እውን ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው? ዳንል ክብረትና አብይ አህመድ – ሰርፀ ደስታ

abiy ....ከዓመታት በፊት ዳንኤል ክብረት ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው የሚል አንድ አጭር ጽሑፍ አስነብቦን ነበር፡፡ ስለዚህ ጽሑፍ ዝርዝር አልገባም፡፡ ሆኖም ዳንኤል እንደጻፈልን ትንሽ ለማስታወስ የአንድ አገር ንጉስ በሆኑ አታላይ ጥበበኛ ነን ባሉ ሰዎች ሰራንልህ ያሉትን በኃጥያተኞች በዓይን የማይታይ ረቂቅና ግሩም ልብስ አለበስንህ ብለውት መለመላውን በአደባባይ በሰረገላው ሆኖ ለሕዝብ ሲገለጥ ሕዝቡ ሁሉ ኃጥያተኛ ላለመባል  የንጉሱን የረቀቀ የተባለውን ልብስ እያደነቀ ጎንበስ ቀና ሲል አንድ ሕጻን ልጅ ንጉሱን በግልጽ ራቁታቸውን መለመላቸውን ስላይ ለአባቱ አባዬ ንጉሱ እኮ ራቁታቸውን ናቸው ሲል  ሁሉም ወደ ሕጻኑ ዞረው አንተ በዚህ እድሜህ ምን ኃጥያት ብትሰራ ነው የንጉሱን እንዲህ የሚያምር በወርቅ የተንቆጠቆጠ ረቂቅ ልብስ ማየት ያልቻልከው ብለው አፈጠጡበት፡፡ ንጉሱ ራሱ በሕዝቡ ሁኔታ ተመስጦ እውነትም የረቀቀ ምርጥ ልብስ የለበሰ መስሎት ነበር፡፡ ሆኖም ያ ሕጻን ልጅ እውነቱን ሲናገር ንጉሱ እነዚያ አታላዮች እንዳታለሉትና ህጻኑ በትክክልም ራቁቱን እንዳየው አውቆ ለሕዝቡ ሕጻኑ ትክክል ነው፡፡ አልተሳሳተም አልዋሸም፣ ኃጥያትም ስለሌለበት ሁላችንም ስንዋሽ እሱ እውነቱን አየ ብሎ በሕጻኑ ላይ ያፈጠጡትን ሕዝብ ገሰፃቸው፡፡

ዛሬ የዛ ጽሑፍ ጸሐፊ ዳንኤል የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የቅርብ ሰው በሆነበት ዘመን ያ እሱ የጻፈው ተረት የሚመስል ጽሑፍ በተግባር እየሆነ እታዘባለሁ፡፡ ዳንኤል ሕጻኑ ላይ ከአፈጠጡበት እንዳንዱ ሆነ እመለከተዋለሁ፡፡ ዳንኤል ስለ አብይ አህመድ የሚናገራቸው ነገሮች የምርም ኃጥያተኛ ላለመባል ካልሆነ መቼም ጠ/ሚኒስቴሩ እያደረጓቸው ያሉት ድርጊቶች ጤነኛ አእምሮ ላለው ትክክል ናቸው ብሎ መቀበል ይከብዳል፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩም እውነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላሉ ሲባል  ብዙ ቲፎዞ ሆይ ሆይ ሲለው ጭራሽ ነገር ዓለሙ እየጠፋቸው የመጣ ይመስላል፡፡ አሁን ያለውን የጠ/ሚኒስቴሩን ችግሮች ለማወቅ እንደ ሕጻኑ ንጹሕ አእምሮ እንጂ ዳረጎትና ምናምን ለሚፈልጉ ዋሾዎች ይከብዳል፡፡

ለመሆኑ ግን ጠ/ሚኒስቴሩ መካሪ የለውም? እሱስ ቢሆን የአገር መሪ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ጥቂት እንኳን አይገነዘብም? እውን በቲፎዞ አጃቢነትና በአድናቂ ብዛት የት ድረስ ለመሄድ ታስቦት ይሆን? በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክና ሌሎች ሚዲያ አራጋቢዎችን ለፕሮፓጋንዳ ማሰማራቱ ሳያንስ ይባስ ዶክሜንተሪ ፊልም እየሰራ ራሱን ማስተዋወቅን ቀጥሎበታል፡፡ አድናቂዎቹ መልዕክታቸውን ሲጀምሩ ይሄን አለማድነቅ አይቻልም የሚል አዲስ የአብይ አህመድን ማሰታወቂያ ሀረግ ድረ-ገጾችን ሁሉ ሞልተዋቸዋል፡፡ ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው የሚል ካለ እሱ ኃጥያተኛ ነው፡፡ ለመሆኑ ግን የአብይ አህመድ አድናቂዎች የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስቴር ማለት ምንም ማለት እንደሆነ ይረዳሉ? በግሌ አብይ መጀመሪያ ላይ እያሳያቸው በነበሩ በጎ በመሰሉኝ ነገሮች ደግፌዋለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን ብዙዎች ስለ አብይ ሲዘፍኑ እኔን የእሱ ንግግሩም ሆነ ድርጊት ብዙም አይመስጠኝም ነበር፡፡ ከእሱ ይልቅ በለማ ብዙ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስቴር ከሆነ ለትንሽ ወራት በጎ የሚመስሉትን ነገሮች በማየቴ ከልብም ከሚደግፉት ነበርኩ፡፡ አብይ የመራው የነዳንኤልና ሌሎች ስብስብ ዲያስፖራን ለመጎብኘት በሚል አሜሪካ ደርሰው ከተመለሱበት ጊዜ አንስቶ ግን ነገሮችን ስመለከት ጥሩ አቅጣጫ ላይ እንዳልሆንን አስተዋልኩ፡፡ ምን ኣልባትም ስላልተረዳሁት አንዳንዴም ነገሮች ውስብስብ ስለሆኑ አቅምም ችግር ያለ እየመሰለኝ እንደምንም ለተወሰነ ጊዜ በደጋፊነት ግን እየሆኑ ያሉትን ነገሮች በደንብ ማስተዋል ቀጠልኩ፡፡ ቆይቶ ግን ሕጻኑ ያየውን እኔም ማየት ግድ ሆነበኝ፡፡

የኢትዮጵያ ልክ፡- እንግዲህ እንዲህ ነው የሚሆነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ መናፈሻ ሰራሁ በሚል ጭራሽ የኢትዮጵያ ልክ የሚል  ፊልም ይዞልን ብቅ አለ፡፡ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ልክ እውን መናፈሻ ነው? ይሄን አለማድነቅ አይቻልም የሚሉለት ቲፎዞዎችስ የመቶ ምናምን ሚሊየን ዜጎችን አገር ኢትዮጵያን የሚለኩበት በአዲስ አበባ መናፈሻ ነው? ለመሆኑ ግን በአዲስ አበባ መናፈሻ በሉት ሌላ መሥራት የጠ/ሚኒስቴሩ ሥራ ነው? ይሄ ነው የኢትዮጵያ ልክ? የእንስሳት መካነ ቦታ (ዙ) ማዘጋጀት? ለመሆኑ ግን እነዚያ እንሰሶች ከየት ነው የመጡት? እኔ እስከማውቀው የኢትዮጵያ ዱሮች ነጭ አንበሳ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ሆኖም እሱ ዙዎን የፈለጉት ሰዎች ፍላጎት ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን እነዚህ ሥራ የተባሉ ነገሮች ላይ እፈሰሰ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ እንደሆነ ልብ ሊባልም ይገባል፡፡ እንግዲህ አድናቂ ነን፡፡ ይሄን አለማድነቅ እያላችሁ ልክ እንደነዚያ ንጉሱን እርቃን በወርቅ ልብስ የተከፈከፈ እንዳሉት ያለ አይን ያላችሁ ኢትዮጵያ ለእናንተ በዚህ ደረጃ ከሆነች እናዝናለን፡፡

ጠ/ሚኒስቴሩ ዛሬ ላይ ትልልቅ ሊሠራቸው የሚችሉ ጉዳዮች እያሉት ተጠምዶ የምናየው በፊልምና በመናፈሻ ሥራ ላይ መሆኑ ትክክል ነው ብሎ ለማሰብ በምን መለኪያ ይሆን፡፡ እነዚህ ሥራዎች በኢትዮጵያ ደረጃ ይቅርና በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ትልቅ አደሉም፡፡ ሥራዎቹን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሊሠራቸው ከመቻሉም በላይ ለከተማው መዘጋጃ ቤት እንኳን ትልቅ ሥራ ተብለው የሚመደቡ አደሉም፡፡ ችግሩ የማሰብ አቅም ውሱንነት ስላለ እንዲህ ያለው ሥራ በከተማው መሪዎች ግዙፍ መስሎ ሊታይ ይችላል፡፡ ሌላው ቀርቶ የአዲስ አባባን ወንዞች ማጽዳትና የመናፈሻ ሥፍራዎች የማድረግ ሐሳብ ሌሎች ባለድርሻዎችን በማስተባበር ለመሥራት ከ8ዓመት በፊት የከተማው ጉዳዩ የሚመለከተውን መምሪያ አነጋግሬ ነበር፡፡ ሥራው የጠፈር ሳይንስን የሚጠይቅ አደለም፡፡ እንዴት መሠራት እንደሚችል ስናናግራቸው ለእነሱ ተራራን የመግፋት ያህል መሥሎ ነበር የታያቸው፡፡ ይሄው ዛሬ ለገበያ ማሟሟቂያ አድርገውት እናያለን፡፡ ሊያውም በዋናው በጠ/ሚኒስቴሩ፡፡ እነዚህ ሥራዎች የኢትዮጵያ ልክ ሳይሆኑ የከተማውም ቅንጣት ሥራዎች ናቸው፡፡ እንግዲህ ከዚህ በላይ መሥራት አቅም ውሱኑነት ላለበት የኢትዮጵያ ልክን ሊረዳ የሚችል አይመስለኝም፡፡

ሌላው የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ በሚል የተከፈተው ዘመቻ ነው፡፡ በእርግጠኝነት በዚህ አካባቢ ከበቂ በላይ ባለሙያዎች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ሥራውንም በሐላፊነት ቢሰጣቸው ብዙ ጫጫታ ሳያሰሙ ውጤቱን ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ ችግሩ አሁንም ጠ/ሚኒስቴሩ ማንንም ለማስጠጋት አይፈልጉም፡፡ ምን ዓልባት አማካሪ ሊኖሯቸው ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን እንደመሰለኝ ያው ከላይ የንጉሱን የወርቅ ልብስ ለማየት የታደሉ ጻድቃን በመሆናቸው እንደ ሕጻኑ አይነት አይን ያለውን ማስጠጋት አይፈልጉም፡፡ ይሄ ዓለም ዓቀፍ ትኩረት የሚያሰጥ ነው ብለውም ስላሰቡ ይመስላል፡፡ ያም ሆኖ አሁንም ይሄን አለማድነቅ አይቻልም ለሚሉት ደጋፊዎቻቸው ለመሆኑ መለስ ዜናዊ ከዚህ በሠፋ እንዲያ ያለ ሥራ ዕቅድ እንደነበራቸው ያውቁ ይሆን፡፡ ችግኝ መትከል ከሆነም ከሚኒሊክ ጀምሮ በኃይለስላሴ፣ በመለስ ችግኝ ሲተክሉና ሕዝቡን ሲያነሳሱ እንደነበር ሳናይ ቀርተን አይመስለኝም፡፡ የበፊቶቹን በማስረሳት የራሳቸውን ትልቅነት ለማሳየት በሚጥሩት አይናችን ካልተጋረደ፡፡ በእርግጥ ነው ለበፊቶቹ መሪዎች ችግኝ መትከሉን አርዓያ ለመሆን ከማሰብ የዘለለ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ አልተጠቀሙበትም ይሆናል፡፡ በእርግጥም በእነሱ ደረጃ ያለ ሰው እንዲህ ያለው መታወቅ አይጠቅምምናም ነው፡፡ በነገራችን ላይ ችግኝ በማስተከልና ዛሬም ድረስ በቀሩ አሻራዎች መታሰብ አለበት ከተባለ ደርግ (መንግስቱ ኃይለማሪያም) ነው፡፡ ወያኔ በትግራይና ከፊል አማራ በመሬት ማገገም ፕሮገራም ትልልቅ ፍሬያማ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡  ዛሬ እንደ ልዩ ሁኔታ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው ወሬ እንዲህ የበዛው እንዴት የመለስ ፓርክ በሚል በየቀበሌው ሳይቀር በኃይለማሪያም ደሳለኝ ጊዜስ የነበሩ እውነቶችን ይረሳል፡፡ ጥያቄው ስኬታማ ነበሩ ወይ የአሁስ ነው? የበፊቶቹ ቢያንስ ለወሬ ብዙ ወጭ ስላላስወጡን ጥሩ ነበሩ የአሁኑ ግን እንደዛ አደለም፡፡ በየ ዓመቱ እንደበቆሎ ማሳ አንድ ቦታ ላይ ችግኝ እየተከሉ በቴሌቪዥን ከመታየት ያለፈ ፋይዳም ያለው አልመሰለኝም፡፡ አሰራሩም ጠ/ሚኒስቴሩ እኔው ብለው በዘመቻ የሚያስኬዱት እንጂ እቅድና ታስቦበት ስላልሆንም፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የተባለውም ቢሆን የጠ/ሚኒስቴሩ ሥራ መሆን ባልነበረበት፡፡ በሚኒስቴር ደረጃ አሁን ደግሞ ቢያንስ በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግስት መዋቅር አለ፡፡  ከዚህ በዘለለ ጠ/ሚኒስቴሩን እንዲህ ባተሌ ሊያደርጋቸው ባልተገባም ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩ መሥራት የሚገባቸውን ትተው የሌሎችን ሥራ ባይሻሙ ብቻም ሳይሆን ባያበላሹ ጥሩ ነው፡፡ ግዙፍ ሥራዎች ነበሯቸው

  1. የሕግና ሥርዓት እንዲሁም የዜጎች ደህንነት፡- በመናፈሻ ሥራ የተጠመዱት ጠ/ሚኒስቴር ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በማንነታቸው በአሳቃቂ ሁኔታ ተገድለው መግለጫ እንኳን ለመስጠት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ እንኳንስ እንደመሪ የተጎዱትን ዜጎች ቦታቸው ድረስ ማጽናናት ይቅርና፡፡ በዚሁ ሰሞን የታዘብኩት የሲዳማና የአኦሮሞ አረመኔ ወሮበሎች በዜጎች ላይ ያየንውንና የሰማንውን አይነት አረመኔያዊ ድርጊት ሲፈጽሙ ትዕዛዝ አልደረሰኝም በሚል ዜጎችን በአራጆች እንዲታረዱ ቆሞ ያየ መከላከያ፡፡ እንኳን ሰው ከጎዳና ወጥቶ ስንጥር ዛፍ እንኳን ያልነካውን የወላይታን ሕዝብ ሰላማዊ ጥያቄ ጠያቂዎች ላይ ግን ጥይት ለማርከፍከፍ በፍጥነት ታዞ አይተናል፡፡ ይሄንንም አለማድነቅ አይቻልም ይሉን ይሆናል ጻድቃን የአብይ አህመድ አድናቂዎች፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩ ስለኢትዮጵያ ሲናገሩ እንባቸው ይመጣል ያለን የንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው ጸሀፊው ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ፡፡
  2. የዜጎች በሚደርሱባቸው የተፈጥሮ አደጋዎች ትኩረት ሰጥቶ መርዳት፡- በአፋርና በተለያዩ ቦታዎች በጎርፍ ምክነያት ብዙ ዜጎች ተጎድተው በአለበት ወቅት ከላይ እንደጠቀስኩት በአካል በቦታው ተገኝተው ማጽናናትና የሚያስፈልጋቸውንም ነገር ማቅረብ የአገሪቱን ሎጂስቲክም ለእንደዚህ ያለ አደጋዎች ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ መሥጠት እንደመሪ የሚጠበቅባቸው ነበር፡፡ ጭራሽ ዜጎችን ለመታደግ ሚዲያዎች እንኳን ትኩረት ሰጥተው እንዳይሰሩ የኢትዮጵያ ልክ በሚል ሚዲያዎችንና የሕዝብን ትኩረት በመናፈሻ ማስታዎቂያ ሞልተዋቸው ታዘብን፡፡ ይሄን አለማድነቅ አይቻልም ለምትሉ የንጉሱ አድናቂዎች የኢትዮጵያ ልክ የአዲስ አበባ መናፈሻ ሳይሆን ሌሎች ትልልቅ ነገሮች እንደሆኑ ማስተዋል ብትችሉ፡፡

ሌላው የተፈጥሮ አደጋ አሁን ዓለምን ጭምር አስጨንቆ ያለው የበሽታ ስርጭት ነው፡፡ ዓለም በሙሉ በዜጎቻቸው ላይ በመጣው በዚህ አደጋ ከምንም በላይ ትኩረት ሰትተው እየሰሩና ሌሎች ፕሮግራማቸውን ሁሉ በአጠፉበት ወቅት የመናፈሻ ሥራን ለማስተዋወቅ ቅድሚያ መስጠት በዓለም ፊት ራሱ ብዙዎች እንዲታዘቡ ሆነዋል፡፡ ይሄ የሚያሳየው የጠ/ሚኒስቴሩ ትኩረት ከዜጎች ደህንነት ጋር ሳይሆን ራሳቸው ገበያ ይሆነኛል የሚሉትን ማስተዋወቅ ሆኖ ታዝበናል፡፡ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚጋባ ብዙ ሌሎች ጉዳዮችም አሉብን፡፡ ከጎርፍ አደጋ በላይ በያመቱም የሚራብ ሕዝብ አለብን፡፡ ይሄን ሁሉ አገራችን ያሉ ዲፕሎማቶች ይታዘባሉ፡፡ ጥሩ ገጽታም አደለም፡፡ እነሱ የሚሰጡትን እርዳታ እንዲህ ጠ/ሚኒስቴሩ ቅድሚያ ስላሉት ብቻ እንደፈለጉ የሚደፉት ሊሆንም አይገባም፡፡ በእነዚህ የጠ/ሚኒስቴሩ ወሳኝ ሥራዎች እየወጣ ያለው ገንዘብም ሥርዓት ያለው አይመስልም፡፡ ይሄ የኢትዮጵያ ልክ ከሆነ አዝናለሁ፡፡

  1. አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጄክቶችን፡- ዛሬ አገራዊ ፕሮጄክቶች በአብዛኛው ቆመዋል እየተባለበት ባለበት ሁኔታ ነው መናፈሻ መስራት የኢትዮጵያ ልክ የሆነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ትልቅ ታሪካዊና ዛሬም ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ያለው የጣና ሐይቅ ይሄው አሁንም ባለቤት አጥቶ አደጋው ቀጥሏል፡፡ ያው የእይታ ችግር ስላለ አማካሪዎችም ሁሉም ጻድቃን ስለሆኑ መሠለኝ ሰሞኑን ጎርጎራ፣ ወንጪና የሆነች ሌላ ኩሬ ፕሮጄክት ወሬዎ መሀበራዊ መገናኛን አጨናንቆ አየሁ፡፡ ቦታዎች መርጦ ማልማትና ለጎብኝ መስህብነት ማዋል መልካም ነው፡፡ ግን ጣናን የሚያህል የአገሪቱን ወሳኝ ሐይቅ ከሌሎች ኩሬዎች ጋር በማሳከር ትኩረት ማሳጣት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ጎርጎራ ላይና ወንጪ ላይ ስለሚሰሩ ሆቴሎች የባለሐብት እንጂ የመንግስትም ፕሮግራም አደለም፡፡ መንግስት ለመዋለንዋይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ከተባለ ደግሞ በብሔራዊ ፓርክነት የተመዘገቡት እነ ሻላና አብያታ እያሉ ወንጪን የመሰሉ ቦታዎች ይሄን ያህል ትኩረት የተሠጠበት ሁኔታ ብዙ ነገሮችን እንድታዘብ አድርጎኛል፡፡ ወንጭን አውቃታለሁ፡፡ ባለሕብት ነኝ እዛ ያዋጣኛል ያለ ሆቴል ሆነ ሌላ ልማት ቢሰራ መልካም ነው፡፡ ግን ወንጭ በየትኛውም መሥፈርት በኢትዮጵያ ደረጃ ቅድሚያ የሚሠጠው ቦታ አደለም፡፡ የወንጪ ሐይቅ እንኳንስ በኢትዮጵያ ደረጃ በክልሉም ቅድሚያ የሚያገኝ ባልሆነ፡፡ ዞኑና ወረዳው ምን አልባት፡፡ ሌላኛውን የተጠቀሰውን ሀይቅ ከእነጭርሱም አላውቀውም በሌላ ሥም ካልተጠራ በቀር፡፡ እኔ የኢትዮጵያን አብዛኞቹን ሐይቆች በአካል ጭምር አውቃቸዋለሁ፡፡ ይሄም የኢትዮጵያ ልክ በሚለው አጀብ ውስጥ ያየሁት ነው፡፡

በአጠቃላይ የንጉሱን እርቃን አለማየት ንጉሱን ከብርድ ሊያድነው አይችልም፡፡ የንጉሱን ወርቃማ ልብስ ከአዩለት ከእነዚያ ሁሉ ጻድቃን ይልቅ የአንድ ኃጥያተኛ ሕጻን አይን ንጉሱን ከብርድና ከሐሩር ታድጎታል፡፡ ስለዚህ አድናቂዎች ሆይ ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ የሕጻኑን አይን ይስጣችሁና እውነትን ተናገሩ፡፡ ለጠ/ሚኒስቴሩም የሚጠቅመው ይሄ ነበር፡፡ አሁን ጠ/ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ ልክ ሆኖ ባዩበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን እናፍራለን፡፡ የኢትዮጵያን ልክ አሳምረን እናውቀዋለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከክፉ ይጠብቅ! አሜን!

 

https://zehabesha.info/archives/109709

 

https://youtu.be/-eST2qqFzMw

3 Comments

  1. “ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!”
    ይህ ምርቃት ለአንተው ይሁን እጅግ ለተምታታብህና ልብህ በክፋት ለተሞላው:: ማን እንበልህ? የልማት ምቀኛ? ዐቢይ በ 2 አመታት ያከናወነውን ሌሎች በ10 አመታት አላደረጉትም ያውም ወያኔ የማያቋርጥ ጦርነት እያካሄደበት::
    በነገራችን ላይ ፅሁፍህን ወደ ትግራይ ሚዲያ ሀውስ ብትልክ በአድናቆት ይቀበሉሀል:: ማፈሪይ ካሁን በሗላ የምትለጥፈውን ቅራቅንቦ አላየውም

  2. አሁን ሠርፀ ባነሣው ነጥብ ላይ አንድ ጸሐፊ ቀደም ሲል በዘሀበሻ ቆንጆ ጽሑፍ እንዳሥነበበን አስታውሣለሁ፤ ችግሩ ሰሚ የለም። ርዕሱ “የነዳንኤል ክብረትና የኔ – ሁለት አቢይ አህመዶች! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ” የሚል ነው። በድጋሚ ፓሥት ቢደረግ እጅጉን ወቅታዊ ነውና ዘሀበሻዎች ፈልጋችሁ ብትለጥፉት ጥሩ ነው። ጉዳዩ ዲያቆኑ ሥለአቢይ ያለው የተለዬ ኢትዮጵያዊነት ነው፤ ግን በተግባር ሢታይ ሠርፀ እንደሚለው ነው። በፈጠራችሁ ያን ጽሑፍ እዩት።

  3. On our way before we fight Egypt we will have a journey to Yemen to drop some locust eating cockroaches. That is people like you who are created by a lesser god. Lest yo forget, the Gonderes since their Axumite empire are your masters whom you ancestors served for thousands of years. But again your back stubbier habit is from your genes and it won’t let you think free. You also think you are a warrior, we will see about that, I bet you won’t last an hour when the gonderes start shooting. But one thing is for shure, you are a thief a liar, a beggar and a prostitute. Leave the battle to the warriors if you don’t believe me wait for “six hours to mekele” March. Hey, cockroach have you ever heard of a saying “ don’t wish too much because you may get it and you don’t know what to do with it?” It is coming for you. Let see if the bloody Arab is going to save you. The only Arab land you are going to join is the miserable original country of yours called Yemen and we are sure of it that will Happen.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.