ሲዳማና ዎላይታ ህዝበ ውሳኔ ለጠየቁ ጥይት! ነፃነት ለጠየቁ ባርነት! ሪፈረንደም ጠያቂ ማነህ ባለተራ? – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ET22ኢቫን ፓቭሎቭ   የህያው ፍጡራንን አካላት ትክክለኛ ሥራ የሚያጠና የራሽያ ተመራማሪ ነበር (ፊዚዮሎጂስት)፣ፓቭሎቭ እንሰሳትን በተደጋጋሚ የማስለመድ ጥናት አድርጎል፡፡ ጥናቱን በቀላሉ ለማስረዳት ከሥዕሉ (1) ውሻው ምግብ ከመመገቡ  በፊት ሲጎመዥ ምራቁ ወይም ለሃጩ እንደሚዝረበረብ፣ (2) ደውሉ ሲደወል ምግብ አልቀረበም፣ ውሻው ምንም ምራቅ ወይም ለሃጭ  ምልክት አላሳየም፣ (3) ደውሉ ሲደወልና  ምግብ ሲቀርብ የውሻው ምራቅና ልሃጭ እንደሚዝረከረክ ይስተዋላል፣ (4) ደውሉ ሲደወል ምግብ ሳይቀርብ፣   የውሻው ምራቅና ልሃጭ እንደሚዝረከረክ በልምምዱ ተደጋጋሚ ሁኔታ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ በልምምዱ ወቅት ውሻው ደውሉ ሲደወል ምግብ እንደመጣለት  በመቁጠር ልሃጩ ይዝረበረባል፣ የፓቭሎቭ ተለምዶዊ ቅፅበታዊ ምላሽ (Pavlovian conditioning)፣ለውሻ ምግብና ደውል በመስጠት (ፓቭሎቭያን የማለማመድ ሁኔታ) ተብሎ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሚያደርገው ፓቭሎቭያን ፖለቲካ (Pavlovian Politics) በቀላሉ ለመረዳት በህወሓት ኢህአዴግ ዘመንና ኦዲፓ ብልፅግና  ምርጫ ይሉህና ጥይት! (ጁዋር መሃመድ ‹‹በምርጫ ወይም በሜንጫ›› እናሸንፋለን!!! “The Ballot or the Bullet”) ነጻነት ይሉህና ባርነት!!! ፍርዱ ይሉህና ውሳኔ!!!  ምግብ ሳይሰጡህ  ደውል!  ሲዳማና ዎላይታ ህዝበ ውሳኔ ለጠየቁ ጥይት! ነፃነት ለጠየቁ ባርነት! ሪፈረንደም ጠያቂ ማነህ ባለተራ? ሕገ-መንግሥት ይሉህና ሕገ-አራዊት መሆኑን ህዝቡ ይሄን በማወቅ የፖለቲካ ሴራውን መረዳት ይጠቅማል እንላለን፡፡ “Classical conditioning (also known as Pavlovian conditioning) is learning through association and was discovered by Pavlov, a Russian physiologist. In simple terms, two stimuli are linked together to produce a new learned response in a person or animal. …During the 1890s, Russian physiologist, Ivan Pavlov was researching salivation in dogs in response to being fed. He inserted a small test tube into the cheek of each dog to measure saliva when the dogs were fed (with a powder made from meat). …Pavlov found that for associations to be made, the two stimuli had to be presented close together in time (such as a bell). He called this the law of temporal contiguity. If the time between the conditioned stimulus (bell) and unconditioned stimulus (food) is too great, then learning will not occur. Pavlov and his studies of classical conditioning have become famous since his early work between 1890-1930. Classical conditioning is “classical” in that it is the first systematic study of basic laws of learning / conditioning.”(https://www.simplypsychology.org/pavlov.html)

በዝናብ ወቅት መጀመሪያ የመብረቁ ብርሃን በሰማየ ሰማያቱ ላይ ይታያል፡፡ ቀጥሎም የመብረቁ ነጎድጎድ ድምፅ ጩኽት ከአጥናፍ አጥናፍ ያስተጋባል፡፡ ብርሃን መጀመሪያ፣ ድምፅ ለጥቆ  ይመጣል፣በተፈጥሮ ሳይንስ የብርሃን ፍጥነት ከድምፅ ፍጥነት ይፈጥናል የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ብልፅግና/ኢህአዴግ  ዶክተር አብይ አህመድ መጋቢት አሥር ቀን 2010 ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ሁለት ሽህ አምስት መቶ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ስድሳ በመቶ የሃገሪቱ ዜጎች በመከላከያ ሠራዊት ኃይል ኮማንድ ፖስት ተጠርንፎና በኮሮናቨይረስ አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ቀሪዋ ነፃነቱን ተለጎሞ ይገኛል፡፡

  • ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ እየገቡ የባህር ዳር የሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ/ም ግድያ ቀድመው ‹‹የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው!!!›› በማለት በብህሃን ፍጥነት ህግ ጣሱ፡፡ በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም የኦሮሚያ የዘርና ኃይማኖት ፍጂት (ጆኖሳይድ) ተቃዋሚ ወገን ሲል ጠቅላዬ  ‹‹ግጭት ነው!!!›› በማለት እንደ መብረቁ ብርሃናቸውን ቀድመው በመፈንጠቅ የህግ ሉዓላዊነትን ጣሱ፡፡
  • በወርሃ ጥቅምት 2012ዓ/ም:- በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በጀዋር መሃመድ የተከብቤለሁ ድረሱልኝ ጥሪ ምክንያት በደሬዳዋ፣ ሀረርጌና ዶዶላ ከተሞች የሚገኙ ፅንፈኛ ቄሮዎች የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዶክተር አብይ መንግሥት አስታውቆል፡፡ ሜንጫ መር ቄሮዎች ብዙ ንብረቶች አውድመዋል፣ 25 ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ 100 የኃይማኖት አባቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ከመቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የዘር ፍጅቱ ያተኮረው በአመዛኙ በአማርኛ ተናጋሪዎች፣ አማሮች ከክልላችን ውጡልን በሚል ምክንያታዊ ዘረፋ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ በሌላ በኩልም በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች በተለይም ለአማራ ያደሩ በሚል ተገድለዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች  የዘርና ኃይማኖት ፍጂት (ጆኖሳይድ)ሲል ጠቅላዩ ደግሞ  ‹‹ግጭት ነው!!!›› በማለት እንደ መብረቁ ብርሃናቸውን ቀድመው በመፈንጠቅ የህግ ሉዓላዊነትን ጣሱ፡፡
  • ሰኔ 23 ቀን 2012ዓ/ም፡- ‹‹የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮሚሽነር ግርማ ገላን መግለጫ መሠረት ‹‹በርካታ ኦሮሚያ ዞኖች በአርሲ፣ በጅማ ብሔር ተኮር ጥቃቶች ተፈጸመዋል፡፡ ከዛም አልፎ በአርሲ አካባቢ ላይ የተፈፀሙት የግድያ ወንጀሎች የሃይማኖት አዘል ንቅናቄዎች ነበሩ፡፡ በሃይማኖት ክርስቲያን እምነት ተከታዬች ኦሮሞ ሆነው የሞቱ በተለይ ምስራቅ አርሲ ሠላሳ አምስት ሰዎች ነው የሞቱት ከዚህ ውስጥ ሃያ ሁለቱ የሸዋ ኦሮሞ ተወላጆች ናቸው፡፡ ክርስቲያን በመሆናቸው የተገደሉ፡፡ አስራሦስቱ የአማራ፣ ደቡብ ክልል ተወላጆች መሆናቸው አረጋግጠናል፡፡››  https://www.youtube.com/watch?v=Cc9jO7RxdVs/ Ethiopia -ESAT ኢሳት ልዩ ዜና Thursday 16 July 2020/58,272 views/•Jul 16, 2020/ የህወሓት፣የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ አልቀረቡም!!!  የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማጋለጡ መንፈቅ ሳይሞላው በወያኔ፣ በኦነግ፣ በኦነግ ሸኔ፣ በኦፌኮ የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የሠላሣ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  መኖር አለበት እንላለን፡፡
  • ዶክተር አብይ አህመድ ድምፃቸውን ባጠፉ በወሩ ‹‹በቅረቡ በኦሮሚያ ክልል ለመናገር በሚያሳፍር መልኩ በርካታ ዜጎቻችን ሞተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት ይህን ተከትሎ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አብራርተዋል። በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጠር ስር ውለዋል ብለዋል። ትናንት የተጸየፍነውን በደል ዛሬ ላይ የምንደግመው ከሆነ ከግጭት አዙሪት ልንወጣ አንችልም ሲሉም ነው የተናገሩት። ግጭቱን የብሔር መልክ እንዳለው አድርጎ የሚያራግቡ አካላት እንዳሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በግጭቱ በርካታ ኦሮሞዎች መሞታቸውን በአስረጂነት አንስተው፤ “ዋናው ነገር ግጭት ከተከሰተ መጀመሪያ የሚያጠቃው እኔን ነው የሚለውን መገንዘብ ያስፈልጋል” ብለዋል። ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትወከል ሳይሆን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ሀገር መሆኗንም ነው የገለጹት። ከዚህ አንጻር ጥቂት ሰዎች ሲያጠፉ ማህበረሰብን ጠቅልሎ መውቀስ አይገባም ሲሉም አብራርተዋል።››2 ጠቅላይ ሚንስትሩ የህግ አውጭ፣ ሕግ ተርጎሚና፣ ሕግ አስፈፃሚ ሥራ በመንጠቅ፣ የአንባገነናዊ ጣልቃ ገብነት ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ የማፍያ ስርዓት ከህወሓት ኢህአዴግ ፓርቲ እስከ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ቀጥሎል እንላለን፡፡ ስለዚህ ለጠቅላይ ሚንስትሩም ሆነ ለተቃዋሚዎችም የማይወግኑ ‹‹ነፃና ገለልተኛ መርማሪ ኮሚሽን›› በማቆቆም የህግ ሉዓላዊነት እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለአራት አማሮች

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥትነት ጥያቄ 69 ሰዎች ሞቱ፣

በደቡብ ክልል ሃምሳ ስድስት ብሄር ብሄረሰቦች አንዳሉና ከዚህ ውስጥ አስራ ሁለቱ የማንነት ጥያቄ በማቅረብ የክልል መንግሥት ለመሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት በዘጠና ዘጠኝ በመቶ ድምጽ ድጋፍ እንዳገኘ መረጃው ያሳያል ለሪፈረንደሙን ለማስፈጸም 750 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖል፡፡ከዚህ በመረዳት  ለወላይታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ፣ ከንባታ፣ ጌዲዬ፣ ጎፋ፣ ወዘተ ቤሳቢስቲን ገንዘብ ወጪ ማውጣት ሃገሪቱ አያሻትም እንላለን፡፡ “2020 marks the 18th year of the Loqqee massacre of the Sidama civilians. On 24 May 2002 over 10,000 Sidama civilians including elders, business persons, civil servants and students staged a peaceful rally in a place called Loqqee in the outskirt of the Sidama capital Hawassa, demanding self-rule and opposing a proposal to move the capital of Sidama from their land of Hawassa to a district town. Although the rally was led by the Sidama elders and was entirely peaceful, the brutal EPRDF-TPLF regime ordered its special military forces known as Agiazi and special police to massacre the civilians indiscriminately. The security forces used live bullets instantly killing at least 69 confirmed civilians including a 10 years old boy on 24 May 2002. Additionally, over 200 civilians were also wounded most of whom have endured permanent disability. Some of the dead bodies were left to be devoured by wild animals in the night of the massacre simply because the Sidama people were not allowed to collect the bodies their loved ones as strict curfew was imposed following the massacre. The EPRDF-TPLF dictatorship was never satisfied with the killings. Therefore, it has also jailed about 2000 innocent Sidama civilians following the indicated massacre.” (https://ayyaantuu.org/english/sidama-nation-commemorates-18th-anniversary-of-loqqee-massacre/The Sidama Nation Is Globally To Commemorate The 18th Anniversary Of The Loqqee Massacre Of Sidama Civilians.)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህውኃት- ዛሬም በጉልበት፤ ኦህዴድ በአስቸጋሪ-መንገድ፣ ብአዴን -በድን ፣ ይገረም አለሙ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ 750 ሚሊዩን ብር ወጪ ማስፈፀሙና በቀጣይ የተገኘው ትምህርት ምንድነው ለወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሃድያ፣ 56 ብሄር ብሄረሰቦች ክልላዊ መንግሥት የመሆን ጥያቄ በቡዙ ቢሊዩን ብር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ህዝበ- ውሳኔውን ፎቶግራፍ፣ ፊርማና ስልክ ወዘተ  ያለው ማመልከቻ በማሰባሰብ (PETITION) ከማድረግ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆኑ መፍቀድ፡፡  የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ጎጆ ለሚወጡት መንግስቶች ገንዘቡን ለዶሮ ርቢ፣ ለመስኖ ሥራ፣ ለከብት እርባታ በአጠቃላይ በምግብ ራስን መቻል ፕሮግራም ቢውል የተሸለ ይሆናል እንላለን፡፡ የትምህርት ዋጋው አዙሮ ማየትና የወደፊቱን መተንበይ ብቻ ነው፡፡ ህዝብን እንደ ኤርትራ ህዝበ ውሳኔ (ሪፍራንደም) ‹‹ከነፃነትና ከባርነት›› ሲዳማ ህዝብም ከሁለት ሦስት ጊዜ የህወኃት ጭፍጨፋ በኃላ 98 በመቶ ህዝብ ድምፁን ሲዳማ ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን መወሰኑን ሰምተናል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ  56 ብሄር ብሄረሰቦች ለወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሃድያ፣ ወዘተ ክልላዊ መንግሥት የመሆን ጥያቄ በትንሽ ወጭ መብታቸውን እንዲጎናፀፉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ 56 ብሄር ብሄረሰብ የክልል መንግሥት መሆን ትፈልጋለህ አትፈልግም፣ ከዳቦና ከድንጋይ የቱን ትመርጣለህ እያሉ የህፃናት ጨዋታ ማጫወት የህሊና ድህነት ነው እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ‹‹የንጉስ ግብር አልበላ አለ እየተባሉ በአደባባይ ለምን ይጨፍጨፋ፣ እንደ ሲዳማ ከ69 በላይ ሰዎች ግድያ፣ በዎላይታ 21 ሰዎች ሞት  ምን እንማራለን!!! ቀጣዮ የክልል መንግሥት ጠያቂ ተረኛ ማን ነው!!! የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ይህ ካልሆነ ህገ-መንግሥቱን መቀየር አንዱ አማራጭ መንገድ እንደሆነ መንግሥትን ማማከር፣ ህዝባዊ ውይይቶች ማካሄድ ወዘተ ይጠበቅባችሆል እንላለን፡፡

የዎላይታ ብሄራዊ ክልላዊ  መንግሥትነት ጥያቄ 21 ሰዎች ሞቱ፡፡

የዎላይታ ህዝብ ጥያቄ፡- ‹‹የሪፈረንደሙ ቀን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በአስቸኮይ ይገለፅልን!!!›› ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ቀኑን ቆርጦ የማሳወቅ ኃላፊነቱ ከሆነ፣ ደም ሳይፈስ በሰላማዊ መንገድ ለቀረበ ጥያቄ ቀኑን ማሳወቅ ለምን ተሳናቸው!!! የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ኦዲፓ ብልፅግና ፓርቲ፣  ከሲዳማና ዋላይታ ህዝበ-ውሳኔ ጥያቄ መልስ የመስጠት ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት የሰዎች ህይወት ማለፍ ተጠያቂ ናቸው እንላለን፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በእራሱ ፍቃድ ህገመንግሥቱን በመጣስ የክልል ምርጫ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ህወሓት ወታደራዊ ኃይል ስላለው ዝንቡን እሽ የሚለው የፌዴራላዊ መንግሥት መከላከያ ሠራዊት አልተገኘም፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩም ህወሓት በምርጫው ካላሸነፈና ሌላ ፓርቲ ካሸነፈ አንቀበለውም በማለት ተሳልቀዋል፡፡ ህዝቡም በአንድ አገር ሁለት መንግስት አለ እያለ ከሌላው መንግሥት ድጋፍ ለማግኘት ሞክረሃል እየተባለ በኦዲፓ ብልፅግና ይመታል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ የክልልነት ጥያቄዎች፣ የደቡብ ክልልን በአምስት ክልሎች ስር ለማዋቀር የተደረገው የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ጥናት በተሳታፊዎቹ ውድቅ ሆኖል፡፡ በህገመንግሥቱ የህዝብ ጥያቄ መሠረት ክልል የመሆን የማንነት ጥያቄ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ ሃምሳ ስድስት ብሄር ብሄረሰብ አካቶ በአንድ ስልቻ ከቶ ለሃያ ሰባት አመታት ይገዛ የነበረው ህወሓት/ ኢህአዴግና፣ ብልፅግና/ኢህአዴግ ለሁለት አመታት በህገመንግሥቱ የተቀመጠውን መብት እንደ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሆሳዕና፣ ስልጤ ጌዲኦ፣ ሸካ፣  ወዘተ ክልላዊ መንግሥትነት መጠየቃቸው የህገመንግሥቱ ሃገር የመበተን እርግማን ወይም በረከት ሆኖል እንላለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል- ኖአሚን በጋሻው

የአባ ዱላ ዱላ…ዶሮ ማታ!!!

ፌዴራዊ መንግሥታዊ አወቃቀር ያጠና ስንት ሃገር በቀል ምሁራን እያሉ መፍትሄ ከታጣ በባህር ማዶ ምሁራን ይጠና ሰዎች አይገደሉ እንላለን፡፡ የፖለቲካ ካድሬዎች የዚህን ችግር ከወገንተኝነት ነፅተው መፍትሄ ማግኘት አይችሉም እንላለን፡፡ ደኢህዴን ብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ክልልን በአዲስ መልክ በአምስት ክልልነት ለማዋቀር በአባ ዱላ የተጀመረው አዲስ የፖለቲካ መዋቅር  የወላይታ ምክር ቤት አባሎች ሰላሳ ስምንት መቀመጫ ትተው መውጣታቸው ተሰምቶል፡፡ ያለህዝብ ፍላጎት የሚደረግ ሁሉ እንደጤዛ ይረግፋል እንላለን፡፡ በህገመንግሥቱ መሠረት ኢትዮጵያ ከአስር ወደ መቶ ትናንሽ መንግስትነት መሸንሸኖ አይቀሬ ነው እንላለን፡፡ ብልፅግና ፓርቲና ተፎካካሪ ፓርቲዎች የብሄር ብሄረሰቦችን ጥናት ማድረግ በፖለቲካ ሴራ የተጫነብንን ህገመንግሥት በተለይ መንግስታዊ አወቃቀር በዘርና ልሳን ላይ በመመስረቱ የተፈጠረ ወደፊት የወሰን ግጭት ወደ ማያበራ ጦርነት  የሃገሪቱን ህዝብ ለሞት፣ እስራት፣ ድህነት፣ እርዛትና ስደት ስለሚዳርግ ህዝባዊ ውይይት በማድረግ መፍትሄ መፈለግ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

‹‹ከእሁድ ማታ ጀምሮ በነበረው አለመረጋጋት ግጭቱ በበረታባት በቦዲቲ ከተማ የሞቱት ሰባት መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር መብራቱ፤ ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በአጠቃላይ 21 ሰዎች ተጎድተው የመጡ ሲሆን ሆስፒታሉ እንደደረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሁለት መሆኑን ተናግረዋል። በሶዶ ክስርስቲያን ሆስፒታል በአሁኑ ሰዓት ሦስት ሰዎች በጽኑ ሕሙማን ክፍል እንደሚገኙ የሚናገሩት ዶ/ር መብራቱ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ክፉኛ የተጎዱ መሆናቸውን አመልክተዋል። ጉዳት ደርሶባቸው ከመጡት መካከል 16 ሰዎች የተለያየ ሕክምና አግኝተው ወደቤታቸው መሄዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ወደ ኦቶና ሆስፒታል በግጭቱ ተጎድተው የገቡት አራት መሆናቸውን ዶ/ር መብራቱ ቢገልፁም ሁለት ሰዎች ብቻ እግራቸው ላይ በጥይት ቆስለው መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጌታሁን ሞላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትተው የሞቱ ሰባት ሰዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር መብራቱ ሦስቱ በተለምዶ ማዘጋጃ ሰፈር የሚባለው አካባቢ፣ ሁለት ማዕዶት ሰፈር፣ ኦቶና ሆስፒታል መሄጃ ላይ 21 ማዞሪያ በመባል የሚታወቀው ሰፈር ደግሞ ሁለት መሞታቸውን በመጥቀስ እነዚህ ሰዎች ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አለመምጣታቸውን አረጋግጠዋል። ››ምንጭ ፡-/https://www.bbc.com/amharic/news-53753308 ወላይታ፡ በወላይታው አለመረጋጋት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 16 መድረሱ /ተገለፀ

ADDIS ABABA, Ethiopia

Security forces may have used excessive force to quell Monday’s protests over autonomy in the Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region (SNNPR), the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) said on Tuesday. Widespread protests erupted in numerous towns in the Ethiopian state’s Wolaita zone on Monday, leading to violent confrontations between civilians and security forces. Two versions came out as to the cause of the deadly incident, the commission said in a press release. Protesters claimed to have taken to the streets after zonal officials were detained for demanding immediate recognition of the Wolaita zone as a separate regional state government. The government claimed that the officials were detained because they were preparing to call for civil unrest in the area, said the EHRC. ….Some 178 people have been detained, 28 of whom are senior officials of the zonal administration, the statement added. The official called for speedy investigations into the deadly confrontations. (https://www.aa.com.tr/en/africa/ethiopia-protesters-may-have-faced-excessive-force/1938616) Ethiopia protesters may have faced excessive force

የህግ ሉዐላዊነት በኢትዮጵያ ምድር ይስፈን!!!

ፍትህ ለሰማዕታት!!! አሰቃቂ ግድያ ፈፃሚ ፅንፈኛ ቄሮዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ምንጭ፡-

{1} https://zehabesha.info/archives/109404 “ስልጣን ላይ እያለን የምንዘርፍበት ስንወርድ የምንሸሽበት ሳይሆን አገልጋይነትን ለትውልድ የምናስተምርበት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ/by ዘ-ሐበሻ/August 11, 2020

3 Comments

  1. ቁጭ ብሎ ቡና እየጠጡ መለቅለቅ ቀላል ነው:: ወላይታ ክልል ከሆነ የወላይታ ረፑብሊክ ከጎን ደግሞ የሀድያ ከዚያም የስልጤ ረፐብሊክ ይሆኑና ከትግራይ ረፐብሊክ ጋር አምባሳደር ይለዋወጣሉ? ይህ ወያኔ 27 አመታት ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማፈራረስና የዘረኝነት በሽታ ፌዴራል መንግስት እንዳይስፋፋ መገደብ አለበት:: ዛሬ የወላይታ ህዝብ እጅግ ስለበዛ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሄዶ ካልሰራ መኖር አይችልም:: መሪ ተብዬዎችም ለራሳቸው ልዩ ፕሬዚዴንታዊ ጥቅም ላይ ከማተኮር ሰፊው ህዝባቸው ባንድ ክልል እንዳይታጠር የበለጠ ኢትዮጵያዊነት ላይ ቢሰሩ መልካም ይሆን ነበር

  2. እውነቱ
    What is good for the goose is good for the gander የሚለውን አባባል ሰምተህ የምታውቅ አልመሰከኝም፡፡ ለሲዳማ የተሰጠው መብት ለወላይታ የማይሰጠው ከምንድን ነው? አንዳንዴ ሳያስቡ መፃፍ የህን ያመጣል፡፡ በበኩሌ ይህን ክልል የሚባል ጣጣ አጥፍቶ የፈጠሩትን እርኩስ ወያኔወችም አብሮ አጥፍቶ ኢቶጵያን በቋንቋ ሳይሆን በጆግራፊ ክፍለሃገር ከፋፍሎ ቢስተዳደር ደስ ይላል፤ ካለዚያ ግን ምንም ፍሬ የለውም፡፡

  3. ዶ/ር አብይ ደቡብ ላይ የከፈተውን የመውጫ በር መልሶ መዝጋት እንደማይችል እያወቀ በስሜትና ሊመጣ የሚችለውን ነገር ቸል በማለት ትልቅ ስህተት ሰርቷል! ሁሉም የደቡብ ብሄረሰቦች የክልል እንሁን ጥያቄ ቢጠይቁ ህግ የሰጣቸው መብት ነው !ህገወጥ ስራ የሚሰራ ካለ አንደኛው የህውሀት የተንኮል ህገ መንግስት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለምን ጠየቃችሁ፣እኔ እንደፈለኩ ላዋቅራችሁ እያለ የማይጠበቅ ወንጀል እየሰራ ያለው የ ዶ/ር አብይ መንግስት ነው! ለዶ/ር ዐብይ ትልቅ አመኔታ ቢኖረኝም ኦረሮሞን ኦሮሞ አይገድለውም በማለት ኦሮምያ ውስጥ የሚሰቀጥጡ ወንጀሎች ሲሰሩ የወንጀለኞች ተባባሪ እስኪመስሉ ድረስ ለወንጀለኞች ሽፋን እየሰጡ ነገር ግን በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ እያደረጉ ያሉት ግድያና ማስፈራርያ በሌሎቹ ብሄረሰቦች ጥርጣሬን እየፈጠረባቸው ነው! ይህ የህውሀት የሰይጣን ህግ ህገ መንግስቱ እስካለ ድረስ የኢትዮጵያ ን ሰላም ማሰብ ይከብዳል!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.