ዶ/ር ዐብይ ለካ መሪ ብቻ ሳይሆኑ መሀንዲስና ጥሩ አስጎብኝም ናቸው!

msgana
ዛሬ ነሀሴ 7/2012 ዓ.ም ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ትልቁ አዳራሽ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዘጋቢ ፊልም ለመመልከት ታድመን ነበር።
በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ሲጀመር ጀምሮ እስከመጨረሻው ድረስ ዋና አስጎብኛችን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነበሩ። በአቀራረባቸው የሚገርም ችሎታና ቀልብን ይዞ መቆየት የሚችል ሀይል ነበራቸው። በዚህም እኒህ ሰው በእርግጥም ለዚች አገር አስደናቂ የሆነ ራዕይና ብሩህ ተስፋ ያላቸው መሪ መሆናቸውን በተግባር አሳይተውናል።
በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ የአራት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የቀረበ ሲሆን እነሱም የአንድነት ፓርክ፣ የኢዮበልዩ ቤተመንግስት፣ የእንጦጦ መዝናኛ ፓርክና የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ናቸው። ስለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ዝርዝር ሁኔታ እዚህ ላይ በቁንጽል ለማቅረብ አልሞክርም። ይልቁንም ነገ ምሽት በቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ጠቁሜ ልለፍ።
ይህም ሆኖ ራዕይ ካለና የይቻላል መንፈስ ከተያዘ ታዕምር መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ አስደናቂ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት እንደሚቻል መመልከታችንን መመስከር ተገቢ ይመስለኛል። በትብብር ከተሰራም ተስፋ ሰጭ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም እንዲሁ።
በዚህም መሠረት የአንድነት ፓርክ (ታላቁ ቤተመንግስት) በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ እንደሚመረቅ የተገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ደግሞ መስከረም አጋማሽ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል። የእንጦጦ ፓርክ አፈጻጸምም በአስገራሚ ሁኔታ እየተጠናቀቀ ነው።
በሚቀጥለው መስከረም ደግሞ ሶስት አዳዲስ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በአማራ ክልሎች ውስጥ ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ታቅዷል። እንዲህ እንዲህ እያሉ በ2014 ዓ.ም በሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እንደሚፈጸሙም ዕቅድ ተይዟል።
በመጨረሻም ባይሆን የምለውን ጠቁሜ ማለፍ ፈለግሁ፣ አንደኛ ዶ/ር አብይ ሁሉንም ፕሮጀክቶች ራሳቸው ከሚያስግበኙን ይልቅ የመግቢያ ሀሳብ አቅርበው ለፕሮጀክት ሀላፊዎች ቢለቁ መልካም ነበር። ሁለተኛ በንግግሮቻቸው መሀል የእንግሊዘኛ ቃላትን ማብዛታቸው ዘጋቢ ፊልሙ በቴሌቪዥን ሲቀርብ ያልተማረውን ሰው ያደናገራል።
ይህም ሆኖ በለውጥና በነውጥ እየተናጠች ያለችን አገር እየመሩ የዚህ አይነት አርአያነት ያለው ስራ አልሞ፣ አቅዶና በአጭር ጊዜ ውስጥ (በአራት ወራት) ተግብሮ አስገራሚ ውጤት ማምጣት በእርግጥም ሰውየው የሆነ ሀይልና ተሰጥዖ እንዳላቸው በግልጽ ያመለክታል።
ዶ/ር ሲሣይ መንግስቴ አዲሱ

5 Comments

 1. ታላቁ ሰዉ ዶ/ር አቢይ አሕመድ እንኳን ኢትዮጵያ አይደለም አለምን መቀየር የሚችል ብቃት ከጥሩ ሰነምግባር ጋር የተቸረዉ ነዉ ።

 2. Dr. Sisay, well, it is the right thing to you to express your admiration to what you saw and what you understood based on your own perception and observation . Yes, you are right it is desirable and admirable to see the story you are telling about but without going into its cynically distorted and hypocritically dramatized characteristics of its real nature .
  What you saw is not something from a genuine and a real sense of political personality . It is rather a politically motivated and idiotically dramatized political game which we have witnessed for a quarter of a century and we continued to do so at this very moment of political tragedy.
  I am sorry to say but I have to say that it is because of persons like you and me who see and perceive things with a very shallow if not stupid way of approach that our country is left with nothing but the horrible story of crisis after after crisis for so many years.
  It is so frustrating to go through your report of painting a golden paint a prime minister who keeps playing a highly orchestrated political game of beautifying the palace yard,, registering his legacy of planting threes and beautifying the city while so many innocent citizens are losing thier precious lives in an extremely inhuman manner .
  It is so disturbing to read your very shallow and highly disgraceful report of admiration of the prime minister who idiotically keeps denying the horrible killings of innocent people based on who they are and what they believe in !
  I am sorry to say but I have to say that It is terribly stupid for you with an academic status of doctorate to go to somehow to the extent of worshiping the guy who did nothing meaningful when millions of innocent citizens have been displaced and exposed to an extremely horrifying situations, and hundreds of them have been killed and mutilated in public .
  It is deeply painful to read your very colorful or rosy perception about the guy (the Pm) who
  was so clever or smart to play as the main character of a highly orchestrated and dramatized political performance .
  It is deeply disgraceful not only to yourself but to those who claim themselves well educated to take or see things at their face values or misleading and misplaced positions and report back to this generation who are tired and disgraced of the very failures of politicians to behave and act with a certain level of rationality and honesty.
  Do’t you really believe that your tour guide (your engineer ) has put innocent engineers such as Yilkal Getnet in prison and terribly violates their basic rights?
  Do’t you have a common sense of seeing things with all their real manifestations , not their fake appearance ?
  Do you have any sense of mindfulness about what the ruling party and government of the Pm is doing to those innocent compatriots such as Eskindir Nega and so many others ?
  Do’t you feel a sense disgracefulness when you tell this story of nothing but dirty political game while you remain silent about so many innocent citizens who have been killed and mutilated by cold -blooded groups oof people who have been supported by officials and security people who belong to the party and government of the guy (the Pm) you are talking about?
  Did you try to see and understand the very true (inside part) of the political personality of the guy when you wrote this rosy report of yours ?
  Didn’t you try to recall and remind your conscience about those innocent citizens who perished in a very shockingly disturbing manner when you wrote this painfully stupid piece of admiration to a person who is very good in articulated rhetoric but not willing and able to stop the evil political behavior and action . Yes, not doing what is right on time and properly but fooling the people that great things are happening is an evil political personality .
  Let me sum up by saying the following .One of the main reasons for finding our country in this very horrible situation is the very repeated and deeply painful failure of the so-called intellectuals or well-educated members of this generation like the one who came up with the above piece of praising or worshiping a politician who grew up and served in a political system that has killed the generation and continued to go with the same if not the worst political game with no any significant sign of change of mind or action .
  I hope with the leadership of genuinely concerned Ethiopians , things will change for the better without paying years and years of sacrifices .

 3. Dr. Sisay good points but the whole idea ,in my view, was about the vision of a leader and no so much about presenting a technical or tourist project. So it was good that he presented it and very eloquently& competently, as you rightly observed. The language, I think was both for the new, current, and old generations, and thus at times mixed with English, which we can all live with.

 4. ዶር ሲሣይ፣ ይቅርታ ዶር አቢይ አስጎብኚነት ያወርዳቸዋል። ባይሆን እጅግ ረቀቅ ያለ ክህሎት ያላቸው አስተዋይ፣ ርህሩህና ባለ ራእይ መሪ ናቸው። ለዚህ ስራቸው ደግሞ ወደፊት ታሪክ ይዘክራቸው ይሆናል። ይመልከቱ T Goshu የሚሉት የዲጂታል መናፍስት ጣቢያ ሲቀላቅል። አስጎብኚ የሚባሉት የጎሹ የመቀሌ ግዞተኞች አይነቶች ናቸው – ሊያውም ከታደሉት ነው ታድያ!

 5. አሳዛኝና አስተዛዛቢ የውዳሴ ከንቱ ድርሰት ነው። ሰውዬው አደርጋለሁ ብሎ ከሚደሰኩረው ሌላ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ያለፈውን 2ዓመት ትርጉም ያለው ስራ አልሠራም ።በተለይ አሁ ጊዜን እየጠበቁ አሳሳች ፊልሞችና ገለፃዎች መስጠት ለሕዝባችን ፋይዳ የለውም።
  የፍጅት ወንጀል የተፈፀመባቸውን ወገኖቻችንን እንደማፅናናት ፣የራሱ ፓርቲ አባላት ጨምሮ ለሚያደርጉት የጭፍጨፋ አነሳሽነት ለፍርድ መቅረብ ሲገባቸው ፣የተጎዱትን ከይቅርታ በላይ መቋቋሚያቸውን እንደማዘጋጀት፣የፈረደበትን አምሐራ ለመደለል ከበድኖቹ የአማራ ክልል አጋሮቹ ጋር ተልክ መትከል እንደትልቅ ሞያ ይወራለታል። አሁን አንገብጋቢ ጉዳዮችን አልተገነዘበም አይፈልግምም።
  ሕዝብን ለማደናገር የሚደረጉ ብልጭልጮች ጊዜያዊ መሆኑን ሕዝቡ ተገንዝቦታል። አዲስ አበባን ዋጋ ቢስ እናደርጋለን ብሎ ሽመልስ እንደዛተው ሰውዬው የምኒልክን ቤተመንግሥት ደብዛውን ለማጥፋት የ unity park ቢለውም የታሪክ ድምሰሳ አንደኛው ወገን ነው። የፅንፈኞች ድድብና ዘለዓለማዊ የሚሆኑ ስለሚመስላቸው ነው።በቅርቡ ታሪካችን እንኳ የህወሓት ን በምን ያህል ያሁኑ ተረኞች እያፈረሱ እንደሆነ እያየን ነው። የኦሮሞ ፅንፈኞችም በጊዜአቸው አይቀርላቸውም። ያውም በፈጠነ ጊዜ።
  አባ ዊርቱ አጎብዳጅ ለመሆኑ ከዚህ በፊት በረዥምና በአጫጭር ፅሁፎቹ አስመስክሯል ። የሚገርመው ግን የዶክተሩ ፅሁፍ ነው። መማር ጥቅሙ ነገርን ለማስተዋልና አገናዝቦ ሐሳብ ለማመንጨት ነበር።ለነገሩማ ድንጋይ ባህር ቢዘፈቅ ዋና ይችላል ማለት አይደለም። በአብይ ዘመን ብዙ አሳፋሪ አጨብጫቢ ምሁር ነን ባዮች መከሰታቸው አያስገርምም። አሳ መግማት የሚጀምረው ከራሱ ነው ብለዋል አበው።
  የጀርመን ናዚዎች የሺ አመት የግዛት ዘመን ያለሙትን በ13 ዓመት ተቀጭቷ ል።እንዲያው ለማስታወስ ያህል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.