የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ፀብ -ጫሪነትን በመሸሽ ወደ አማራ ክልል በመግባት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

tigray
(ኢፕድ) – የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ፀብ ጫሪነት በመሸሽ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ አማራ ክልል የሚገቡ የክልሉ የልዩ ኃይል አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።
የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይሎች የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ፀባ ጫሪነት በመሸሽ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ አማራ ክልል እየሸሹ ነው። ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።
ከሰሞኑ ብቻ በሰሜን ጎንደር ከሰላሳ የሚበልጡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የአጥፊነት መልዕክትን በመክዳት ወደ አማራ ክልል ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው መግባታቸውን ያስታወቁት ኃላፊው፤ ከነዚህ መካከል አንዳንዶች የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ያለባቸው የክልሉ ነዋሪዎች ልጆች መሆናቸውን አመልክተዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን ገልጸዋል።ይህም ክልሉልዩ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ መፈረካከስ እንዳለ አመላካች ነው ብለዋል።
ከትግራይ ክልል መንግሥት ሸሽተው የሚመጡት ዜጎቻችን በመሆናቸው ክልላችን በሚታወቅበት እንግዳን በአክብሮት የመቀበል ባህላችን ተቀብሎ እንክብካቤ እያደረገላቸው ነው ብለዋል።
ህወሃት በአሁኑ ወቅት በርካታ ወጣቶችን በወታደርነት በመመልመል ለጦርነት እያዘጋጀች መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፣ የትግራይ ሕዝብ የክልሉ መንግሥት እያደረገ ያለው ትክክል አይደለም ብሎ እንደሚያምን በፈቃዳቸው ወደ አማራ ክልል ከገቡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት መረዳት መቻሉን አስታውቀዋል።
በግዳጅ የሚታጠቁ ወጣቶች ከእነትጥቃቸው በተደጋጋሚ ወደ አማራ ክልል እየገቡ ናቸው።በአማራ ክልል በኩል በእንደዚህ ዓይነት መልኩ ሰው እንዲመጣ አንፈልግም።ምክንያቱም ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ ኃላፊው አመላክተዋል።
ከትግራይ ክልል ጋር በምንዋሰንበት አካባቢ ለእረጅም ጊዜ የቆየ የአማራ ክልል ጥያቄ የሆነ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ መኖሩን የጠቆሙት ኃላፊው፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የህወሃት የአድዋ ቡድን የጦርነት ዝግጅት ለሀገር እድገት እና አንድነት ተገቢ አይደለም ብለዋል። በድንበር አካባቢ ወደ ጦርነት ለመግባት የማኮብኮብ ዓይነት እንቅስቃሴዎች መኖራቸውንም አመልክተዋል።
«የአማራ ክልል ወደ ጦርነት አይገባም። የአማራ እና የትግራይ ሕዝቦች ሁለት ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው።በግልፅ እንደሚታወቀው አብረው ተጋብተው እና ተዋልደው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው።ምንም ዓይነት ጉንተላ እና ፀብ-ጫሪነት በትግራይ ክልል መንግሥት በኩል ቢኖርም መቼም ቢሆን ሁለቱ ሕዝቦች ወደ ጦርነት ይገባሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው» ብለዋል ።
ከአማራ ክልል በኩል እስከዛሬ ድረስ ምንም ዓይነት ትንኮሳ የለም ወደፊትም አይኖርም የሚሉት ኃላፊው፤ በእኛ በኩል እየጠየቅነው ያለው የሕዝብ ጥያቄ የሆነውን የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ነው። ይህ ደግሞ ሕጋዊ ጥያቄ ስለሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴራሉ መንግሥት ሕጋዊ አሠራር ተከትሎ የራሱን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል እንጠብቃለን ሲሉም ተናግረዋል።
– አዲስ ዘመን
ተጨማሪ ያንብቡ:  መሪዎቻችን ስልጣን ሙጭጭ የሚሉባቸው ሦስት ምክንያቶች - ከስዩም ተሾመ

3 Comments

 1. The Amara region’s constitution permits these members of the Tigray special forces to join the Amara region’s special forces. The Amara region’s constitution allows any Ethiopian from any ethnic background to hold high level regional administration office, no other region’s constitution allows other ethnicities to hold such high level government offices as the Amara region’s constitution does permit.These defectors we read about above are more like deportees than defectors , these defectors/deportees are
  Tigray born half Amaras half Eritreans who lied about their ethnicity claiming to be Tegaru, now the truth is coming out so expect more to be dumped to Amara region in the coming months.

 2. ወሬው የሚታመን ከሆነ ማለፊያ ነገር ነው። ወራሪ በሌለበት ተወረሃል የተባለው የትግራይ ህዝብ የወያኔ ማላገጫ መሆኑ የሚያበቃበት ጊዜን አመላካች ጉዳይ ነው። የትግራይ ህዝብ ግፍ በወያኔ አይቷል። እያየም ነው። ለራሳቸው የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ህዝብ ወያኔ በደርግ አስደብድቦ በቪዲዮ ቀርጿል። ደርግ በሰፈራ ሰዎችን ከትግራይ በውድና በግዳጅ ሲወስድ ወያኔ ደግሞ የሃይል ምንጩ እንዳይመነምንበትና የመለመኛ ጆኒያው እንዳይደርቅ የትግራይን ህዝብ ይህ ነው ለማይባል መከራ በግድ ከትግራይ መሬት በማስወጣት ሱዳን ውስጥ እእላፎች እንዲያልቁ አድርጓል። ወያኔዎች ለትግራይ ህዝብ ጭራሽ ያረጉት ነገር የለም። ራሳቸው ግን ኑረዋል። እየኖሩም ነው። አሁን አማራ መጣባችሁ፤ ሻቢያ ሊወራችሁ ነው። ዶ/ር አብይ ወታደር ልኮ ሊፈጃችሁ ነው እያሉ የትግራይን ህዝብ የማታለል ዘዴያቸው አልሰራም። ሽማግሌው፤ ወጣቱና ምሁሩ ነቅቶባቸዋል። ቀናቸው የተቆጠረ ነው። አቦይ ስብሃት የተንኮል ገንቦ ነው። እጅ በደም የተነከረ ብዙዎችን በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ያስገደለ ሰው ነው። በመሰረቱ ወያኔዎች ከመግደል ሌላ ምንም ነገር አያውቁም። ያኔ ገና በረሃ እያሉ በሃሳብ ከአንድ አመራር ጋር ይጋጫሉ። ጊዜው ወያኔዎች ማግባትና መዋደድ የተፈቀደበት ጊዜ በመሆኑ ይህ ሰው አግብቶ ልጅቷ አርግዛ ነበር። የሃሳብ ግጭቱ በመጠንከሩ ወደ ሱዳን ይሰደዳል። ወያኔ ተናዶ ሚስቱን መርዝ አብልቶ ይገድላታል። ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው። ዛሬ ጄኔራል፤ ኮሌኔል፤ አምባሳደር ወዘተ የሚባሉት የወያኔ መሪዎች ገድለውና አስገድለው በሰው ደም ተጨማልቀው ነው እየኖሩ ያሉት። አሁን በሃገሪቱ ምድር ተሰባጥረው ሰርተው የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች ኑ፤ ውጡ ሃገር ጥላችሁ የሚለው ወያኔ ያው ያንኑ ቆሻሻ የፓለቲካ ስልቱን ያም በትግራይ ህዝብ ስም መነገድን ለመቀጠል እንጂ በ 27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ የት ወደቃችሁ ብሎ አልጠየቃቸውም። እንዲያውም አብረውት ደርግን ሲፋለሙ የነበሩ ተጋዳዪችን አዲስ አበባ ሲገባ ወደ 30 ሺህ የሚሆኑትን መሳሪያ አስፈትቶ እንዳሰናበታቸውና ለመከራ እንደዳረጋቸው ታሪክ ያመላክታል። በኤርትራ ለ 30 ዓመት የመገንጠል ጥያቄ የወንድማማቾች ፍትጊያ ቆስለውና አካላታቸው ጎድሎ ነጻነት ተገኘ ከተባለ በህዋላ ስለኑሮ ጥያቄ በማቅረባቸው በጥይት ተደብድበው ነው የሞቱት። ዳግመኛ ሞት ይሉሃል ይህ ነው። ታዲይ በዚህ እይታ ዛሬ በትግራይ መሬትም ሆነ በሌላው የጎሳ ፓለቲካ ጎጥ መሳሪያ ታጥቆ እንዘጥ እንዘጥ ማለቱ ትርፉ ምንድን ነው? ለማን ነው ትግሉ? ማን ሊበላ ማን ሊሞት? ማን ሊገደል፤ ማን ሊገድል? የእብዶች ፓለቲካ ሁልጊዜ በሰዎች መካከል ፍርሃትና ጥርጣሬን መንዛት ነው። የወያኔም ክህነቱ ተንኮልና ሴራ ብቻ ነው። ስለሆነም የትግራይ ተወላጆች ከእነ መሳሪያቸውም ሆነ እንዲሁ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ሲገቡ ህዝቡ በፍቅር ተቀብሎ ያስተናግዳቸው ዘንድ እመክራለሁ። አዎን ከእነዚህ መካከል ሰላዪችና የክፋት ተልኮ ያላቸው እንደሚኖሩ ጥርጥር የለውም። ግን ሁሉን በዘዴ በመለየት አብሮ መኖርን አብረን ልክ እንደ በፊቱ አብረን እንድንኖር መጣር አለብን።
  በመጨረሻም በወያኔና በሻቢያ ላይ አዲስ አበባም ሆነ በሌላው የሃገሪቱ ክፍል ሆናችሁ ክፋታቸውን የምትናገሩ፤ ተጻራሪ ሃሳብ ያላችሁ ባጭሩ ተቃዋሚዎች ጠንቀቅ በሉ እላለሁ። በአለም ዙሪያ የሻቢያና የወያኔ የስለላ መረብ ውስብስብ ነው። አውሮፓ ላይ ለፍልፎ አዲስ አበባ ላይ ታፍኖ የት እንደገቡ የማይታወቁ ብዙ ናቸው። ሻቢያም ሆነ ወያኔ ያፍናሉ፤ በመኪና ገጭተው ይገድላሉ፤ መርዝ አብልተው ይገድላሉ። ይህ አልሳካ ካላቸው ደግሞ ዘመድና አዝማድን ያሰቃያሉ ወይም እስር ቤት ይሰውራሉ። ስለሆነም ጠንቀቅ እና ወገብን ጠበቅ ነው። የሻቢያ የስለላ መረብ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በንግድ መልክ፤ በትምህርት ስም፤ በጉብኝት መልክ በማስመሰል በፊት የነበሩ የስለላው መረብ ተካፋዮችንና ከሃገር ወያኔ ያላባረራቸውን ኤርትራዊያን በማሰባሰብ ስለላው ጡፏል። የስለላው አላማ ሁለት ነው። አንድ የሻቢያውን አለቃ የሚቃወሙ ሁሉ እየተፈለጉ ስፍራ ማስያዝ፤ ሌላው ደግሞ ወያኔና ሻቢያ በባድሜ አሳበው ከመላተማቸው በፊት እንደነበረው ኤርትራን ቡና አምራችና ቡና ለአለም አቅራቢ ለማድረግ ነው። ባጭሩ ሁለተኛው ሃሳብ የወያኔን ምዝበራ በሻቢያው ምዝበራ መተካት ነው። የትግራይ ልዪ ሃይል አባላት ከታሪክ መማር አለባቸው እንጂ በወያኔ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ዳግም የትግራይን ህዝብ ለመከራ መዳረግ የለባቸውም። መገዳደል ይብቃ! ሽሹ!

 3. Are these TPLF sent spies entering the Amara region or what?

  How come not one of them defected to Afar if their intentions were only to run out of Tigray?

  Woyanen yamene gum yezegene

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.