ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ዶክተር አብይ አሕመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር (አንድነት፣ የቅንጅት ስዊዘርላንድ የውይይት መድረክ)

ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም.
ለክቡር ዶክተር አብይ አሕመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር
አዲስ አበባ

abiy

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ሰላምታችንን አስቀድመን እናቀርባለን።

በመጀምርያ ስለ እኛ ማንነት በጥቂቱ እንግለጽልዎ፣ እርስዎም የሚወዷት ውድ ኢትዮጵያን አብዝተን የምንወድ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገራችን ወጥተን በየአህጉራቱ የተበተንን፣ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሠለጠንንና በመሰልጠንም ላይ የሚገኙ ወጣቶች የሚገኙብን፤ በእካል ከኢትዮጵያችን በብዙ ሺህ ማይሎች ብንርቅም ዘወትር በጸሎታችንና በሀሳባችን የማንለያት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነን። በሣምንት አንድ ጊዜ ዘመኑ ባስገኘልን ቴክኖሎጂ የፓልቶክ የመወያያ ዘዴ በ‘’ቅንጂት ስዊዘርላንድ የመወያያ መድረክ’’ እየተገናኘን እንመካከራለን፤ ለሀገራችን በየጊዜው ከምናደርጋቸው የገንዘብና ቁሳቁሳዊ አስተዋጽዖ በተጨማሪ ለውጡን እንዴት አድርገን ማገዝ እንደምንችል ሀሳብ እያዋጣን እንመካከራለን፤ እንዲያው ለርስዎ ይኽን አደረግን አይባልም እንጂ በየምንኖርባቸው አገሮች ተደራጅተን በንዋይም ሆነ በሙያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ አድርገናል በማድረግ ለይም እንገኛለን። ለህዳሴ ግድብ ቦንድ የገዛን፤ ለ EDTF የበኩላችንን ያደረኝ ብዙዎች ነን።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ፤ የሀገራችን ሰላም፣የሕዝባችን ደህንነት ብሎም የኢትዮጵያ አንድነት ያሳስበናል። የመንግሥትዎ ቸልተኝነት ደግሞ በአያሌው አስደንግጦናል። የሕግ የበላይነት የሚባል ነገር በፍጹም የማይከበርበት ሀገር ስትሆን ማየቱና መስማቱ አሳምሞናል። በቅርቡ በዘፋኝ ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ግድያን ምክንያት አድርጎ በኦሮምያ ክልል የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በዚህ ምእተ ዓለም ውስጥ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሆኖ እንደማያውቅ ተንቀሳቃሽ ምስሎቹን ያዩ ሁሉ የሚስማሙበት ነው። ሰው ሰውን አረዶ ቤት ንብረቱን አቃጥሎ ከሞት የተረፈውን የቤተሰብ አካል አንተ መጤ ነህ እዚህ ልትኖር አይገባም እያለ በገዛ ሀገሩ መግቢያ መውጫ ሲያሳጣው፣ መስማትና ማየት ለእኛ በመልክ፣ በቀለምም ሆነ በታሪክ የማይመስሉን ሀገራት በጥገኝነት መጥተንባቸው በሰላም ለምንኖር ሰዎች አስደግጦናል በእጅጉ አሳፍሮናልም። ጥንታዊት ኢትዮጵያ የሦስቱም ታላላቅ እምነቶች ሀገር፤ የመቻቻል ተምሳሌት የነበረች ኢትዮጵያ ዛሬ ምነው የአውሬ መፈንጫ ሆነች? ብሎ መጠየቁ የዋህነት ቢመስልም ያ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን ሲጨፈጨፍና ንብረት ሲወድም የክልሉ ሕግ አስከባሪዎች የት ሄደው ነው? የፌደራሉስ?፤ ገዳዮች የስም ዝርዝር ይዘው እየመረጡ በአማርኛ ተናጋሪውና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኙ ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ የመንግሥትዎና የክልል መንግሥት ተብዬው ዝምታ ጭካኔ ብቻ ሳይሆን ከገዳዮች ጋር መተባበርን ያመላክታል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ይጣራ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም " ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን

ከዚህ ሀዘን ሳንወጣ፣ ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአሁን አሁን የተጎዳውን አካባቢና ወገን ሄደው ያጽናናሉ፤ የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማም ለተወሰኑ ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ፣ ለተፈናቀሉና ቤት ንብረታቸውን ላጡ ቢያንስ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋሉ፣ ለዚህ የዘር ማጥፋት/ማጽዳት ጭፍጨፋ ዋናው ተጠያቂ በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የኦሮምያ ክልል መንግሥት ስለሆነ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ንብረታቸው የወደመባቸውን ክሶ ወንጀለኞችን ለፍርድ ያቀርባል ብለን ስንጠባበቅ፤ የአቶ ሽመልስ የናዚዎችን የ1933 Final Solution“, መሰል ንግግር አፈትልኮ ወጥቶ ሰማነው።

ለካ ከ8 ወራት በፊት የታቀደውና በሚስጥር የተነገረው እየተተገበረ ነው?

እውነት ነው አቶ ሽመልስ ክፉኛ ግራ አጋብቶናል። እውነት የፓርቲዎ መመርያ አቶ ሽመልስ እንዳለው ነው? ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ይኽ ሁሉ ከምናውቀው የክቡርነትዎ ስብዕና ጋር ከቶውንም አይሄድም፤ ትዕግሥትን እንደ ፍርሃት ደግነትን እንደ ሞኝነት የሚቆጥሩ ብልጣ ብልጦች ‘’አይብ ሲያድር አጥንት ይሆናል’’ ሆነው ይሆን?። ትግላቸው ሁሉ ለእኩልነት ሳይሆን ለበላይነት እንደሆነ እያየንና እየሰማን ዝምታው እስከ መቼ? እርስዎም በተደጋጋሚ እንደሚሉት ሁሉም ሰው፣ባለሥልጣናትም ጭምር ከሕግ በታች እንጂ በላይ አይደሉም እና ስለሕግ የበለይነት ብለው እባክዎ ሕግና ሰብአዊ መብትን አስከብሩልን!

 

ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር፣

ሀ. ወንጀለኞችና እጃቸው ያለበት ባለሥልጣናት፤ በቸልተኝነት የእልቂቱ ተባባሪ የሆኑ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ፣

ለ. ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉባቸው፣ለተጎዱባቸውና ንብረታቸው ለወደመባቸው የክልሉ መንግሥት ካሣ እንዲከፈል፤

ሐ. ለተፈናቃዮች ፣ አስፈላጊው ቁሳቁስና መጠለያ ከተሟላ ጥበቃ/ዋስትና ጋር እንዲዘጋጅላቸው

መ. አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ፤ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ የትንኮሳ ንግግር ላደረጉት ተጠያቂ እንዲሆኑና ለፍርድ እንዲቀርቡ፣

ረ. ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታውጆ ሰንደቅ ዓላማችን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዓድዋ፡ የቅኝ ግዛት ዘመን ትርክትን የቀየረ ገድል

 

በመጨረሻም የጥላቻ እና ለፍጅት ቅስቀሳ የሚያደርጉ በሙሉ እኩይ ተግባራቸው ስር ሳይሰድ ለፍርድ እንዲቀርቡ በትህትና እንጠይቃለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ ይጠብቅ።

አንድነት፣ የቅንጅት ስዊዘርላንድ የውይይት መድረክ አስተዳደርና ታዳሚዎች ዙሪክ/ ስዊዘርላንድ

5 Comments

 1. Well, it must be said that your letter addressed to the PM in general terms is truly appreciable!
  I would like to hope that as a group which has its own platform of the very worrisome situation in the country , you would be able to challenge any critique without being offended .
  . Do you really believe that the PM does not know or is not well informed about the very dirty and deadly political game of his own party for the last couple of years ?
  .Do you really believe that the PM has nothing to do with the coming into being of Queero by being part and parcel of the local government and causing a huge and deep pain to the innocent people of Ethiopia?
  . Yes, it is the right thing to expression your concern that the government in general terribly failed both in terms of prevention and swift action to stop the genocide . But why you seem unnecessarily politically and diplomatically correct by not holding the PM, the head of the government and the commander-in chief responsible for the very horrible crime of genocide ? Who should be in the forefront of responsibility and accountability other than the head of the government who terrible failed either to prevent or to take swift action and mitigate the severity of the crime ? Why you chose to go around the bush ?
  By the way, why you terribly failed to call a spade. a spade ( a genocide a genocide)? Is it because you did not want to upset the PM who stupidly failed to discharge his responsibility or. you are victims of a very nonsensical propaganda that days calling a spade a spade would make those deadly extremists more deadly? If this is the case, forget about the impact or effectiveness of you letter of complaint !
  . Agree or disagree , unless we talk about our own tragic political behaviors and actions straightforwardly and clearly , forget about getting things going in the right direction !!!

  With all due respect!!!

 2. “ስለሕግ የበለይነት ብለው እባክዎ ሕግና ሰብአዊ መብትን አስከብሩልን”
  ልመና ኢትዮጵያን የትም አላደረሳት ወደፊትም አይበጃትም። ሽመልስ አብዲሳ ያላሳመነውን አደናግረናል ያለው በናንተ ዘንድ የደረሰ ይመስላል። ሰውዬው ከነ ከፓርቲው አካል ጀምሮ ፣ከቡድኑ የአማራ ክልል አጋዦቹ አባ አጨብጫቢዎቹ ፣በኢትዮጵያ የሚካሄውን በደንብ ያቁታል ።እነርሱን ደልዪ፣ለምኜ ያዋጣኛል ብሎ ማሰብ ዶሮን በመጫኛ ጣሏት አይነት ተራ ቁማር ደሞ ቁማሩ መብላቱን ነግሮናል ። ስዊዝ ተቀምጣችሁ ረዥም ጽሑፍ ማቅረባችሁ ካልቀረ ማድነስበሱ ያስተዛዝባል።
  “የ1933 Final Solution (end Lösung )መሰል” ሳይሆን፣ ነው። በመሪቻችን ላይ የቀን ቅዠት አይናወጠን።

 3. አንተ ለኢትዮጲያ ተቆርቃሪ ከነበርክ ከወራት በፊት ሞጣ ላይ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ እኩይ ተግባር ሲፈፀም ዬት ነበርክ አብዛኞቻችን አገር ወዳድ እየመሰልን ግን ብሄርተኝነት ያጠቃናል ኢትዮጲያን የሚወድ በሙሉ ቦታና ብሄር ሳይመርጥ ወንጀልን መጥላት ኣለበት ይህ ነው አገር መውደድ ፡በሰሞኑ የአርቲስቱን ግድያ አስመልክቶ በተፈጠረው ነገር እኛም አዝነናል፡፡

 4. ሎሬት መልካም ብለሀል ግን አድራሻው ለአለም ሰብአዊ ድርጅቶች ለአውሮፓ መንግስታት ቢሆን ትርጉም ይሰጥ ነበር። ሰውየው አዘኔታ የለውም ሰንደቁን ዝቅ አድርገህ ስቀል ትለዋለህ ያን የሚያደርገው እኮ ሲያዝን ነው በተጻራረ የተናገረው ገዳዮቹን ሟቾች አድርጎ ነው ። በአማራ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ነገር ልቡ አይደርስም። በውሳኔው ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሱ እጅ የለበትም ማለት አይቻልም።
  ብአዴን የሚባለው ሙትቻ በእግሩ ካልቆመ የአማራው ስቃይ ይቅጥላል አሳምነው ጽጌ ነብሱን ይማረውና የተናገረው ይህንኑ ነበር። ብ3አዴን እሱን አሳርዶ በነሽመልስ መቀለጃ ሁኗል።

 5. የተማፀናችሁት ጠ/ሚር ከትላንት በስትያ ባደረገው ንግግር ሟቾች በ3 እጅ ኦሮሞ ነው ብሎ አርፎታል። እናቱ አማራ ለመሆናቸውን ባለፈው OBN በሰጠው ኢንተርቪው ክዷል ። የናቱን ማንነት የካደ ሌላ ብዙ ነገር ወደፊት ይክዳል ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.