በአቶ ጃዋር መሐመድ ቤት በብርበራ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ ለግለሰብ የማይፈቀድና ሕገወጥ መሆኑ መረጋገጡ ተነገረ

Getachew reda and Jawar Mohamedከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው አቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ በግለሰብ እጅ መያዝ የሌለበት ከመሆኑም በተጨማሪ ሕገወጥ መሆኑ እንደተረጋገጠ ዓቃቤ ሕግ ተናገረ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ፀጋ እንደገለጹት፣ የተጠርጣሪው ቤት ሦስት ጊዜያት ተበርብሯል፡፡
በዚህም የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የሳተላይት መሣሪያዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
የሳተላይት መሣሪያው ከአምስት እስከ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንና የአገሪቱ ቴሌኮም የኔትወርክ አገልግሎት ቢቋረጥም በራሱ የሚሠራ መሆኑን አቶ ፈቃዱ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሳተላይቱ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች እየተጻፈ እንደሚገለጸው የሁሉንም ስልክ መጥለፍ አይችልም፡፡ ነገር ግን በተጠቀሰው ርቀት ላይ ግን የተለያየ ሥራ ሊሠራበት እንደሚችል ተናግረዋል፡
መሣሪያው በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በኩል አለማለፉን ኮሚሽኑ ማረጋገጡን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በግለሰብ እጅ እንዲቆይም ሆነ እንዲያዝ የማይፈቀድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እንደነዚህ ዓይነት መሣሪያዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅደው ኢትዮ ቴሌኮም ሳይሆን ከዓመት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን መሆኑንና እሱም ስለ ሳተላይቱ ምንም ዓይነት ፈቃድ እንዳልሰጠ መግለጹንም አቶ ፈቃዱ ገልጸዋል፡፡ ሳተላይቱ እንዴት እንደገባና ከነማን ጋር በመመሳሰጠር እንደገባ በቀጣይ የሚጣራ መሆኑንም አክለዋል፡፡
የግለሰቦችን ስም እየጠቀሱ ‹‹የእነ እገሌ ስልክ ተጠልፎ ነበር›› የሚባለው መረጃ ትክክል አለመሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር-

1 Comment

  1. አህመዲን ጀበል ይሄን ሁሉ ጉድ እያየ ሽምግልና ይሄዳል ጁዋርን ሊያስፈታ? ፍትህ ቢኖር ዋና ታሳሪ አህመዲን ጀበል ነበር። የኢትዮጵያ አምላክ እሱንም ጠብቆ ዋጋውን ይሰጠዋል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.