ብዙ ሕዝብ በግድ ኦሮሞ የተደረገ እንጂ ኦሮሞ አይመስለኝም – ስርፀ ደስታ

አይመስለኝም ስላልኩ ደግሞ ክፍተት ያገኛችሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ መረጃውን ለሌሎችም አይተው እንዲፈርዱ እድል ለመስጠት ነው፡፡ የዘመኑ ሳይንስ የታሪክ እውነታዎችንም እንድንፈለፍል አስችሎናል፡፡ የኢትዮጵያን የክብረ ነገስት ታሪክ ተረት ተረት ነው ለሚሉ ለዘመናዊ ታሪክ አዋቂ ነን ባዮችና የልተፈጠረ ታሪክ ተራኪዎች የክብረነገስትን እውነትነት ለማረጋገጥ የታሪክ ሰው መሆን ሳይሆን የዘመኑን ሳይንስ ማወቅን ብቻ ጠይቋል፡፡ ፓጋኒ ሉቃስና ጓደኞቹ የእናውን ፕሮፌሰር እንዳሻው በቀለን ጨምሮ በፈረንጆች 2012 ባሳተሙት የኢትዮጵያውያን የዘረ-ሐረግ ጥናት በትክክለም ሚኒሊክ ቀዳማዊ ከእስራኤል ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና የመጡበትን ዘመን ሁሉ ዛሬ በአለንው ኢትዮጵያውያን ደም ውስጥ የሚገኘውን የዘር ማንነታችንን በዋቢነት አሳይተዋል፡፡ ይሄን ለበርካታ ጊዜ እንድታዮት ጋብዤያችሁ ነበር፡፡ አስቂኙ ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ የሚያወራ ምሁር አልሰማሁም፡፡ በተለይ የታሪክ ምሁር ነኝ የሚል ይህ ጽሑፍ ወሳኝ መረጃው በሆነ ነበር፡፡ ችግሩ ከራሳችን ፈጥረን ማውራት እንጂ የሳይንስ ውጤት ምስክሮችን ለመመረቂያ ካልሆነ አንሞክራቸውም፡፡ ለመመረቂያውም ግድ ሆኖብን ነው፡፡ ለዚህ ግን በጽሑፍ አሳምረው ታሪኩን ያቆዩልንን የክብረነገስትም ሆኖ ሌሎች ጸሐፊያንን እያመሰገንኩ ዛሬ የእነሱ መዝገብ ለሳይንሱም ትልቅ ማጣቀሻ ሆኖ በማየቴ እኮራባቸዋለሁ፡፡

በዛሬው እለት የማቀርብላችሁ እነ ፓጋኒ የተጠቀሙትን የዘረመል መረጃ (ዴታ) ከዌብ ሳይት አውርጄ እኔው የሠራሁትን ነው፡፡ ይህ የጥናት ውጤት የሚያሳየን ታሪክን እንደወረደ ነው፡፡ እነ ፓጋኒ ብዙም ትኩረት ያላደረጉት ነገር ነው፡፡ በዚህ ጥናት መሠረት ኦሮሞ እየተባሉ ዛሬ የሚጠሩ ሰዎች የዘረ-ማንነታቸው ከተለያየ እንደሆነ ነው፡፡ ለዚህ እንደምክነያት ሊሆን የሚችለው በኦሮሞ ማይግሬሽንና ከዛም በኋላ ማንነታቸውን እንዲያጡ የተደረጉ ግን በደማቸው ማንነታቸውን ይዘው የቆዩ መሆናቸው ይመስላል፡፡ ዛሬ ዛሬ ገዳ የሚባለው ሥርዓት የብዙዎችን ማንነት በማጥፋት እየተከሰሰ ነው፡፡ ብዙ ምሁራንም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል፡፡ ዛሬ ባለንበት በአሁን ወቅት ሳይቀር የኦሮሞ ፖለቲከኞች ዋና ስልት አድርገው የተነሱት የሌሎችን ማንነት በማጥፋት በኦሮሞነት መተካት የሚል በመሆኑ በ16ኛው ክፍለዘመን የሆነውን ጭፍጨፋና ሌሎችን ማጥፋትን በድጋሜ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ምስል እንደምታዩት ኦሮሞ ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ይልቅ የተለያየ ዘር ሆኖ ነው፡፡ ሆኖም ግን አብዛኛው ዛሬ ኦሮሞ ነኝ የሚለው የአማራና ትግሬ ዘር እንደሆነ ታዘቡ፡፡ እርግጥ ነው እናውቀዋለን፡፡ ሸዋ ሙሉ በሙሉ የነገስታቱ ቤተሰብ እንደሆነ፡፡ ዛሬ ሸዋን ለዘመናት እንደምንም ያቆየውን የአባቶቹን ኃይማኖትም ሊያስጥሉት ያለ የሌለ ጉልበታቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ ፍቼ ላይ ሄዶ ደብረ ሊባኖስን እንወርሳለን ያለው ሰውዬ ደብረ ሊባኖስ ሲጀምር የማን ነው፡፡ ዛሬ ወደ ኦሮሞነት የተቀየረው የፍቼና አካባቢዋ ሕዝብ እኮ የአቡነ ተክለኃይማኖት የቀጥታ የዘር ሐረግ ያለው ጭምር ነው፡፡ ያ ሕዝብ በወራሪዎች ነው ዘሬ ኦሮሞ የሆነው፡፡ እንዳልኩት ነው ሸዋ የነገስታቱ ዘር እንጂ ዛሬ ኦሮሞ ነን የሚሉት እንደሚተርኩት አደለም፡፡ የገዳ ወረሪዎች በገቡበት ቦታ ሁሉ ቦታዎችን ሰውንም ቦታውንም መሠረቱ እንዳይታወቅ ሥሙን በመቀየር ማንነትን የማጥፋት ስልት ቢኖራቸውም በሸዋ ዛሬም ድረስ ለመጥፋት ያልቻሉ ምልክቶች አሉ፡፡ ጥቁር እንጪኒ፣ ግንደ-በረት፣ መናገሻ (ይሄ የአሁን ስም እንዳይመስላችሁ ቢያንስ የመናገሻ መድኀኔዓለም ገዳምን አትርሱ)፣ ሌሎችም፡፡ በነገራችን ላይ የመናገሻ ሱባ ደንን የተከሉት አጼ ዘረያቆች ናቸው፡፡ ይሄንንም ተረት ተረት ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ በዲጋሜ በዚህ ላይ ራሴው ጥናት ያደረኩና በማያሻማ ሁኔታ ስላረጋገጥሁ አሁንም የታሪክ ሰነድ ሳይሆን የመለዘር (ዲኤንኤ) ጥናት ውጤት ማቅረብ እችላለሁ፡፡ መዝገቡንማ ደብተራ የጻፈው ምናምን እያሉ ያጣጥሉታል፡፡ በእነ ተክለሃይማኖትና በነገስታቱ ምድር ሸዋ ገና ብዙ መጠናት ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ የዝቋላ ገዳምን ለማጥፋት ብዙ ጊዜ ተሞክሯል፡፡ የአዳዲ ማሪያም ሌላዋ ምልክት ነች፡፡

የማንነት አጥፊው ገዳ ዘሮች ዛሬም ማንነትን ማጥፋት ቀጥለዋል፡፡ የቦታ ሥምን መቀየር ዋና ተግባራቸው ነው፡፡ ዝዋይን ባለመስሙ የዜይ ሕዝብ ዛሬም ድረስ ለምልክት እየኖረበት ያለውን ይሄው ባቱ ብለውታል፡፡ ይሄንኑ ተቀብሎ ሌላውም ባቱ እያለ መጥራቱን ቀጥሏል፡፡ ታሪክንና ማንነትን ማውደም እንዲህ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይሄን ጽሑፍ የምታነቡተ ሁሉ የዝዋይ ወደ ባቱ መቀየር በዘመናችን እየተደረገ ያለ የሌሎችን ማንነት ለማጥፋት የሚሰራ እኩይ ተግባር እንደሆነ ተገንዝባችሁ ባቱ በማለት ከመተባበር ይልቅ ትቃወሙት ዘንድ እላለሁ፡፡sat3ከላይ እንደምታዩት ነው እውነታው በዳር በኩል ወይነጠጅ የሚመስለው ብዙ ዛሬ ኦሮሞ ነን የሚሉ የተቀላቀሉበት የወላይታ ሕዝብ የዘር ቅርንጫፍ ነው፣ ቀጥሉ አረንጓዴው የኢትዮጵያ ሱማሌና የሱማሌ (ሐርጌሳ) ሱማሌ ነው፡፡ ቀጥሉ ውሀ ሰማያዊው አሁንም አማራና ትግሬ የተቀላቀሉበት ኦሮሞ የበዛበት ነው፣ ቀጥሎ ያሉት ሶስት ቀለሞች እንደ እውነቱ የዘር ርቀታቸው በጣም ተቀራራቢና የቤተሰብ ያህል ነው የመጨረሻውን ቀዩን ጨምሮ፡፡ በነገራችን ላይ ቀዩ የተነጠለ ይመስላል ግን በጣም ቅርብ ነው ለቡኒውና ቀላል አረንጓዴው፡፡ ከውሀ ሰማያዊው ቀጥሎ የምታዩት ቀላል አረንጓዴው የሚገርም የቤተሰባዊ አንድነት ስላለው እንጂ ከቡኒው ልዩነት የለውም፡፡ ይሄ ቀላል አረንጓዴ አፋሮች ናቸው፡፡ አፋር በድሮ ጊዜ ከሸዋ ሸፈተው በረሀ የገቡ ናቸው እየተባለ ይወራል፡፡ ይሄን እውነት ነው እነደወረደ የምታዩት፡፡ ምን አልባትም ምስሉ እንደሚያሳየን የአንድ ሰፈር ቤተሰብ ናቸው፡፡ ቡኒውና እንደምታዩት የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ውህደት ነው፡፡ አስተውሉ ቅርንጫፎቹ በተቀራረቡ መጡን በተለይ የጫፎቹ የቤተሰብ ቅርርባቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ ትግሬና አማራ ባይለያዩ አይገርምም፡፡ በቡኒውም ሆነ በቀዩ የምታዩት የኦሮሞና አማራ ውህደት ከትግሬና አማራም ይበልጣል፡፡ አልፎ አልፎ ኦሮሞ ከትግሬም እንዲሁ፡፡ በአጠቃላይ በዚህ የዘር ቅርንጫፍ የምናስተውለው ሁለት አማራ ነን፣ ትግሬ ነን፣ ኦሮሞ ነን ከሚሉት ይልቅ ትግሬና አማራው፣ ኦሮሞና አማራው ተቀራርበው እናያለን፡፡ ግለሰቦቹን ለማየት ዙም ኢን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

በነገራችን ላይ የሱማሌ ሱማሌና ኢትዮጵያ ሱማሌ በጣም ይቀራረባሉ ሆኖም ግን በተወሰነ ይለያያሉ እንደ ቡኒውና ቀዩ አደሉም፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ የኢትዮጵያ ሱማሌ ከኢትዮጵያው ሱማሌ ይልቅ የበረበራ ሱማሌ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ሌሎች መረጃዎች አሉኝ ግን ለሕዝብ ስለማይገቡ ነው እንጂ በጣም የሚያስደንቅ ነገሮችን እናየላን፡፡ እነፓጋኒ ያሳዩንን በሌላ መልኩ ለመስራት ሞክሬ ነበር፡፡ እጅግ የሳዝናልም ያስደስታልም፡፡ የእነዚህ ሁሉ ከላይ የምታዩት ቅርንጫፎች ግን ከአንድ የመጡና በጊዜ ብዛት እየተለያዩ የሄዱ ናቸው፡፡

ሰሞኑን መረራ ምን እንዳለ አላውቅም ግን የዘመኑ የኦሮሞ ምሁራን ነን እንደሚሉት ያው የተለመደውን ኦሮሞነት ሳያወራ አይቀርም፡፡ ኢትዮጵያ እንዲህ ዛሬ የምናያውን ብዝሀነት ሊኖራት የቻለው መሪዎች ማንነትን በማጥፋት

ላይ ስለማይሳተፉ ነው፡፡ ትንሽ ሕዝብም ሆኖ በራሱ ማንነት የቀጥላል፡፡ ሌላ ቀርቶ ከውጭ መጥተው በራሳቸው ማንነት ብዙዎች ኖረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በእምነቱም ሆነ በባህሉ ማንነትን የሚጠብቁ መሪዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ሙስሊም ሁሉ የሚናገርለት ክርስቲያኑ ንጉስ እስላሞችን መቀበሉን እናውቃለን ግን ዛሬ ላይ የአጥፊው የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን ሌሎችን እየጠፋ እናያለን፡፡ እንደነመረራ ያሉት በማደናገር ብዙ ኖረዋል፡፡ ሌሎቹ በይፋ በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥፋት አውጀው ለዘመናት ሲሰሩ ነበር፡፡ ሕዝብን ከማንነት፣ ከእምነት እንደልብ ሳይሆንላቸው ገድለን እንጨርሳለን በሚል ቀመር ነው እየሰሩ ያሉት፡፡

በነገራችን ላይ የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አሁን በዩኔስኮ ተመዝግቦ ይገኛል ወደፊት ግን ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ ሳያስነሳ እንደማይቀር እሙን ነው፡፡ ለብዙ ሕዝብ መጥፋት ምክነያት የሆነ ሥርዓት ነውና፡፡ በገዳ የጥፋት ዘመቻ የተነሱ ሰዎች መጀመሪያቸው ዛሬ በወላይታና ጋሞ መካከል ካለ ቦታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በታሪክም የገላናን ወንዝ ተሻግረው እንደመጡ ይነገራል፡፡ ሁለት በመጨረሻ አንድ የሚሆኑ ገላናዎች አሉ ገላና ሰገንና ገላና ዱሊ፡፡ አባ ባሕሬ ስለየትኛው ገላና እንደተናገሩ ግልጽ ባይሆንም የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ግን ገላና ሰገን ነው፡፡ ሥሙን ስናይ ግን ገላና ዱሊም ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ ከሱማሌ ጋሬ የኩሽ ምናምን ነገድ እያሉ የሚቀሳፍቱት የኦሮሞ ምሁር ነን ባዮች ታሪክና ያሉን ወሳኝ መረጃዎች የሚያመለክቱት ግን ከኦሮሞ ማይግሬሽን በፊት የሱማሌና የአሮሞ የተባለው ሕዝብ አንድም ግንኙንት አልነበረውም፡፡ በእርግጥ ነው በተለይም በሚኒሊክ ኢትዮጵያ አገር ሥር የተሰባሰቡ ሕዝቦች ሁሉ ከሚያዋስኗቸው አገሮች በተለየ የታሪካዊ የደም መነሻ አላቸው፡፡ በእነ ሚኒሊክ ቀዳማዊ ጊዜ ሁሉም አንድ ነበሩ (ተረት ነው ለኦሮሞ ምሁር እንደራሳቸው እየመሰላቸው)፡፡ አፋር ከላይ እንደምታዩት ከትግሬና አማራ ጋር አንድ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ሱማሌም ዋናውን ጨምሮ እንዲሁ ነው፡፡ ከመነሻው ሁሉም አንድ ናቸው፡፡ ኦሮሞ ጨምሮ ማለቴ ነው፡፡ ከአጥፊ አስተሳሰቡ በቀር፡፡

የማያሻሙ ወሳኝ መረጃዎችን እውነተኛውን ታሪክ ተረት ተረት እያሉ የራሳቸውን ተረት እየጫኑበት ላሉት ትውልድ ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

2 Comments

  1. ምን ጥርጥር አለዉ? ብዙ ህዝብ አሮሞ የተደረገ ነዉ። ራያ አከባቢ ከትግራይ ህዝቦች በተደረጉት ወሳኝ ዉግያዎች ባይገታ ኖሮ የኦሮሞ ማይግሬሽን ምናልባት እስከ ቀይ ባህር ይዘልቅ ነበር።

  2. ሰርጸ ደስታ ከዚህ በፊትም የዲ ኤነ ኤ ፐሮፋይሎችንም አዉጥተህ በበኩሌ ግንዛቤዬን ወስጃለሁ የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታትም ብዙ ታንክና ሚሳዬል ሳይሆን የሚያስፈልገን 20 የ ዲ ኤን ኤ መመርመረያ ማሺን አስቀምጠህ ጠቅላላዉን መመርመር ከዛ ማን ማን እንደሆነ ይታወቃል እኛም ተፋፍረን እንቀመጣለን አባ ዊርቱም እራሳቸዉን ወይ ሰሜን ወይ ሱዳን ያገኙት ይሆናለ። መራራ ጉዲና/ሌንጮ ለታ/ዳዉድ ኢብሳ………ሌላ ነገድ ሲሆኑ ጁዋር መሀመድ/በቀለ ገርባ/ለማ መገርሳ ከሌላ ነገድ ሁነዉ ሲያገኟቸዉ ሱባኤ ይገቡ ይሆናል እዚህ ነገር ላይ በርታልን ለጊዜዉ መፍትሄዉ ይሄ ብቻ ነዉ።

    እንዲህ ምርምር የሚጠይቅ መጽሀፍ አዲሶቹ ጸሀፊዎች አይወዱም የነሱ ሞዴል ተሰፋዬ ገ/አብ አንዳርጋቸዉ ጽጌን የመሳሰሉ እዉቀት ጥዩፋን ናቸዉ። እንደምታዉቀዉ አንዳርጋቸዉ ባለፈዉ በጻፈዉ መጽሀፍ ባዋቂዎቹ ተአማኒነቱ ሲተነተን ስንሰማ በሀፍረት ተኮማትረናል እሱ ግን አሁንም አንዳንድ ስብሰባዎች ላይ ኮት ለብሶ አየዋለሁ። ስለዚህ መጽሀፍ ከንቱነት ወልቃይት ድረ ገጽ ላይ የአይን ምስክርነታቸዉንና ስለ ጠቀሳቸዉ ስሞች ሳይቀር ሃሰት መሆኑን አስገንዘበዉናል። ወደ ታሪኩና ያጣቀሳቸዉ መጽሀፎችንና ጸሀፊዎችን አስመልክቶ ቴዎድሮስ ጽጋየና እቻምየለህ ታምሩ እራሳቸዉ እስኪያፍሩ ድረስ ድርሳናትን እያገናዘቡ ከበቂ በላይ ትንታኔ ሰጥተዉናል። ተመጣጥና የተሰራች ሀገር ከዛ ሌባዉ ይሰርቃል ከዚህ ሌባ አዳጅ እጂ ከፍንጂ ይይዛል እንዲህ ሁነን ነዉ የተሰራነዉ።
    ክብር ለአቻምየለህ ታምሩና ቴዎድሮስ ጸጋዬ ዶር ብርሀኑ ልደቱ ጎን ቁጭ ብዬ ከምሞግት እንጦሮጦስ ብወረወር ይሻለኛል እንዳለሁ ሁሉ አንዳርጋቸዉም ስለ መጽሀፍህ በርእዮት ሚዲያ ቀርበህ ሃሳብህን ስጥ ቢባል አሻፈረኝ ብሏል አቅሙን ስለሚያዉቅ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.