ዘር-ፍጅት ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ትብብር ጥሪ

Sage

በሃገራችን ብሔርን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ አገዛዝ ተግባራዊ ከሆነበት ከ1983 ዓም ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ ብሔር ተለያይቶ እንዲፉጅ መንግሥት መርዘኛ ተንኮል ሲፈጸም ቆይቷል ። የኢትዮጵያን መዐከላዊ መንግሥት ላለፉት 27 አመታት ተቆጣጥሮ የቆየው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሃት) ሕዝባችን ለዘመናት ገንብቶት የኖረውን ሕብረ ብሄራዊ አንድነቱን በማላላትና እርስ በእርስ በጠላትነት እንዲተያይ በማድረግ ዛሬ ለደረስንበት አስከፊ ብሄራዊ ቀውስ ዳርጎናል ።

ሕወሃት በዋናነት፣ ሌሎች ተገንጣይ ኃሃይሎች በተላላኪነት፣ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ስደት ምክንያት ሆነዋል ። በተለይም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በአርባጉጉ፣ በወተርና በበደኖ ያካሄደው አንድን ብሔር መሠረት ያደረገ ዘግናኝ ጭፍጨፉ የሚዘነጋ አይደለም ። እነዚህ ጽንፈኞች የአማራን ተወላጆችና ክርስቲያኖችን በመነጠል ላደረሱት የጅምላ ጭፍጨፉ በተገቢው መንገድ አለመጠየቃቸው ከዛ በሗላ ለተከተሉት ተደጋጋሚ የዘር ጭፍጭፉዎች ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ።

በቅርቡም በአክራሪ የኦሮሞ ሃይሎች በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በባቱ፣ በአርሲ ነገሌና በጅማ ለደረሰው አማራንና ክርስቲያኖችን የለየ ጭፍጨፉ መሰረቱ፣ ለሚፈጸመው ተደጋጋሚ ወንጀል ተጠያቂ የሚሆን አካል አለመኖሩ የፈጠረው ክፍተት ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም ። ከሁሉም በላይ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት ሃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ለመወጣት አልቻለም ። በፊትም አሁንም በጸጥታ መዋቅሩ ያሉ ሃላፊዎች ለወንጀኞች ተባባሪ በሆኑ አካላት መሞላታችውን መንግሥት ባለመቆጣጠሩ ለደረሰው እልቂትና ውድመት ከተጠያቂነት
አያመልጥም ።

ከዶር አብይ አህመድ ሹመት በኋላ በተደጋጋሚ ለተካሄደው በአማራና በክርስቲያኖች ላይ ለደረሰው ጭፍጨፉ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው፣ ሕዝብ በይፉ የሚያውቃቸው ግለሰቦችና አካላት ለሠሩት ወንጀል ሕግ ፊት ሲቀርቡ አልታየም ። መንግሥት ሕግን ለማስከበር ዳተኛ መሆኑ ሰሞኑን ለደረሰው፣ በአይነቱም በመጠኑም ከፉ እና አሰቃቂ ለሆነ፣ እልቂትና ውድመት አብቅቶናል ። እስካሁን የተፈጠረውን በዘር ላይ ያተኮረ እልቂት ከመደባሰስ አልፎ፣ የችግሩን ክብደት ቀርቶ መኖሩን እንኳን መንግሥት በገሃድ ለማዎቅ ፈቃደኝነት አያሳይም። ወደፊትም መንግሥት ወንጀለኞችን ይዞ ለፍርድ ያቀርባል ብሎ ለመገመት ያስቸግራል ።

በሃገራችን ከዚህ በሗላ ተመሳሳይ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፉና ውድመት እንዳይከሰት፣ ወንጀለኞችና ተባባሪዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንቅስቃሴ ጀምረናል ።

እንቅስቃሴያችን ሰብዓዊ መብትን ለማስጠበቅና ወንጀለኞችን ሕግ ፊት ለማቅረብ ከተሰማሩ ሃገር-አቀፍና አለም-አቀፍ ተቋማት ጋር በመደጋገፍና መረጃ በመለዋወጥ ለመሥራት ተዘጋጅቷል ። ይህ ጅማሮ ለውጤት እንዲበቃ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከምንዘረጋቸው መዋቅሮች ጋር በመሆን ሕጋዊነትን በተከተለ መንገድ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን ።

የሃገር ሰላምና የሕዝባችን ደህንነት እንዲጠበቅ የሚፈልጉ አካላት፣ የመንግሥት አመራሮች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ያላቸውን ማንኛውንም የተፈጸመውን ወንጀል የሚገልጽ መረጃ ወደ እኛ እንዲልኩልን ፍትህ በሚሻው ወገኖቻችን ስም እንጠይቃለን ።

መርጃዎቹም:-
1. የተቀረጹ የቪዲዮ ምስሎች
2. ፎቶዎች
3. የሰነድ ማስረጃዎች
4. በድምጽ የተቀረጹ (ኦዲዎ) ማስረጃዎች
5. ወንጀሉ ሲፈጸም ያዪ ፈቃደኛ ምስክሮች
6. በማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት ጄኖሳይድ እንዲፉፉም ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሚድያዎችና ግለሰቦች ከግዜ በኋላ ያጠፏቸው ጽሁፎችና ምስሎች።

ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቱን ሊያሳዩ ይችላሉ የምትሏቸውን ተጨባጭና ሕጋዊ መረጃዎች በቅርቡ በምናሳውቀው መንገድ እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ።

ፍትሕ በግፍ ለተጨፈጨፉ ወገኖች!

SAGE Executive Committee

[email protected]

July 28, 2020

2 Comments

  1. መልካም ነው፤፤ ይህ ቀደም ብሎ በተፈጸሙት ወንጀሎች ስላልተደረገ ዛሬም እልቂቱ ቀጥሉዋል፡፡ መረጃው ከተሰበሰበ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሆኖ በአንድ ቁዋት ተከማችቶ፣ በባለ ሙያ ተተንትኖ እና ተተርጉሞ ለፍትህ አካል መቅረብ አለበት፡፡ ጥሩ ሐሳብ ነው፡፡ዜጎች ሁሉ ተባበሩ፡፡

  2. የዘገዬ ቢሆንም መልካም ሃሳብ ነው፤ዘር ተኮር ጥቃት በቃ ሊባል ይገባል፤የጥላቻ መልዕክቶችን የሚያሰራጬ በሰው ልጅ ህይወት የሚቀልዱ ቁማርተኞችን ህዝቡም መንግስትም ሊዋጋቸው ይገባል።
    መንግስት ቸልተኛ ነው፤ህግና ስርዓትን አላስጠበቀም ተብሏል ልክ ነው በጊዜው ከበዛ ትዕግስቱ አንጻር በዙ ጥፋቶችን አስተናግደናል ።አሁን ደግም የከፋ ነገር ተከስቶ መንግስት እርምጃ ሲወስድ ታሰሩብን፣ተገደሉብን በሚል መንግስትን የሚኮንኑ ወገኖች ተነሱ ።ስለዚህ አንዱን መምረጥ አለብን ፤አየተጨፈጨፍን መንግስት ዝም ይበለን፤ ወይም አመጸኛና ሀኬተኛ በሆኑት ላይ በትሩን ሲያነሳ ጎሽ ፣በርታ እንበል ።
    ግራ ተጋብተን ግራ አጋቢዎች አንሁን።እናስተውል።
    ስለ በጎ አሳባችሁ አመሰግናለሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.