በኦሮምያ በቅርቡ ስለተከሰተው የኅይማኖትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ – ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ ዕርቁ ይመር

EthiopiawinetAugust 12, 2020

ለዶ/ር አቢይ አህመድ
የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽና ፓርቲ ሊቀመንበር
ለፖለቲካ ፓርቲዎች
ለሲቪክ ማኅበራት
ለእምነት ተቋማት
ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ

በያሉበት፣

ከድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ፣ አዲስ አበባን ድሬዳዋንና ሐረርን ሳይጨምር፣ በኦሮሚያ ክልል ብቻ የዘጠኝ ወር እርጉዝና ሕፃናት ሳይቀሩ ከ239 ዜጎች በላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡በተጨማሪም፣ 523 የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ 195 ሆቴሎች፣ 232 የንግድ ቤቶች፣ 8 የተለያዩ ፋብሪካዎች 273 የግል፤ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች ወድመዋል።በምዕራብ አርሲ ብቻ 19 ምዕመናን ተገድለዋል 3362 በየቤተክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ 934 ድርጅቶች/ሱቅ፣ ሬስቶራንት፣ሆቴል፣ት/ቤት/

ወድመዋል, 493 መኖርያ ቤቶች፤ 72 ተሽከርካሪዎች ወድመዋል 1 ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል። https://twitter.com/i/status/1281958254881370113 ከላይ የተጠቀሱት አሀዞች የመጨረሻ ላይሆኑ ይችላሉ። አሰቃቂው ጉዳት ለደረስባቸው ቤተስቦችና ዘመድ አዝማዳት፤ ጓደኞችና ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን፡

ይህ በሃጫሉ ሞት ምክንያት ወጣቱ በግብታዊነት ብቻ የፈፀመው ሳይሆን፣ ያንን ሰበብ አርጎ በተለይ “ሃይማኖት ላይ ያተኮረ” ፍጅት ለማድረግ ቀደም ተብሎ የተቀነባብረ ነበረ የሚያሰኙ መረጃዎችን እንመልከት፣

1) ጥቃቱ ባለፈው ጥቅምት ወር በአርሲ፣ ባሌና ሐረርጌ ደርሰው ከነበሩት ሃይማኖትንና ቋንቋን መሠረት ካደረጉት ጭፍጨፋዎች ጋር በቦታውና በወንጀሎች አይነት ተደጋጋምም

መሆኑ፣ ለዚያ ጊዜ ቢያንስ የ87 ዜጎች ጭፍጨፋዎችና የንብረቶች ውድመት መንግሥት ለሕግ ያቀረባቸው አለመኖራቸው፣

2) የንፁሃን ዜጎች ግድያ፣ ዘረፋ፣ ቤት ንብረት ማውደሙ፣ ወዘተ፣ በብዙ ቦታዎች ሃጫሉ በሞተ በሰአታት ውስጥ በመቶዎችና በሺህ በሚቆጠሩ የተደራጁ የየአካበቢው የወጣት ቡድኖች መሆኑ፣

3) እነዚህ ቡድኖች ከገጠር ቀበሌዎች ወደየከተሞቹ በተዘጋጁላቸው ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀሳቸው፣

4) ሊጠቁ የተዘጋጁ የዜጎች የስም ዝርዝርና አድራሻዎች እየተነበቡ መገደላቸው፣ ንብረታቸው መዘረፉ፣

5) ከሞላ ጎደል ተጠቂዎች የክርስትናን፣ በተለይም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችና “መጤ” ተብለው የተለዩ፣ የሸዋ ኦሮሞዎችን ጨምሮ፣ አማርኛ፣ ጉራግኛ፣ ጋሞኛ፣ ወላይትኛ የሚናገሩ ላይ ያነጣጠረ መሆኑ፣

6) ከጥቃቱ በህዋላ “የአካባቢው ሰዎች” ናቸው ተብለው ለተለዩት ነዋሪዎች “መጤዎችን”

እንዳይቀርቡ፣ እርዳታ ግብይትና እንዳያደርጉ፣ መጤዎች ወደውም ተገደውም “ወደየሀገራቸው” እንዲሄዱ የሚገልፅ በኦሮምኛ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት መበተኑና የመሳሰሉት ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህሊና ጥሪ ለሰብአዊነት አስቸኳይ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በፍራንክፈርት  

7) ይህ አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት በይዘትም ሆነ በቅርፅ ሃይማኖትንና የብሔር ማንነትን መሠረት ያደረገ ፍጅት (ጄኖሳይድ) ውጭ ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም። ወደድንም ጠላንም የአለምን የጄኖሳይድ መመዘኛዎችን ያሟላ መቅሰፍት ነው።

ሀዘናችንን እጅግ ከባድ የሚያደርገው ያ ሁሉ መዓት በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ ሲወርድ በስፍራው የነበሩት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና የየአካባቢ የወረዳ፣ የዞንና የክልል አመራሮች እልቂቱንና የንብረት ውድመቱን ለማስቆም ፈቃደኛ ያልነበሩ መሆናቸው ነው። ከእልቂቱም በሁዋላ በሕይወት ለተረፉት ዜጎች ያደረጉት ርዳታና ትብብር አልነበረም ። ጥቂት ማስረጃዎች እንጥቀስ፣

1) ጥቃቶቹ ሲጀመሩ ጀምሮ ዜጎች ለየአካባቢው የፀጥታ አመራሮች፣ ለከተማ ከንቲባዎችና ኃላፊዎች የነፍስ አድን ጥያቄና ልመና ሲያቀርቡ ነበር። ከሞላ ጎደል በሁሉም ከተሞችና አካባቢዎች አግኝተው የነበሩት መልሶች- “አልታዘዝንም”፣ “ምንም ማድረግ አንችልም”፣

“አያገባንም”፣ ወዘተ ነበር። የፌደራል ፖሊስ እርምጃ መውሰድ እስከጀመረ ድረስ የክልል የፀጥታ ኃይሎች እዚህ ግባ በሚባል የሕግ ማስከበር እርምጃዎች አልተሳተፉም። ለተጠቂው የሕዝብ ክፍል የድረሱልኝ ጥሪ መልስ አለመስጠት፣ ቢያንስ ግዴለሽነት ነው፣ አልያም ተባባሪነት ነው።

2) በሻሸመኔ በአንድ ወቅት የአካባቢው የመከላከያ አንድ ዕዝ ጣልቃ ሊገባ አለቃውን ፈቃድ ጠይቆ ያገኘው መልስ ” አርፈህ ተቀመጥ” ተብሎ የነበር መሆኑ ተዘግቧል።

3) በሕይወት ተርፈው በየቤተክርስቲያናቱ የተጠለሉት ዜጎች የሚደርስባቸውን”ለቅቃችሁ ውጡ”፣ እንገላችህዋለን” እየተባሉ በወንጀለኞች ማስፈራሪያዎች ሲቀርብባቸው ይሰጣቸው የነበሩት መልሶች “ሲመጡ ጥሩን”፣ በቂ ኃይል የለንም ወዘተ ነበር።

4) እስከ አለፈው ሁለት ሳምንት ድረስ ማንም የክልል ባለሥልጣን ስለተደረገው ፍጅት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል ወጥቶ በግልፅ የኮነነ አልነበረም።

ወንጀሉ በሕግ እንዲታይ ተጠርጣሪዎች ተይዘው የምርመራና የፍርድ ሂደቱ መጀመሩና ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ባለስልጣናት ከስራቸው መታገድ መጀመራቸው መልካም ቢሆንም፣ አሁንም በማወቅም ሆነ ባለማውቅ ከአንዳንድ የክልሉ ባለሥልጣናት የተከላካይነት ማስተባበያዎችና ማስፈራሪያዎች ሲናገሩ ይሰማል።

በቅርቡ ለጋዜጠኞች ከተነገረው አንዱ “ጉዳዩን ከሃይማኖትና ብሔር ጋር የምታያይዙ

ተጠንቀቁ” የሚለው መልዕክት ነው። የሃይማኖት ወይም የብሔር የፅንፈኝነት ድርጊቶች በብዙ አገሮች ታይተዋል። ፅንፈኝነት የቡድን ወይም የተደራጁ ኃይሎች ሥራ እንጂ እንወክለዋለን የሚሉት ሃይማኖት ወይም ሕዝብ አይደለም። ፅንፈኞች አደጋውን አደረሱ ማለት የኦሮሞ ሕዝብ ገደለ፣ ብሔር ለይቶ አጠቃ ማለት አይደለም። የኦሮሞም ሆነ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዱ በጋራ የሚገለፅበት ባህሪው የአብሮነት ባህሉ ነው። አደጋው በደረሰባቸው አካባቢ ያለው ሰፊው የኦሮሞ ማህበረሰባችን በሺህ የሚቆጠሩትን ከሞት አድኗል። በተቻለው ሁሉ የምግብና፣ የመጠለያ እርዳታዎች አቅርቧል። ሀዘኑንና ቁጣውን ገልጧል ። ማንነቱን በተግባር አሳይቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት ጠገዴ ዳንሻህ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ጦር ጥቃት እየተሰነዘረበት የዘር ማጥራት እየተካሄደበት ነው

https://www.youtube.com/watch?v=L4apOHpcE&feature=youtu.be!

ዜጎች በማንነታቸው ግፍ ተፈፅሞባቸው እያለ “የተደረጉት ያልተገቡ ድርጊቶች ናቸው ” ወይም “የሆነው ግጭት ነገር ነው ” በሚል አሳንሶ ማቅረብና እውቅና መንፈግ ለአጥቂዎቹ ሽፋን እንደመስጠት ሊያስቆጠር ይችላል። የየትኛውም እርከን የመንግስት ኃላፊዎች

ክእንደዚህ አይነት አነጋገሮች መታቀብ አለባቸው። መሰመር ያለበት ሰሞኑን በአርሲ፣ በባሌና ሐረርጌ የደረሱት ሃይማኖትና ዘር ተኮር ዘግናኝ ግድያዎችና የንብረት ውድመቶች በጥቅምት ወር በነዚሁ ቦታዎች ከደረሱት ሃይማኖታዊና ብሔር ተኮር ግድያዎች ጋር በይዘትና በቅርፅ አንድ መሆናቸው ነው።

መንግስት ያለበትን ውስጣዊ፤ እካባቢያዊና ስትራቴጅያዊ እንቅፋቶች ብዙ እንደሆኑ እንገነዘባለን። መፍትሄው ሁሉ ከመንግሥት ይመጣል የሚል ግንዛቤም የለንም ፡፡ ይህ ዓይነቱ ጥቃት እንደገና እንዳይከሰት የሚከተሉት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ብለን እናምናለን፡

1. በወንጀለኞቹና በአስተባባሪዎቹ ላይ እስር ቤት ማጎር ብቻ ሳይሆን ሕጋዊ ፈጣንና የተሟላ ፍትሐዊ እርምጃ መውሰድ፣

2. የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል የተከሰተው የሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ሃላፊነታቸውን ባለመወጣቸው በመሆኑ፤ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣

3. የተፈጸሙት ወንጀሎች የጄኖሳይድ ጠባዮችን የያዙ ስለሆነ የፍርዱ ክስ አመሰራረት ወደ ዘር ማጥፋት ደረጃ ከፍ እንዲል ማድረግ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዐዊ መብት ጥበቃ በኩል እንዲጣራ ማመቻቸት፣

4. በሕይወት የተረፉት አሁንም ካልተያዙ ወንጀለኞችና ተባባሪዎቻቸው ዛቻና ማስፈራርያዎች እየደረሳቸው እንደሆነ ይወተውታሉ። መንግሥት በቂ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው፣

5. አቅሙ ያለው ሰው የራሱን መከላከያ መሳርያ በህጋዊ መንገድ ገዝቶ እንዲታጠቅ ህገ መንግስታዊ መብቱን ማክበር፣

6. ሕዝብ ራሱን የሚከላከልበት አደረጃጀት እንዲኖረው ማድረግ፤ ከመንግስት የፀጥታ አካላት የሚቀናጅ ፣ አካባቢን የመከላከል አደረጃጀት ማስቻል፣ ለዚህም አስፈላጊውን ትጥቅ ማሟላት፣

7. ለጥፋቶች ሁሉ መነሻ ባለፉት 45 አመታት የተራገቡት ሚዛናቸውን የሳቱ ትርክቶች መሆናቸውንና ወጣቶች የዚህ የተዛባ ትርክትና አሻጥር ሰለባዎች መሆናቸውን

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከእናቴ ጋር ቀጠሮ (አዲሱ ደረጀ)

ተገንዝቦ በተለይ ወጣቶች ላይ ያተኮረ በኢትዮጵያውነትና ዜግነት ላይ ቅስቀሳዎችና

ትምህርቶች ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ሥርዓተ ትምህርቱ ከሥሩ መከለስ ይኖርበታል። ከመንግስት በተጨማሪ የሲቪክና የሃይማኖት፣ ድርጅቶች የሙያ ድርጅቶችና የመሳሰሉት በዚህ ጥረት መሳተፋቸው ሀገርን ይጠቅማል። በኛ በኩል በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ያሉንን የሰውና የማቴርያል ኃይሎች ሁሉ ተጠቅመን ለማገዝ ዝግጁ ነን።

እንደዚሁም አሁን ሀገሪቱ የምትደዳርበት በዘርና በቋንቋ የተዋቀረው የክልል አስተዳደር ሕዝባችንን በማያባራ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንደሚከት የታወቀና በተግባር እያየነው ነው፡፡ አሠራሩ በየትኛው ዓለም የማይታይ የአስተዳደር ዘዴ ሲሆን እኛም ከዚህ የጥቂት ጠባቦች ክልላዊ የሥልጣን ጥማት ማርኪይ ዘዴ ተላቀን ዘርና ቋንቋ ሳንለይ በጋራና በእኩልነት የምንገለገልበት ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱ አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው ብለን እናምናለን፡፡

8. ድርጅታችን ይህንን መግለጫ አዘጋጅቶ ለመንግሥትና ለሕዝብ ለማሳወቅ በዝግጅት ላይ እያለ፤ በኦሮምያ ክልል አስተዳደር በኩል ከወራት በፊት በተክናወነ ስብሰባ “አንዱን ጠቅሞ ሌሎች ወገኖችን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚያስችል” ሀገር አፍራሽ ስትራቴጂ አለ ተብሎ ተነግሯል። በመረጃው መሠረትም በድብቅ የጥፋት ፖሊሲ ቀርጾ በሌሎች ወገኖች ላይ የበላይነትን ለማስፈን ሲንቀሳቀሱ እንደነበረና ለወደፊቱም በዚሁ መልክ አጠንክረው እንደሚቀጥሉ በዝርዝር ተነግሮአል። የጥፋቱ ስፋትና ጥልቀት እንደዚሁም የአስፈጻሚዎቹ ማንነት በሚገባና በዝርዝር መታወቅ እንዳለበት እናምናለን፡፡ በተለይም ሀገራችን አሁን ባለችበት የደህንነት ይዞታ አንጻር ችግሩ በገለልተኛ ዜጎች ተመርምሮ ለሕዝባችን ይፋ ከሆነ በኋል የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አመክረን እናሳስባለን፡፡

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆችዋ ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

ዕርቁ ይመር

ሊቀመንበር

An international and independent rights-based civic movement @Ethiopiawinnet;
ethiopiawinnet@gmail.com

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.