እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ! መንጋ እንኳን እስክንድርን ክርስቶስን “ስቀለው! ስቀለው!” ብሎ አሰቅሏል!

115887539 10218143647444466 1144185640356231667 nበላይነህ አባተ ([email protected])

በእስክንድር ላይ የሚደርሰውን ዳር ያጣ ግፍ ለማሳየት ክርስቶስ በአስረጂነት ሲነሳ “እስክንድርን እንደ ክርስቶስ ተቆጠረ” ብሎ የሚያሞጠሙት አለሁ ባይ ወለወልዳ፣ የእውቀትና የእምነት ድውይ እንደማይጠፋ መገመት ቀላል ነው፡፡ በክርስቶስ በተሰቀለበት ዘመን የሆነውም ይኸው ነበር፡፡ “የሮማው ንጉስ ተቀመጠው ክርስቶስ አለ አቅሙ ንጉስ ነኝ ብሏል!” የሚል ክርስቶስን ለማጣጣል የሚደረግ ማሽቃበጥ ነበር፡፡

ይህቺ ምድር ያልቻለችው ይህ ሰማይም የማያየው ግፍ የለም፡፡ ምድርና ሰማይ እንደሚመሰክሩት ከሃያ ስምንት ዓመታት በፊት ጀምሮ እስክንድር ህይወቱን ለሕዝብና ለአገሩ ሰጥቶ የኢዮብን መከራ እየተቀበለ ያለ መንፈሰ ጠንካራ ሰው ነው፡፡ ስንቱን ጀሮ እየጠቡ ሲያስገድሉ፣ ሲያስገርፉ፣ ሲያሰልቡና የምከራ ቸነፈር በአገሪቱ ያወረዱት ዛሬም እስክንድርን ወንጅለው የሐሰት ምስክር ሲያቀርቡበት ማየት ህሊና የሚያነፈረቅ ወንጀል ነው፡፡

የይህ አድግ አረመኔዎች ዳግመኛ ከሳሽ፤ እስክንድር ዳግም ተከሳሽ ሆኖ ማየት የፈሪሳውያንን ከሳሽነትና የክርስቶስን ተከሳሽነት የሚያስታውስ ነው፡፡ ለሰላሳ ዓመታት ሕዝብን የጨረገደውና አገርን ቆርሶ የሸጠው የይህ አድጉ ጆሮ ጠቢ አብዮት ከሳሽ፤ ለተጨረገው ሕዝብና ለተቆረሰቺው አገር ያለመታከት የጮኸው እስክንደር ተከሳሽ ሆኖ መመልከት በእርግጥም የፈሪሳውያንን ክስ፣ የይሁዳን ምስክርነትና የክርስቶስን ተከሳሽነት የሚያስታውስ ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በሶቅራጥስ የደረሰው ግፍም የዚሁ ዓይነት ነው፡፡ በሶቅራጥስም ዘመንም ሆነ ክርስቶስ የሰው ሥጋ ለብሶ በምድር በመኖረበት ዘመን የነበረው መንጋ  ተአሁኑ ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው፡፡

ሶቅራጥስ ራሱን ለእውቀት፣ ለእውነትና ለማህበረሰብ ንቃት ገብሮ የኖር ሰው ነበር፡፡ ዳሩ ግን እንደ አረመኔ ይህ አድጎች እውቀትን፣ እውነትንና የማህበረሰብ ንቃትን የማይፈልጉ እርጉሞች ‘አምላኮቻችሁን እየከዳ ነው፣ ወጣቱንም እያበላሸ ነው” ሲሉ ከሰው የሐሰት  ምስክሮች ቀጥረው አስመሰከሩበት፡፡ ሰቆራጥስ የሰራውን በዓይናቸው ተማየት ቀጣፊ ከሳሾቹ በምላሳቸው የተንጣጡትን በጆሯቸው ሰምተው ያመኑ 500 መንጋዎች “ግደለው! ገደለው! ብለው መርዝ አስጨልጠው አስገደሉት፡፡ [1] ሶቅራጥስ ተገድሎ  እነሱ ቆመው አልቀሩም፡፡ ከሳሾቹምን፣ የሐሰት ምስክሮችንም ሆነ ስቀለው ያሉትን  መንጋዎች ምስጥ መጥምጦ ጨርሷቸዋል፡፡ እንደሚታየው የሶቅራጥስ ገድል እስከ ዘላለም ይነሳል! ከሳሾቹና መንጋዎችም እስከ ዳግም ምጣት ሲረገሙ ይኖራሉ፡፡

ሶቅራጥስ ከሞተ 435 ዓመታት በኋላ  የይህ አድግ ዓይነት የሀሰት ክስ፣ የሀሰት ምስክርነት፣ የሀሰት ፍርድና የመንጋ ስቀለው! ስቀለው! ጩኸት  የሰው ሥጋ ለብሶ  ወደ ምድር በመጣው ክርስቶስ  ስቅላቱ ተፈጠመ፡፡[2] ፈሪሳውያን  ክርስቶስን ከሰው በሀሰት አስመስክረው በይሁዳ ጠቋሚነት አሲዘው አሰቀሉት፡፡ ክርስቶስ በሶስተኛው ቀን ተነሳ። የሐሰት ከሳሾችን ፈሪሳውያን፣ የሀሰት ምስክሮችንና ይሁዳን ምስጡ ፎርፉሮ ሰለቀጣቸው፡፡ ነፍሳቸውንም ገሀነብ እንደ ቋያ አቃጠላቸው፡፡ ክርስቶስ ለዘለላም ይመለካል፡፡ የሐሰት ከሳሾች ፈሪሳውያን፣ የሐሰት ምስክሮቻቸውና ይሁዳም ለዘላለም ሲረገሙ ይኖራሉ፡፡

ዛሬ ያለው መንጋም በሶቅራጥስና በክርስቶስ ዘመን የነበረው መንጋ ነው፡፡ ይህ መንጋም ከልጅነቱ ጀምሮ ለፍትህ የታገለውን እስክንደርን ለጪራቆች አሳልፎ ሰጥቶ፣ በሀሰት እየመሰከረ ፍረዱበት እያለ ነው፡፡ ሲጨፈጪፈው፣ ሲገርፈውና ሲያሰድደው ለኖረው አብዮት አመዴ እየሰገደ ሊታገልለት የኖረውን እስክንድርን እየኮነነና አሳልፎ እየሰጠ የሚኖር የአሳማ መንጋ ነው፡፡ ክርስቶስ የከዳ የአሳማ መንጋ እስክንድር ቢከዳ ምን ታምርነት አለው?

እንደ ሶቅራጥስ ሰው ነውና እስክንድር ለእውነትና ለፍትህ ሲታገል ኖሮ ማለፍ አይቀርምና ያልፋል፡፡ እንደ ይሁዳ የከዱት የድሮም ሆነ የአሁኑ ጓደኞችም ክህደታቸውን በቀላማጅ ምላሳቸውና አንደበታቸው እንደ ጎረሱ ያልፋሉ፡፡ ከሳሾቹም እንደ ሰው በላዎች ፈሪሳውያን እንደ ትቢያ ብን ብለው ይጠፋሉ፡፡ የሀሰት ምስክሮችም እንደ ደረቅ እንጨት ይነክታሉ፡፡ እኛ መንጋዎችም  የዘር ማጥፋት ወንጀል ለሚፈጥሙት እያረጠረጥን፣ በሀሰት እየመሰከርን፣ እየከዳንና ለእኛ የሚታገሉትን አሳልፈን ስንሰጥ ኖረን ክንቺር እንላለን፡፡ እነእስክንድር ስማቸው እንደ አለት ተመሬት ተተክሎ ሲመሰገኑ፤ ነፍሳቸው በገነት ስታብብ ይኖራሉ፡፡ እኛም ይኸንን ሰፍሳፋ ስጋችንን ምስጥ እንደ ነቀዘ ብሳና እንክት ሲያደርገውና ነፍሳችንም ሲዖል እንደ ዝልዝል የአሳማ ሥጋ ስትጠብሰው እንኖራለን፡፡

እንኳን ሌላው ከአመታት በፊት የአብዮት የስለላ መረብ እስክንድርን ተጨለማ ቤት ሲያጉረው የእስክንድርን ፎቶ እየሸጡ ገንዘብ የሰበሰቡት ከርሳም ፈሪሳውያንም ዛሬም አብዮት አህመድ እስክንድርን እንደገና ከርቸሌ ሲያሳድረው  በደም የተጨማለቀውን የአብዮትን እግር እየሳሙ እስክንድርን ከድተውታል፡፡ አንዳንዶች እንዲያም እስክንድር ለጲላጦስ ችሎት  ይቅረብልን ሲሉም ጮኸዋል፡፡ ታዲያ ይህ ክፉ ዘመን የሶቅራጥስንና የክርስቶስን የፍዳ ዘመን ታላስታወሰን ምን ሊያስታውሰን ይችላል፡፡

እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ! መንጋ እንኳን እስክንድርን ክርስቶስንም “ስቀለው! ስቀለው!” ብሎ አስቅሏል!

 

 1. The Trial of Socrates: Famous Courts https://www.famous-trials.com/socrates/833-home#:~:text=He%20is%20also%20guilty%20of,of%20thirty%2C%20chosen%20by%20lot.
 2. የሐዋርያት ሥራ 21:36 ሕዝብ አስወግደው አስወግደው እያሉና እይጮኹ ይከተሉት ነበርና

Similar Read: Who Has Been Selflessly Working to Save Ethiopia, Abiyote Ahmed or Eskinder Nega? https://www.amharic.zehabesha.com/who-has-been-selflessly-working-to-save-ethiopia-abiyote-ahmed-or-eskinder-nega/

ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

5 Comments

 1. The judge presiding over the charges against Eskinder Nega & his associates, was heard saying on the telephone “this trial is a waste of time because we already know exactly the verdict we will pass on the defendants”.

 2. ጎበዝ ምነው የሀሳብ ደሀ ሆንንሳ ?፦የእስክንድር መታሰር የኦሩሙማ ምስረታ ፕሮግራም አካል ነው። እስክንድር ይፈታል የሚፈታው ምርጫ ተደርጎ አዲስ አበባ ዳግም በኦሮሞ ነገድ ከንቲባ ላይ ስትወድቅ ነው።ካልሆነም ብርሀኑ ነጋን በመሰሉ የሀገር መውደድ ስሜት በሌላቸው እጅ ስትወድቅ ነው።

  እስክንድር በነጻነት ተለቆ አዲስ አበባ ከእስክንድር ውጭ ይመርጣል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። ስለዚህ የኦሮሙማን እቅድ ክቡር ሽመልስ ለተሰብሳቢዎቻቸው በኩራት ገልጸውታል ነውረኛው ብአዴንም አጠገባቸው ቁጭ ብሎ ኢንዶርስ አድርጎታል።
  በዚህ አጋጣሚ አማራ ክልል የሚኖር ህዝብ በዝምታው የሽመልስና የብአዴን ደጋፊ መሆኑን ማሳሰብ አስፈላጉ ይሆናል ።ዛሬ አማራ ተብሎ ባልታጠረው ክልል አማራው ታይቶ በማይታወቅ ግፍ መከራውን ያያል ነገ ደግሞ እነሱ ላይ የደረሰው መከራ ባለህበት ይዘንብልሀል እስከዛው የነሱ ችግር ያንተ ችግር አይሆንም።

 3. አቶ ሰመረ ይህ ከገባዎት ለማስቆም ምን እያደረጉ ነው? በሰው ጽሒፍ ታች ድንዝዝ ብሎ መናገሩን አስተዋጥው አድርገውት ነው? እስቲ ተገባዎች ምላ ይፍጠሩና ተንኮሊን ያስቀሩት

  እስቲ እያደረጉ ያሉትን ያካፍሉን?

 4. አያሌው ነህ ንጉሱ በጣም ስትጠበብና አእምሮህ የመጨረሻው እንጥፍጣፊውን ጨምቆ የሚያወጣው ጥያቄ መሰለኝ የጠየቅኸኝ። ጥሩ ጥያቄ ነው በሱዳን ድምበር የሱዳንና የግብጽን ጥቃት የሚከላከል በቂ የሆነ ፓትሮይት ሚሳየል አስቀምጫለሁ ወራሪውና ግፈኛው የወያኔና የሻቢያ ጦር ተከዜን አልፎ እንዳይመጣ ዘምናዊ ብረት ለበስ ጦር አስፍሪያለሁ በዚህ መሀል አንተ ክራቫትህን እያስተካከልክ ወግ መጠረቅ ነው። የመለስኩልህ መሰለኝ።
  ሰው በግፍ አለቀ ከግፈኞች አስጥሉት ማለት እንዲህ ካበሳጨህ ምን ይደረጋል ሂድና በተግባር እርዳቸው ይከፍሉሀል።

 5. ሰመረ
  ስምህ አልሰመራም መሆን ነበረበት እኔን ” ክራቫትህን እያስተካከልክ ወግ መጠረቅ ነው” ስትል አንተ ታንክ ላይ ቆመህ እየተዋጋህ ነበር? አስቁሙት እምትል አንተ ቢራህን ጠጥተህ ሽንትህን በወሸላህ እያንደቀደእ ነው?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.