ማላጅ  – ያሚ ፀጋ

gettyimages 1175318270 1024x1024 1ትናንት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ከፍተኛ የመንግስት እና የህዝብ ተጠሪዎችን በመጋበዝ በጅምር እና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙትን የዕንጦጦ እና ሸገር  መዝናኛ ስፍራወችን ( የልማት ስራወችን)  የማስጎብኘት ፣ ማብራሪያ እና ትንተና መስጠታቸዉንና ይህ በሚመለከት ያላቸዉን ብሄራዊ ቀናኢነት እና ጥረት ልባዊ ተነሳሽነጽ በማድነቅ ሲሳይ መንግስቴ(ዶ/ር) በፅሁፍ ገልፀዋል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዉያን  የክቡር ጠቅላይ መኒስቴር አብይ አህመድ  ምኞት እና ራዕይ  ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ የክብር ማማ ሠገነት ለማዉጣት እና ህዝቧን ከተረጅ እነት እና ጠባቂነት  ባርነት ነጻ ለማድረግ  እንደሆነ ከባዕለ ሲመት ንግግር(መግለጫ) አስከ አሁን ዕለት ብርቱ ድካም እና ተጋድሎ የሞት ሽረት ትግል  ከሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር  ማድረጋቸዉ አይካድም፡፡

ነገር ግን ይህን ብሄራዊ  እና ህዝባዊ ዕድገት፣ ልማት እና አንድነት የሚያቀረሻቸዉ  በቅርብ ርቀት መኖራቸዉን ከረጅም ጊዜ ቅዠት እና ቀቢፀ ተስፋ  ክፋት  በምግባር እና በተግባር የሚታወቁ እንደመሆናቸዉ  ችላ የማለት የአፍታ ትኩረት  እንዳይነፈግ እንዲሁም በአገር እና በህዝብ ችግር (ዋጋ) የግል እና የቡድን ጥቅም ህዝብ በማስለቀስ  ሲያጋብስ እና ሲያገበሰብስ የነበር አሁንም ስላለ መጠርጠር እና መመንጠር ዕለታዊ እና ወቅታዊ ተግባር ነዉ ፡፡

በያንዳንዱ የአገር እና ህዝብ የዕድገት ጥንስስ እና ፈዉስ  ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ መኖራቸዉ  አጠያያቂ አለመሆኑን እየተገነዘብን ….“ጠርጥር ከገንፎ መሀል አይጠፋም ስንጥር ”…..እንዲሉ አበዉ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዉያን  መሆኗን አስረግጠን በቃል እና በገቢር ማለፍ አለብን፡፡

ወደ ተነሳሁበት የ ዶ/ር ሲሳይ  አስተያየት ከተረዳሁት መልዕክት አድናቆታቸዉ አድናቆታችን ሁኖ ነገር ግን በሰጧቸዉ ሁለት አስተያየቶች ላይ እኔ የገባኝን ልበል፡፡

addis ababa park addis ababa 3

፩ኛ.  ጠቅላይ ሚ/ሩ የመግላጫ እና ማብራሪ ስራ ለባለሙያ ቢሰጡ ላሉት(ዶ/ር) እኔ በሁለት መሰረታዊ ጉዳይ ለየት ያለ እይታ አለኝ፡፡

ይኸዉም ፡ –

 • ጠ/ሚኒስቴር አብይ በጉዳዩ ላይ ያላቸዉ  ጥልቅ እና በሩህ ፍላጎት ፣ ምኞት፣ የመረዳት እና ማስረዳት ፣ የመተንተን ብቃት ከዉብ አቀራረብ ጋር መሆኑን ከዶ/ር ሲሳይ ከተረዳን መሰጠት ነዉና ሁሉም የየራሱ የፀጋ ስጦታ ስላለዉ እርሳቸዉ(ጠ/ሚ) ማብራራታቸዉ ተገቢነት እና ልክነት አለዉ ፡፡
 • ሌላኛዉም ባለሙያዉ (የስራ) ባለቤት ምንአልባት ህዝብን እና አገርን ሊያነቃቃ በሚችል አቀራብ እና ለዛ ሊያከናዉን የሚችልበት ሁኔታ (ብቃት) ስለመኖር አለመኖር ልብ ሊባል እና ሊታሰብበት ይገባል እና ከዚህም እኳያ እንደ መሪ አስተባባሪ ልክ ናቸዉ የሚል እይታ አለኝ፡፡

፪ኛ. ሌላዉ ቋንቋ መቀላቀል ለሚባለዉ  በልዩነት መስማማት እንዳለበት የሚታይበት ጉዳይ ነዉ  ፡፡

 • ልዩነት ያልኩት ቋንቋ አጠቃቀም የመማር አለመማር (በዘመናዊ ትምህርት የመኖር አለመኖር) አይደለም ፡፡አንድነት የምለዉ ቋንቋ በራሱ ምልዑ ስለሆነ ሳይበረዝ እና ሳይደለዝ ጥቅም ላይ ሲዉል ለታዳሚዉ ብቻ ሳይሆን መልዕክት ለሚያስተላልፈዉም አካል የሚኖረዉ ቅቡልነት ከባህል፣ ከብሄራዊ ክብር እና ፍቅር እና ከአገር ልዋላዊነት አዉድ ሲታይ ህጋዊ እና ተገቢ መሆኑ ያስማማናል ፡፡

አዚህ ላይ ከምንግስትም ሆነ ከሌሎች  በሚሰጡት ማብራሪያ በብሄራዊ ቋንቋ የዉጭ ቋንቋ (እንግሊዝኛ) መቀላቀል ላልተማረዉ ሠፊዉ ህዝብ ግርታ ወይም መልዕክቱን የመረዳት ብዥታ ያስከትላል ላሉት  ትክክል ከመሆኑም በላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አስበዉበት እና አዉቀዉት ሳይሆን ለጉዳዩ ካላቸዉ በጎ ሀሳብ የተነሳ አፅንኦት ያስገኛል ብሎ ከማሰብ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

እንደ እኔ ይህ የርሳቸዉ ብቻ ነገር ነዉ ብየ አላስብም የሆነዉ ሆኖ የመገናኛ ብዙሃን ምን እየሰሩ እንደሆነ በየዕለቱ ሳንፈልግ እያመመን   የምንሰማቸዉ ጉራማይሌ የቋንቋ ቅልቅል ንግግሮች መኖራቸዉን ማስታወስ ግድ ይላል ፡፡

ዶ/ር ሲሳይ እንዳሉት  ላልተማረዉ ታዳሚ(አድማጭ፣ ተመልካች)  እኔ እንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር፣ መስማት እና መጻፍ የዕዉቀት መጀመሪያም መጨረሻም አይደለም ሊሆንም ሊታሰብም አይችልም  ፡፡ ይህን ዶ/ር ያጡታል ብየ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል  ፡፡ የሆነዉ ሆኖ እኛን ወደ ኋላ ያስቀረን የእኛን ማንነት እና ሁለንተናዊ ምንነት ትተን በሌላ ባዕድ ልሳን እና ማንነት መዘፈቃችን በማህበረሰባችን ሳይቀር የራሱን አጥቃቂ (አጥላይ) የሩቅ ናፋቂ በሆነ አባዜ እና ድንዛዜ  ዉስጥ እንዲሆን ዳርጎታል ፡፡

ዛሬ በታሪክ ከእኛ በኋላ ተወልደዉ ያደጉ  አገሮች እና ህዝቦች እኛን ትተዉ በባህል፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ህይወት መስተጋብር እና በጥበብ ጎዳና የከነዱን የራሳቸዉን ቅርስ እና ዉርስ አጥብቀዉ ከሌላዉ ልምድ እና ተሞክሮ በመዉሰድ እና በመከለስ  ነዉ ፡፡

ከዚህ አኳያ የነበራቸዉን አኩሪ እና ገንቢ ታሪክ እና ማንነት ይዘዉ እና አዳብረዉ የሚጎድለዉን ፈልገዉ በማስማማት ሁለንተናዊ ስልጣኔ እና ዕድገት ያስመዘገቡ አገራት እና ህዝብ ታምር የእኛ የሚሉትን ሰንቀዉ በምግባር እና በተግባር አንድነት ተግተዉ በመስራት  ነዉ ፡፡

እኛ አገር ከዚህ በተቃራኒ የሰራን በመዉቀስ ፣ ያልሰራን  በማወደስ ፤በማንገስ  በከንቱ  ዉዳሴ ተጠምደን  የነበር ስናፈረስ ፣ ድንበር ስንድ ፣ የማይድን(የማይጠገን) ስናድስ  ይኸዉና ጥንትም ዛሬም ታዳጊ ህዝብ እና አገር እንላለን ፡፡

አበዉ ዘመደ ብዙ ጠላዉ ቀጭን ነዉ እንዲሉ ምንጊዜም ተስፈኞች እና ጥገኞች የሚመሩት አገር እና ህዝብ ያለዉን ብቻ ሳይሆን ደሙን እና ወዙን እንደመዥገር ተጣብቀዉ ስለሚመጡት  ለስራ እና ለዕድገት እንዳይነሳ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ቋጥኝ ስለጫኑበት ይህን  ይጥላቻ፣የመከራ ፣ የባርነት እና የድህነት  ቋጥኝ  በራሳቸዉ ላይ ሊገለብጥ ይገባል ፡፡ ምንም ዓይነት ለሰዉ ልጆችም ሆነ ለአገራቸዉ ህዝብ እና ልዑኣላዊነት ስሜት የማይሰጣቸዉ ራስ ወዳዶች እና ስስታሞች ዛሬም እንደትናንቱ ሳይሳሩ  መክበር እና መከበር የሚፈልጉ ህልመኞችን መንግስት እና ህዝብ  አሁን በቃ ……በቃ ሊላቸዉ ይገባል ፡፡

ካልሆነ  የብዙሃን ኢትዮጵያዉያንም  ሆነ  የጠቅላይ ሚ/ር  ሩጫ እና ድካም  ህልም እና ምኞት  ሆኖ እንዳይጠፋ የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተጨባጭ እና በተግባር ስርነቀል ህብር እና ትብብር በመፍጠር  መትጋት የሚጠየቅበት ኢትዮጵያዊነት የሚመዘንበት ብሄራዊ እና ታሪካዊ ወቅት ላይ የምንገኝ መሆኑን ለአፍታ ሳንዘነጋ እና ሳንዘናጋ መንቃት እና  መገንዘብ ይገባል ፡፡

“ኢትዮጵያዊ አይዘናጋም ፤ አያንቀላፋም” !!!

ያሚ ፀጋ

2 Comments

 1. ጥሩ ፕላን ነው ማንም ቅር የሚለው የለም፡፡ እሪሳ አጋድሞ ውሮ ወሸባዬ አለ እንዴ?
  እውነት አሁን ሽር ሸር የሚይስኬድን ወቅቱ ነው? ጠ/ሚሩ ሥራው አገር ማስተዳደር መስሎኝ ለካ ቱሪዝም ኮሚሽን ሆኖ ነው ይሄ ሁሉ ህዝብ በእርሱ አስተዳደር ሲታረድ የሚያላግጥብን፡፡
  የከተማው በወረበላ እየተዝረፈ፣ ክልሌ እያለ ኦንግ እና ቄሮ የስንት ሰላማዊ ህይወት አጥፍቶና አሁንም በየመጠለያ የሚሰቃዩ እያሉ እድሜ ለኢትዮጵያ ነግስታቶቻችን ታሪክን አክብረው ያቆዩትን ቅርስ ፕ/ሚሩ መተረኪያ ጊዜ መውሰዱ አስገርሞኛል፡፡ ያስጎበኘን የአማራ ህዝብን ጨዋነት እና አገርን አስከባሪነት የሚያኮራ ታሪክ ቅርስ ትተው ማለፋቸውን በዛው መጠንም የአማራን የዛሪይቱን ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ላይ ዛሬ ኢትዮጵያ እንድቶሆን ያደረጋት ታላቅ ህዝብ መሆኑን ተገንዝቦ እየተለማመጠነም ይመስላል፡፡
  የሚያዋጣው አማራን አቅፎ የሸዋን ህዝብ ይዞ ኦነግ እና ቂሮን የለመዱት በርሃ አሳዶ ማስወጣት እና ከዛ አገር ማልማቱ ላይ ቢያተኩር ይመረጣል ለራሱም ፕ/ሚር ሆኖ ለመቆየት ህልውና ሲልም የመሪነቱን ሥራ ቢሰራ ይሻላል፡፡ ችግኝ እና ሽርሽር መናፈሻ ማስተዋወቁን ለባለሙያዎቹ ይተውላቸው፡፡ አሁን አገር ሰላም እንደሆነ ባያሰመስል ጥሩ ነው፡፡ ለሁሉም ቦታ እና ጊዜ አለው፡፡

 2. አንዳንዴ መጻፍ ያለብን ለትችትና ችግር ብቻ ለማዉራት ይመስለናል ።ይህ ፈጽሞ ሚዛናዊ እይታን አያመለክትም ።ስለሆነም አንዳንድ ጊዜ እንኳ ጥሩን እያበረታታን ትክክል ያልሆነዉን እንዲስተካከል አቅጣጫ እየጠቆምን ብንሔድ የሚጠቅም ይመስለኛል ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.