ፍፋናዎች በቴሌቭዥን ካሰራጩት የአቶ ሊላይ ሃይለማርያም የስም ማጥፋት ሙከራ – አበበ ገላው

ፋናዎች በቴሌቭዥን ካሰራጩት የአቶ ሊላይ ሃይለማርያም የስም ማጥፋት ሙከራ ጋር በተያያዘ እርምት ለመጠየቅ ባደረኩት ሙከራ ሳቢያ ሊያጉላሉኝና ደጅ ሊያሰጠኑኝ ሞክረዋል። ይሁንና ትናንት ከብዙ ጥረት በሁዋላ የፋናን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በቀለ ሙለታን በስልክ ለማናገር ችያለሁ። እርሳቸውም ጥያቄዬን ተቀብለው እኔና አቶ ሊላይን በፋና ቴሌቪዥን ላይ አቅርበው ለማፋጠጥ እና ተጨማሪ መረጃ አጣርቶ ለማቅረብ ቃል ገብተዋል።ለዚሁም ሳላመሰግን አላልፍን።
በዚህ አጋጣሚ ከአለም ዙሪያ በመደወልና በተለያየ መንገድ ድጋፋችሁን ለገለጻችሁልኝ እንዲሁም በጽሁፍና በሚድያ እውነቱ ጠርቶ እንዲወጣ ጥረት ላደረጋችሁ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ልባዊ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ። በወገኔ ኮርቻለሁ!
አንዳንዶች እንደሚመክሩኝ ሳይሆን ጉዳዩን ፈጽሞ ችላ ብዬ የማላልፈውና እስከ መጨራሻው እውነቱን ፍንትው አድርጌ ለማውጣትና ግለሰቡንም ይሁን በዚህ ድርጊት ተባባሪ የሆኑን ሁሉ በህግ አግባብ የምጠይቅ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ። እኔ ለአንዲት ሴኮንድም ቢሆን የወያኔን ተዘርዝሮ የማያልቅ ሃጢያትና የገለማ የግፍ ታሪክ ለመሸከም ፈጽሞ አልፈቅድም። እውነት ያሸንፋል!
ለማንኛውም ሰሞኑን ፍጥጫ ፋና ላይ ጠብቁ!

2 Comments

  1. አይ አቤ ይሄን ያህል እርቀት መሄድ አልነበረብህም እኮ ሲሳይ/ሰላይ/ሲላይ የተባለዉ ትግሬ ተመቻችቶ ለቃለ መጠይቅ ሲቀመጥ ያሰበዉን ሳይሆን ትርፍ የሚያመጣለትን ሊያስደምጠን እንደሞከረ የምናዉቅ አዉቀናል። የትግራይ ፖለቲከኞች ከአባታቸዉ ከአቶ አረጋዊ በርሄ ጀምሮ ሚዲያ ላይ ሲቀርቡ ተጨንቀዉ አስተካከልን ብለዉ አበላሸተዉ ፍሬ ከርስኪ የሆነ ትያትራቸዉን ዉድ በሆነዉ የቴሌቭዥን ስርጭት አባክነዉ ሰራንላቸዉ እያሉ ይሰናበታሉ። በመሰረቱ አንድ ሰዉ ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲቀርብ ያወቀዉን ያሳዉቃል ከሚል እሳቤና ካሳለፋቸዉ የስራ ልምድና ካካበታቸዉ እዉቀቶች ያካፍላሉ ከሚል እሳቤ መሆን ነበረበት። ይህ ደናቁርት ሰላይ እሱ እራሱን ከሚያዉቀዉ በላይ አምበሳዉ አቻምየለህ ታምሩ አበጥሮ ስለነገረን እሱን ዳግም ወደ ቴሌቭዢን መስኮት አቅርቦ መመልከትና ማዳመጥ እራሱን የቻለ ቅጣት በመሆኑ ዳግም ባናየዉ መልካም ነዉ ይልቅስ አቻምየለህ ሁለተኛዉን ክፍል አቀርባለሁ ስላለ ቶሎ እንዲልክልን እሱን መማጸን ነዉ።

    በተረፈ ሰላይ አንተን የጠመደዉ መለሰ ዘራዊን ከላይ በተሰጠህ ሀይል በመብረቅ ፍጥነት ስለገላገልከን በዚህ ተከፍቶ ነዉ። ስለዚህ አንትን ይልቅ የምንጠይቅህ ይህ ግምቦት/አንዳርጋቸዉ/ነአመን ዘለቀ/ብርሀኑ ነጋን ታክከህ የምትመጣዉን ትተህ በሁለት እግርህ እራስህን ችለህ ለኢትዮጵያ ብትቆም ላንተ ያለን ክብር ከፍ ያለ ይሆናል። በተለይ በተለይ ያንን አጋንንት ብራቅ እንደመታዉ አድርቀህ ማስቀረትህ ገና ስምህ ዘመን ተሻጋሪ እናደርገዋለን። ብትችል ከዛ ሰላይ ጋር አብረህ አትቅረብ ያቻምየለህን ጽሁፍ ጠብቅ በሀሳብ ብትመታዉም ከአቻምየለህ በላይ እንደማታሳምመዉ በእርግጠኝነት መናገር ይችላል። ሰላም ሁን አቦ ዘመነኞችንም እንዲሁ ክዉ አድርገህ ብታስቀርልን መልካም ነበር።

  2. In the first place the media in Ethiopia is corrupted since the time of the emperor for not doing the right job of presenting balanced news to the people.The emperor was having puppets who ignored the extreme poverty and oppression of the people,the military Junta Derg was using the media for promoting the evil Marxist ideology while the so called journalists ignored the massacre of murderer of hindered thousands jailed and killed for opposing the regime.Same was true during the TPLF tribal rule the media continued to be mouth piece of the divisive abusive TPLF regime.this time while we have better options of press, the media still presents what is interesting for the current government and the party. Lilay was a TPLF hard core member who pass secrets of Ethiopian government living in the capital and ruined our economy by the sabotage of TPLF. How on earth the Abiy government media presented him.On another aspect Abebe Gelaw was not fair to hide the secrets of Abiy Ahmed involvement when Abiy was director of the intelligence of TPLF. Do Justice for all with out favorism!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.