የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲያሰማ ትእዛዝ ሰጠ

Eskinderየፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ ባላቆምነው ተከላካይ ጠበቃ አንወከልም ማለታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲያሰማ ትእዛዝ ሰጠ።
ችሎቱ ከትናንት በስቲያ በነበረው ቀጠሮ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩም ጠበቆቻቸውን ማሰናበታቸውን ተከትሎ የመንግሥት ጠበቃ እንዲመደብላቸው ትእዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ዛሬ ሦስቱም ተጠርጣሪዎች መንግሥት ከመደበላቸው ጠበቆች ጋር ቢገኙም ባልወከልነው ጠበቃ ጉዳያችን ሊታይ አይገባም ብለዋል።
ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ ከትላንት በስቲያ በነበረው ችሎት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ተጠብቆ በመንግሥት ተከላካይ ጠበቃ እንዲወከሉ ቢደረግም ዛሬም ባለመፈለጋቸው የተመደቡት ተከላካይ ጠበቆች ተሰናብተው ጉዳያቸው እንዲታይ ጠይቋል።
ችሎቱም ተጠርጣሪዎቹ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ተጠብቆ ባለፈው ቀጠሮ የመንግሥት ጠበቃ ቢመደብላቸውም ባለመቀበላቸው በራሳቸው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ እና ምስክር የመስማት ሂደቱም ይቀጥል ብሏል።
መስቀለኛ ጥያቄ ካላቸውም የማንሣት መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለትም ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ አግባብ ዐቃቤ ሕግ አራት ምስክሮችን ያቀረበ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።
ከአራቱ ምስክሮች አንደኛው ማንነቱ ሳይታወቅ ቃሉን የሚሰጥ ሲሆን፣ ሦስቱ ደግሞ የምስክርነት ቃላቸውን በዝግ ችሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ ይዞ እንዲቀርብ በማዘዝ ለነሃሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
EBC

1 Comment

  1. “በዝግ ችሎት” means No international diplomat, no journalist … .. Noone present at the hearings except the accused individuals on one side and the Querro ethnic Oromos or PM Abiy Ahmed & Co. on the other side .

    This is proof the justice scale is vertical in Ethiopia . The accused are right in deciding not to be part of this court hearing process because the justice scale is horizontal in this court proceedings, potentially affecting the ongoing genocide victims more.

    “ማንነቱ ሳይታወቅ” Most probably this person’s identity is PM Abiy Ahmed himself.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.