“በአቶ ጃዋር መሐመድ እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ የጉምሩክ ሥርዓትን ሳይከተል ወደ ሀገር የገባ ነው” – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

courtየፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአቶ ጃዋር መሐመድ እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሳይፈፀምበት ወደ ሀገር የገባ መሆኑን አስታወቀ።
የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጉምሩክ ኮሚሽን እና የኮሙኒኬሽን ባለስልጣንን በደብዳቤ በጠየቅኩት መሠረት መሣሪያው ምንም ዓይነት ፈቃድ የሌለው እና ህጋዊ አለመሆኑን ማረጋገጫ ተሠጥቶኛል ማለቱን የዐቃቤ ሕግ መረጃ ያመለክታል ።
ሳተላይቱ የኢትዮ-ቴሌኮም ኔትወርክ ተቋርጦም ከ5 እስከ 25 ኪ.ሜ በሚገኝ ርቀት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ እንደነበርም በባለሙያ ተረጋግጧል ብሏል።
ይህ የሳተላይት መሣሪያ በግለሰቦች እጅ ሊገኝ የማይገባ እና ፈቃድ ያላገኘ መሆኑን ነው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያስታወቀው።
በሌላ በኩል የድምፃዊ ሀጫሉን ሞት ተከትሎ ከተጠርጣሪዎች የተገኙ ዘጠኙም የሬዲዮ መገናኛዎች ከኢትዮ-ቴለኮምም ሆነ ከሌሎች ሥልጣን ካላቸው የመንግሥት ተቋማት ፍቃድ የሌላቸው መሆናቸውንም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጠቁሟል።

2 Comments

  1. የኢትዮጵያ አምላክ የትቢቱን ልክ አይቶ ወደሚገባው ላከው እንጅ ምን ጊዜ ህጋዊ ስራ ሰርቶ ያውቃል? ተው እንጅ አትቀልዱብን አሁን እኮ የምትነግሩን ትንሿን ስህተቱን ትልቅ አድርገን እንድናምን ነው። እንድትታመኑ ክሱ በዘር ሽብር ቅስቀሳ ባስፈጃቸው ኢትዮጵያውያን መሆን አለበት። እነ አዳነች አቤቤም ሆነ ሽመልስ አብዲሳ የሚቀርብልህ ክትፎ ቅቤ አነሰው ወይ አይነት እንክብካቤያቸውን ቢተውት መልካም ነው ጁዋርና በቀለ ለማንኛችሁም አይመለሱም።
    ለነገሩ ጉዳዩ ፍትህን ባገናዘበ መልክ ከታየ ወንጀሉ ከሽመልስና አብይ የሚበልጥ አይደለም

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.