የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ የኦህዴድ ብልፅግና ቄሮመር የዘርና የሃይማኖት ሽብር ይቁም!! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

et7የኦህዴድ ብልፅግና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መር የዘርና የሃይማኖት ሽብር በሃገር ውስጥና በባህር  ማዶ ነፃና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን  ይቁም!!! በኢትዮጵያ የሠማዕታቱ ደም በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ ይጣራል ሊደበቅ የማይችለውን የዘርና የሃይማኖት መንግሥት መር ሽብር የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ባየው ዘግናኝ ኢሰብዓዊ የሰዎች ግድያ ድምፁን ከአጥናፍ አጥናፍ በማስተጋባት እንኳን ለጅምላ ጭፍጨፋ ለአንድ ሰው ዘብ ቆመዋል፡፡ በአሜሪካ የጆርጅ ፈሎይድ በፖሊስ አሰቃቂ ግድያ የዓለምን ህዝብ ታሪክ ቀይሮል፣ የቀለም ልዩነት፣ የዘር፣ የብሄር፣ የኃይማኖት ልዩነት የሚደረጉ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ከእንግዲህ በዓለማችን ቦታ የላቸውም፡፡ በሃገራችን ሰው የሚያርዱ፣ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ፣ በድንጋይ ወግረው የሚገሉ፣ በቶርቸር ገርፈው የሚገሉ ጋንግስተሮች ሁሉ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ በሃገር ውስጥና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ተደጋጋሚ የዘርና የኃይማኖት (ጆኖሳይድ) ፍጅት ከፍተኛ ትኩረት በልጆቻ ያላሰለሰ ጥረት ታውቆል ምስጋና ለጵሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የመንፈስ ፅናት ቀጣዩ ትውልድ በ‹‹ህገ-አራዊቶች ዘመን›› ውስጥ በፍፁም አይኖርም፡፡

በሃገር ውስጥ የትብብር እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የቀረበ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን በዶክተር ዳንኤል በቀለ ለመንግሥት በጥቃቱ ሰለባዎች ላይ ቀጣይ ማስፈራሪያ ስላለ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የቀረበ ጥብቅ ማሳሰቢያና ቀጣይ ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባዔ የምርመራ ሪፖርት፣ እንዲሁም  የኢትዮጵያውያን የዘር ፍጅት መከላከል ንቅናቄ በአውሮፓ(Ethiopians Genocide Prevention Movement in Europe) ‹‹በሃገራችን የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ፣በተፈጠረው ክፍተት በመጠቀም፣ በአንዳንድ ጽንፈኛ ሃይሎች፣ እየተደጋገመ እየተፈጸመ ያለው፣ ማንነትን እና እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በእነዚህ ማንነት እና እምነት ተኮር ጥቃቶች፣ዜጎች ከቤት ነበረታቸው ተፈናቅለዋል፣ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት ሰለባ ከሆኑት በተጨማሪ፣ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች፣ውድ ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደረጓል።››ብሎል፡፡ በተመሳሳይ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የተካሄደውን የዘር፣ ሃይማኖት ፍጅትና የአናሳ ብሄር ብሄረሰቦች ጥቃትን  በማውገዝ ባወጡት መግለጫ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ልዩ መረጃዎች መሰረት አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች ንፁሃን ዜጎች ላይ እርምጃ በመውሰድ  ግድያና ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን ገልፀዋል፡፡ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ታዋቂው የኦሮሞ ዘፋኝ ግድያ በኃላ  የተጀመረው ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙንና በዚህም ምክንያት ጥቂት ሰዎችን ፖሊስ በግድያ ወንጀል ጠርጥሮ አስሮል፡፡ እንደ መስክ ሪፖርት ዘገባ መሰረት ክርስትያኖች በጣም አሰቃቂ ጊዜ በኦሮሞ ክልል ውስጥ አሳልፈዋል፡፡በክልሉ ውስጥ የተለያዩ አመለካከት ያላቸው አንጃዎች ይገኛሉ አንዳንዶቹ የብሄር ብሄርተኞች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የሃይማኖት አክራሪዎች ናቸው፡፡ ብዙዋቹ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉትና  የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት አንገታቸው የተሰየፈና ሰውነታቸው የተተለተለ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዬች የሆኑ የአማራ ብሄር ተወላጆች ናቸው፡፡ ሌሎች የጥቃቱ ሰለባዎች ደግሞ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ትራዋይ፣ ጋሞ ብሄሮች እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የመንግስት ኃይል ድርጊቱ በተፈጸመበት ሥፍራ ምንም እንዳልነበር እንዲሁም ግድያው የተፈፀመው በቢላዋችና በሽጉጦች እንደነበር ታውቆል፡፡ ማንም ሰው ሊያስቆማቸው አሊያም  ጣልቃ መግባት  አልተቻለውም፡፡ ከግድው በኃላ የመንግስት ወታደሮች ደርሰው በቦታው እንደሰፈሩ ታውቆል፡፡››

ከባህር ማዶ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የሥራ ባልደረቦች፣ የዓለም አቀፍ  ማዕከላዊ ስትራቴጅ ጥናት፣ ፍሪደም ሃውስ፣ ሂውማን ራይት ዋች፣ ክራይሲሲ ግሩፕ፣ ፖፕ ፍራንሲስ በኢትዮጵያ የጅዋር ቄሮ የሰማንያ ስድስት ሰዎች የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) ጸሎት አድርሰው በየመገናኛው ብዙሃን ሚዲያዎች አድርገው ነበር፡፡ ጆኖሳይድ ዋች የኢትዮጵያን የዘርና ኃይማኖት  ጭፍጨፋ በማጋለጡ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ የፍርድ ቀን ደርሶል! ‹‹የተባበሩት መንግስታት የስብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሮበርት ኮልቪል፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሣ መገደል በኃላ የተፈጠረው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል፡፡  የሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያ በሃገሪቱ ውስጥ ተቃውሞ ቀስቅሶል አንደኛው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሆን ሌላው ነውጠኛ  ነበር፡፡ በኦሮሚያ ክልል አውራ መንገዶች ተዘግተዋል፣ ፎቅ ህንጻዎች ተሰባብረው ተቃጥለዋል፣ የመሣሪ ድምፅ ተስተጋብቶልበአዲስ አበባ ቦንብ ፍንድቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የህዝቡን አመጽ ለመግታት መንግሥት በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ የኢንተርኔት ግንኙነት በመዝጋት  መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖል፡፡ መንግሥት 50 ሰዎች ሞተዋል ሲል ሌሎች ሚዲያዎች የሞች ቁጥርን 80 ሲያደርሱት  ሦስቱ የፖሊስ አባሎች እንደሆኑ ዘግበዋል፡፡ ›› የዘርና የሃይማኖት (ጆኖሳይድ) ፍጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታውቀል፡፡

 

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት   ‹በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች›› አንቀፅ  28 መሠረት  እንዲሁም የክልል ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ሕገ-መንግሥት ላይ የሠፈረው ‹‹በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች›› አንቀፅ  29 መሠረት  ‹‹ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ህጎች ‹‹በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች›› ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅነት ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡ በህግ አውጭው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡›› 1

ያለፈው የሰኔ 22 ቀን 2012 .ም  የእውቁ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በአገራችን በተቀሰቀሰው የዘርና ማጥፋት ወንጀል የንብረት ጉዳት ደርሷል፡፡ ዜጎች በሃይማኖታቸው እና በብሔራቸው ምክንያት ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል፤ ሃብት ንብረታቸውም ወድሟል፡፡ የፍትህ ስርዓቱ ለደረሰው  የሰው ሕይወትና ንብረት ውድመት ተጠያቂ የሆኑትን በዘር ማጥፋት ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ሁሉ በአስቸኮይ ለፍርድ ማቅረብ ሂደቱም በነፃን ገለልተኛ መርማሪ ኮሚሽን በግልፅና ያለአንዳች አድሎ እንዲከናወን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው  በግልጽ ችሎት የመዳኘት ህገ መንግስታዊ መብት እንዲከናወን  ጠይቀዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተደጋገሚ የዜጎችን ዘር እና ሃይማኖት ተገን ተደርጎ ለተፈጠረው የዘር ማጥፋት /ጄኖሳይድ/ እና የስርዓቱ ጋሻ ጃግሬዎች ላደረሱት ወንጀል ሽፋን በመስጠት በሌሎች ንፁሃን ላይ በማላከክ ሕግ እንዳይከበር እና አለመረጋጋቱ ተባብሶ እንዲቀጥል እየተደረገ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሥራ ባልደረባዎች፣ የአለም አቀፍ ማሕብረሰብ ለመረዳት ችለዋል፡፡
“ካንጋሮ ፍርድ ቤት”አቃቤ ሕግ ተከሳሾቹን በፖሊስ ተገደው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ የአቃቤ ሕግ ጥያቄ ተቀብሎ ትእዛዝ ማሳለፉ የዳኝነት ሂደቱ በሕገ መንግስቱና በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌዎች ሳይሆን በፖለቲካ አመራር እየታዘዘ የሚሰራ መሆኑን በገሃድ ለመገንዘብ ችለዋል፡፡  

የፍርድ ሂደቱ አያያዝ ከህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን በከፋ ደረጃ ኦዲፓ ብልፅግና  ፍትሃዊነትን እየተላበሰ ስለመሆኑ፣ ፖሊስ ለመክሰስ የሚያስችለው ምንም ማስረጃ ማቅረብ ሲያቅተው በድብቅ ምስክሮችን ለማቅረብ በማሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን እያለ የፍርድ አሰጣጡን ሂደት ያለበቂ ምክንያት ሲያራዝመው መታየቱ፣ ከጅምሩም ክሱ የሃሰት እንደሆነና  በዚህ አይነት የአምባገነኖችካንጋሮ ፍርድ ቤትፍትህ ማግኘት ስለማይቻል  በሃገር ውስጥ ትግልና የዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖል፡፡ ስለዚህ የአለም አቀፍ ሕብረተሰብ በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ከመጋረጃው ጀርባ ሆነው ያስፈፀሙትን ጭምር ለሕግ እንዲቀርቡ እንዲደረግ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ዜጎች  ጥረት እንዲያግዙ ማድረግ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ በመጨረሻም በአገራችን የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን  በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣የኢትዮጵያ ወዳጆች የሥራ ባልደረባዎች፣ የአለም አቀፍ ማሕብረሰብ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይና ቁርጠኛ ለሆነው ሰላማዊ እና ሕጋዊ ለሆነው የትግል እንቅስቃሴ ከጎኑ በመቆማችሁ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

   ህዝቡ የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) እንደማይደገም ዋስትና አጥቶል!!!

ወንጀለኞቹ ለጊዜው ታስረው እንደተለቀቁ የምርመራ ቡድኖች አጋልጠዋል!!!

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!! የህግ ሉዓላዊነት ይከበር!!!

ምንጭ

{1} https://chilot.me/wp-content/uploads/2012/02/amhara-national-regional-state-constitution.pdf

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.