባባል አንድ ትውልድ በጥይት አልቆል፣ በአንድ ጉድጎድ ተቀብሮል፡፡ በሃገራችን የማርክሲስት፣ሌኒኒስት ርዕዬተዓለም ተከታይ የነበሩ እንደ ሆችሚንህ፣ቼጉቬራ፣ ፊዳል ካስትሮ ጫካ የገቡ ዱር ቤቴ ያሉ የሻብያ ፣ጀብሃ፣ ህወሃት፣ ኢህአፓ፣ ኢድዩ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ሲአን፣ ግንቦት ሰባት ወዘተ በአመዛኙ በዘር ተኮር ሽምቅ ውጊያ ወይም በአንድ ዘር የተመራ የትጥቅ ትግል በማድረግ ወደ የአንድ ዘር የጦር አበጋዝ በመሆን ዘመናቸውን ጫካ የጨረሱ የኤርትራ ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሱማሌ፣ የሲዳማ የጦር አበጋዞች ሆነው የተፈለፈሉ ለመሆን በቁ፡፡  የቬትናም ህዝባዊ ትግል የኩባ ህዝባዊ  ትግልና የቻይና ህዝባዊ ትግል እንደኢትዮጵያ በዘር ላይ የተመሠረተ ስላልነበር የተሳካ ነበር፡፡ የእኛ የፖለቲካ ምሁራን የመረዳት ትልቅ ችግር አለባቸው፡፡ ምሁራኑ ለመኮረጅ እንኳ አልታደሉም፡፡ የሃሰት ታሪክ የተጋቱ የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሱማሌ፣ የሲዳማ ወዘተ የፖለቲካ ምሁራን ትግላቸው ‹‹ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት›› ለመላቀቅ የተደረገ የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል እንደሚያደርጉ ተከታይ ጀሌዎቻቸውን ሲሰብኩ በዚህ የሴራ ፖለቲካቸው አገር ሲያወድሙ፣ ህይወት ሲቀጥፉ፣ ህዝብ ለእስር፣ ለርሃብና ለስደት ሲዳርጉ ሃምሳ አመታት አልፎል፡፡ እነዚህ የዘር የጦር አበጋዞች ሁሌ ስለ አጼ ሚንሊክ በቅኝ ግዛት መስፋፋት ተወርው እንደተገዙ ይተርካሉ፡፡ እነዚህ ምሁራን እንደ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተብዬዎች አፍሪካን በቅኝ ግዛት ለመቀራመት በበርሊን የተሰበሰቡ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቱጋል፣ ጣልያን፣ ቅኝ ገዥ ሃገራት  ከመሳሰሉት ጋር ኢትዮጵያን በመፈረጂ የታሪክ ስህተት አውቀው ሲፈፅሙ  ይስተዋላሉ፡፡ ለዚህ ነው ‹‹አንድ ከብት ለማስተማር ሰባት ከብቶች መሸጥ አልነበረባቸውም !!!›› የምንለው፡፡

ሻብያ፣ወያኔና ኦነግ በግንቦት 1983ዓ/ም ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነፃ ወጥተው ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን፣ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን፣ ሌንጮ ለታ ኦሮሚያ የምትባል ክልል ተበጅታለት ለመግዛት እንደቆመጠ ግማሽ ክፍለ ዘመን ተቆጠረ ፡፡  ለኤርትራ ህዝብ፣ ለትግራይ ህዝብ፣ ለኦሮሞ ህዝብ፣ ለሱማሌ ህዝብ፣ ለሲዳማ ህዝብ፣ ለአማራ ህዝብ ወያኔ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት የሰበከው ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ ህገመንግስት፣ እኩልነት ወዘተ የተስፋ እንጀራ ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ወያኔ/ ኢህአዴግ ጦር አበጋዞች ለህዝብ ቃል የገቡትን አንዱንም ሳይፈፅሙ ከስልጣን ተወግዶ ወደ ክልሉ ትግራይ ከደደቢት በረሃ ከተመ፡፡ ከዛም ሆኖ ወደ መኃል ሃገር ሽብር ስፖንሰር በማድረግ በመሳሪያ ዝውውር፣ በገንዘብ ዝውውር፣ የፖለቲካ ሴራ በመንደፍ አገር በማተራመስ ላይ ይገኛል፡፡ በ2013ዓ/ም ህወሓት /ኢህአዴግግብዓተ መሬት በጀግናው ትግራይ ህዝብ ይፈፀማል፡፡

ሻብያ፣ ወያኔ፣ ኦነግ ወዘተ የጦር አበጋዞች መንግሥት በህዝብ ላይ የፈጸሙት የህይወት ማጥፋት፣ የስብዓዊ መብቶች ጥፋት፣ የንብርት ውድመት፣ የእስራትና የጅምላ ግድያ መቃብር ሥፍራዎች አንድ ቀን ይፋ ይወጣል፡፡ እነዚህ ነጻ አውጭዎች በእራሳቸው ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት አፍነው በመያዝ በህዝብ ላይ የፈፀሙት ወንጀል አንድ ቀን ይገለፃል፡፡ የሶማሌው ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ በሱማሌ ህዝብ ላይ የፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል፣ የጅምላ መቃብር፣ ጄል ኡጋዴ፣  ወዘተ   መጥቀሱ በቀጣይነት በትግራይ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ወዘተ ክልሎች ውስጥ የተፈፀሙ ወንጀሎች የጅምላ መቃብሮች መጋለጣቸው አንድ ቀን አይቀርም፡፡ ለአንድ ክልል ህዝብ አንድ ሽህ አንድ ፓርቲ ማቆቆቀም የፖለቲካ ምሁራኑ የስልጣን ሃራራና የሃብትና ንብረት ማለትም የጥቅም የማግኘት ፍልጎት ሆዳምነትን ያሳያል፡፡ ለአንድ አሮም ህዝብ አስርና አስራምስት ፓርቲ መመሥረት፣ ለአንድ አማራ ህዝብ  አስርና አስራምስት ፓርቲ መመሥረት፣ ለትግራይ፣ ለደቡብ፣ ጋምቤላ፣ ሱማሌ፣ ወዘተ የሚመሠረቱ ፓርቲዎች በእውነት ለህዝብ የሚያገለግሉ ከሆነ አንድ ሁለትና ሦስት ፓርቲዎች  ብቻ በመመስረት ተወዳድሮ በመመረጥ ህዝብ ማገልገል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

በዶክተር አብይ አህመድ የኦዲፓ ብልጽግና ፓርቲ  ህወሓት/ኢህአዴግን በማሽቀንጠር በትረ ስልጣኑን ተቆጣጠረ፡፡ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ የተቸረው መንግሥት ሀኖ ቢቆይም አሁን የኦሮሞ የኦሮሙማ የፖለቲካ ሴራም በኦፌኮ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ፣ ጁዋር አህመድ ወዘተና ተባባሪዎቻቸው የፖለቲካ ሽብር በመምራት ለአለፉት ሁለትና ሦስት አመታት በመጠናከር የዶክተር አብይ መንግስትን ለመገልበጥ በስውርና በቀጥታ የሽብር ተግባር ሲፈፅሙ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ዝም ተብለዋል፡፡

ኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ በዚህም መሠረት በትግራይ ክልል አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሽህ ሠራዊት ተደራጅቶ ለማያባራ የድንበር ጦርነት አሠፍስፎ ይገኛል፡፡ ልዩ የፖሊስ ኃይል ማሰልጠን  ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው፣ ሸነሸነው፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት እየጣረ ይገኛል፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ በሱማሌ ክልል በአብዲ ኢሌ ዘመን አርባ ሽህ የልዩ ኃይል ሠራዊት በመገንባት በሱማሌና በኦሮሞ  ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ወንጀል የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ዛሬም በኦዲፓ ብልፅግና መንግሥት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በዘር ላይ የተመሠረተ  ልዩ የፖሊስ  ኃይል ለሰላሳ አንደኛ ጊዜ በማሠልጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

የዘመናዊ ሽብርተኛነት ታሪካዊ አጀማመር ከፈረንሳይ አብዬት ጋር ይያያዛል፡፡ በዘመኑ የሽብርተኛነት ሥረ መሠረቱ መንስዔው ሥልጣኔ አሊያም የባህል ግጭቶች፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ኃይማኖታዊ ግጭቶች፣ የእስራኤልና የፓልስታይን ግጭት፣ አሊያም የራሽያ አፍጋኒስታን መውረር በሃገራት መህል የተከሰቱ ሽብርተኞነት ያካትታል፡፡ የዘመናዊ ሽብርተኛነት በግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ብስጭት፣ የመገለል ስሜት፣ አሉታዊ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን ማፍቀርና ማምለክ ንዴት እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ  ስሜቶች ይካተታሉ፡፡ አምስት ዓይነት ሽብርተኛነት

 • መንግሥት መር ሽብርተኛነት (State-Sponsored terrorism)፡- በመንግሥት የሚመራ በመንግሥታዊ መዋቅሮቹ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ ፖሊስ ኃይሉ፣ በጸጥታና ደህንነት ድርጅቱ በጋራ የተቀነባበረ የሽብርተኛነት ድርጊት ያሳያል፡፡
 • ተቃዋሚ ሽብርተኛነት (Dissent terrorism) ፡- በተቃሚዎች የሚመራ ሽብርተኛነት ቡድን ሲሆን ኢላማውም የመንግሥት ባለሥልጣኖችና መንግስታዊ ተቆማት ላይ ነው፡፡
 • የግራና ቀኝ ሽብርተኞች (Terrorists and the Left and Right)፡- በፖለቲካ ርዕተ ዓለም ፍልስፍና የግራ ፖለቲካ ሽብርተኛና የቀኝ ፖለቲካ ሽብርተኛ በመባል ይታወቃሉ፡፡
 • ኃይማኖታዊ ሽብርተኛነት (Religious terrorism)፡-ዋልታ ረገጥ ወይም ፅንፈኛ ኃይማኖታዊ ሽብርተኛ ቡድን በሌሎች የእምነት ተከታዬች ላይ የሚፈፅሙት ሽብር ነው፡፡
 • የወንጀል ሽብርተኛነት (Criminal Terrorism)፡- ወንጀለኛ ሽብርተኞ ቡድኖች በወንጀል ድርጊት ኃብትና ንብረት የሚዘርፉ ቡድኖች፣ በዕፅ ንግድ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በሰዎች ዝውውር፣ በወሲብ ንግድ፣ በህጻናት ሽያጭ፣ በገንዘብ ዝውውር በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ብድኖችን ያካትታል፡፡

የሽብርተኛነት ጽንሰ-ሃሳብ በስፋት ሲዳሰስ ዓለም አቀፋዊ አመፅ፣ ሽብር፣ ነውጥ በመቀስቀስ የፖለቲካና የኃይማኖት ዓላማዎችን በኃይል ማሳካት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ አብዬት ዘመን የጀመረው ሽብርተኛነት በ1970 እኤአ በሰሜን አየርላንድ አመፅ፣ በሃገረ ባስክ፣ በፓለልስታይን ምድር  ዘመናዊው ሽብርተኛነት ተስፋፋ፡፡ሬድ አርሚ ፋንክሽን፣ ላይላ ካሊድ በ 1970ዎቹ ሽብርተኛ ተብለው ተፈርጀው ነበር፡፡ በ1983 እኤአ የቤሩት የአሜሪካ የጦር ሠፈር የቦንብ ጥቃት፣ የ2001 እኤአ የሴፕቴንበር አስራአንድ የአሜሪካ ጥቃትና የ2002 እኤአ የባሊ የቦንብ ጥቃት ለአብነት ያህል ይጠቀሳሉ፡፡ ከ1980 እኤአ ጀምሮ እራስን አጥፍቶ ማጥፋት ሽብርተኛነት እየጨመረ በመሄድ  በሴፕቴንበር ኢለቨን በ2001 እኤአ ሽብር በኒዬርክ ከተማና በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተፈፀመ፡፡በዓለማችን የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች፣ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች፣ ብሄርተኛ ቡድኖች፣ ኃይማኖተኛ ቡድኖች፣ አብዬተኞችና ገዥው መንግሥት በአጠቃላይ፣ መንግሥትና ተቃዋሚ ቡድኖች በሽብርተኛነት ፅንሰ-ሃሳብ ላይ ተስማምተው ባያውቁም ሁሉም ዓላማቸውን ለማሳካት ሽብርተኛነትን ይተገብራሉ፡፡ ሁሉም የሽብር ድርጊቱን ፈፅመው ከደሙ ንፁህ ነን ይላሉ፡፡ ሽብርተኛነት እንደ ጦር ወንጀል (war crime) ለመፈረጅ ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡

የሽብርተኝነት አጥኝ ምሁራን ምንጭ መሠረት አራት ዋና ዋና የሽብርተኞች ማዕበል በዓለም አቀፍ ሽብርተኛነት ተመዝግበዋል እነሱም አንደኛ የአናርኪስቶች፣ ሁለተኛ የፀረ ቅኝግዛት፣ ሦስተኛ ዘኒው ሌፍት እና አራተኛው ኃይማኖታዊ ሽብርተኝነት ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ በአለፈው አርባ አመታት ውስጥ ተጠናቀው የተከወኑ የሽብር ዓይነቶች ሲሆኑ አራተኛው ኃይማኖታዊው ሽብር ደግሞ ሶስት አስርት አስቆጥሮል ይሉናል፡፡  “Scholars of terrorism refer to four major waves of global terrorism: “the Anarchist, the Anti-Colonial, the New Left, and the Religious. The first three have been completed and lasted around 40 years; the fourth is now in its third decade.” 1

የዓለም አቀፍ ሽብርተኛነት መረጃ ቆት መሠረት ከ2000እኤአ እስከ 2014 እኤአ ባሉ አመታት ውስጥ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ጥናት ዘገባ 61000 (ስልሳ አንድ ሽህ) መንግሥታዊ ያልሆነ ሽብርተኛነት መከናወኑን በሽብሩ ድርጊትም 140000 (መቶ አርባ ሽህ) ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቦል፡፡ “The Global Terrorism Database, maintained by the University of Maryland, College Park, has recorded more than 61,000 incidents of non-state terrorism, resulting in at least 140,000 deaths, between 2000 and 2014.” 1   በተለያዩ አገራቶች የተከናወኑ ሽብርተኛነት ጥቃቶች ብዛት ብንቃኝ ደግሞ  በኢራቅ (15864)፣ ፓልስታይን (9708)፣ አፍጋኒስታ(7641)፣ ኢንዲያ (6023)፣ ፊሊፒንስ (2872)፣ ታይላንድ (2848)፣ ሱማሊያ (2313)፣ ናይጀሪያ (2170)፣ የመን (1821)፣ ራሽያ (1753)፣ ኮሎምቢያ (1738)፣ አልጀሪያ (1311)፣ ሊቢያ (1084)፣ እስራኤል(1025)፣ በሌሎች አገሮች ውስጥ (13964) የሽብር ጥቃቶች መፈፀማቸው ከመረጃ ቆት ተመዝግቦል፡፡ ሽብርተኝነት የኃይለ መንገድ ዘይቤ ወይም ቴክኒክ በመጠቀም አሊያም በህብረተሰቡ ውስጥ ስጋት በመፍጠር በፍርሃት ቀንበር ውስጥ በመዝፈቅ  እንዲኖሩ የማድረግ እኩይ የፖለቲካ ሴራ ነው፡፡ “a tactic or technique by means of which a violent act or the threat thereof is used for the prime purpose of creating overwhelming fear for coercive purposes”. It classified disorders and terrorism into six categories:-
{1}  ማህበራዊ ስርዓተ አልበኝነት (Civil disorder):-  ህዝባዊ አመፅ የማህበረሰቡን ሠላም ያጠፋል፣ የጸጥታን ደህንነት ያናጋል፣ የተለመደውን ሥራ እንዳይከናወን ያደርጋል፡፡ ሰው መግደል፣ ንብረት ማውደም፣ መንገድ መዝጋት፣ መንግሥታዊ ተቆማቶችን ማውደም ሥርዓተ አልበኝነት ያስከትላል፡፡ የህዝቡን ሠላማዊ ህይወት ያናጋል፣ የሃገር ፀጥታና የህዝብ ደህንነት ያናጋል፡፡

{2} ፖለቲካል ሽብርተኛነት (Political terrorism)፡- ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል የተቀነባበረ የወንጀል ድርጊት በመፈፀም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሃት በመንዛት፣  በዘርና በኃይማኖት ላይ በዋናነት የሚፈልጉትን ወገን አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድሎ ነፍጠኛ ነው የገደለው በማለት የአማራ ዘርንና የኦርቶዶክስ ክርስቲኖችን በማጥቃት የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት ያካትታል፡፡

{3} ኢፖለቲካዊ ሽብርተኛነት (Non-Political terrorism)፡- ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ያልተቀነባበረ  የወንጀል ድርጊት በመፈፀም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሃት በመንዛት፣ በዋናነት የሚፈልጉትን ወገንና ቡድን በማጥቃት የግለሰብ ወይም የቡድን ጥቅምን የማስጠበቅ ዓላማ ያለው ነው፡፡ የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት አያካትትም፡፡    –

{4} ሽብርተኛ መሳይ/ብጤ (Quasi-terrorism):- የሽብርተኛ ዓይነት ድርጊት በመፈፀም ሰዎች በማገት ገንዘብ የመጠየቅ፣ ከክልላችን መጤና ሰፋሪዎች ይውጡ ጥያቄ መጫር፣ በዚህ ክልል አይቀበሩም ወዘተ ሽብርተኛ መሳይ/ብጤ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

{5} ውስን የፖለቲካ ሽብርተኛነት (Limited political terrorism) ሃቀኛው የፖለቲካ ሽብርተኛነት መሰረቱ አብዬት ነው፡፡ ህዝባዊ አብዬት በማድረግ  የፖለቲካ ስልጣን መጨበጥ ዋነኛ ግብ ነው፡፡ ውስን የፖለቲካ ሽብርተኛነት መሠረቱ የፖለቲካና የርዕዬተ ዓለም ኢላማ ላይ ብቻ ያተኮረ ሲሆን የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ አይታገሉም፡፡

{6} መንግሥታዊ ሽብርተኛነት (Official or state terrorism):- መንግሥት መር ሽብርተኛነት ፖሊሲ ሲሆን  በመንግሥታዊ መዋቅሮችና ቢሮክራሲ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይል፣ የፀጥታና ደህንነት ተቆማት በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በህዝብ ላይ የሚደረግ የአፈና ጭቆና ሽብርተኛ ሥርዓት በመዘርጋት ህዝብን በፍርሃት ቀንበር ስር መግዛትን ያካተተ ነው፡፡

ማጠቃለያ  ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን የኦነግ፣ የኦነግ ሸኔና ኦፌኮን የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) አስወግደን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡ በኢትዮጵያ የዘርና የኃይማኖት ፍጅትና ዘርፈ ብዙ ሽብርተኛነትን ለማስወገድ ፡-

 • አንደኛ ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣
 • ሁለተኛ በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣
 • ሦስተኛ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣
 • አራተኛ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

ክልሎችም ያንጃበበውን አደጋ ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች እጅ የወደቀ ዕለት የመጀመሪያዎቹ የጥቃት ኢላማዎች እነሱ መሆናቸውን ሊያጤኑት ይገባል። በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል። ይህን ለማድረግ ግን ወሳኙ ነገር የአገዛዝ ሥርዓቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ያንጃበበውንም አደጋ በበቂ ሁኔታ መረዳትን ይጠይቃል። ይሄን የተጠመደ ፈንጂ ሳያመክኑ በጀርባ አዝለው እየዞሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለት ብቻውን አደጋውን አያስቀረውም።››2 የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ሊታደጉት ይገባል እንላለን፡፡ በሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ተከትሎ መቶ ስልሳ ሰባት ሰዎች ህይወት መጥፋት ቤተሰቦች ሳያፅናኑና ለወደመው ንብረት በተለይ የሻሸመኔ ከተማ መቃጠል ለመርዳት በሃገር አቀፍ ደረጃ የእርዳታ  ገበታ ሳያዘጋጁ አዲስ አበባ ለማስዋብ የአምስትና አስር ሚሊዮን ብር የገበታ ድግስ ማዘጋጀት ቅድሚያ ለማን ይሰጥ? ከተማ ከመገንባት በፊት የቄሮ ህሊናን መገንባት ይቅደም፣ እንደ ሻሸመኔ ከተማ አገር ያቃጥሉና እንላለን፡፡

 

ኢትጵያ ብዙ ሃገር ወዳድ ምሁራን ያላት ሃገር ናት!!!

አድርባይ ምሁራን ለፍርድ ይቅረቡ!!!

 

ምንጭ፡-

(1) https://en.wikipedia.org/wiki/Terrorism

(2)  የክልል ልዩ ታጣቂ ኃይል ይፍረስ፤ በዘር ተደራጅቶ፣ በዘር የታጠቀ፣ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል…!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)/ Posted by admin | 2020-08-04 | / EthioReference

2 Comments

 1. If Eskinder , Yilkal , Lidetu and alike were free they would have went to Shashamane , Ziway , Arsi… in person to console with the victims , while as always Abiy is hiding in Addis Ababa. EZEMA did not console with the victims by showing up on the ground either. Shimeles Abdissa Oromia region’s president sent his cadres around the make shift shelters chasing help away , blocking help from reaching those ethnic cleansing victims.

  Abiy knows he is not able to guarantee his safety in Oromia so he just keeps himself busy throwing dinner parties and beautifying Addis Ababa, ensuring his safety by securing a stage with impenetrable terrace at Mesqel Square which is grenade proof top of the line high tech security system on the Ethiopian Orthodox church’s grounds turning the place into his architectural design instead of the church’s.

  Remember less than a year ago Abiy got chased out of Ambo when he went to Ambo city to make a speech right after the 86 people were killed after Jawar’s security was in limbo last year, since then Abiy knows he should only lurk around with his beautification project buddies in the capital when anything major such as the recent attacks happen in Oromia.

 2. At least Melesse was right describing Merera as a house hold animal or cattle which merara keeps proving he is and chasing him out of the university seems the right decision now.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.