አማራ ሰፊ አገር እንጅ  ክልል ከልሎት አይኖርም! – በላይነህ አባተ

Flagየአማራ ክልል እየጮህ፣ ጋዜጠኛ ነኝ የምትል ለንጨጫም፤
አማራ በአንተ ላንቃ እንጅ፣ ክልል ኖሮትም አያውቅም፡፡

ቁማር የሚጫወቱብህ፣ ባንዳው ገረዱ ብአዴን፤
የተንኮል ቁማርተኞቹ፣ ከብት መስሏቸው ልክ አንተን፤
ክልልህ ግባ እያሉ፣ በሜንጫ አረዱት አማራን፡፡

አማራ ነፃ ሕዝብ እንጅ፣ የእንሰሳ መንጋ አይደለም፤
እንደ ከበት በክልል ታስሮ፣ ሳር ቅጠል ሲነጭ አይኖርም፡፡

አማራ እንደ  አንበሶቹ፣ እንደ አያቶቹ በርትቶ፤
በመላ እርስቱ ይኖራል፣ ሰው አራጅ አውሬን ድል ነስቶ፡፡

የመላ ጦቢያ አፈሩ፣ ውሀው አየሩ ይመርመር፤
በአማራዎች  ሥጋ ደም፣ በአጥንቶቻቸውም ተከብሯል፡፡

ሙቱን ብአዴን ካርታ አርገው፤ የተንኮል ቁማር ቢሰሩም፣
አማራና ጪስ መውጫ በር፣ ጎዳናው ጠፍቶት አያውቅም፡፡

ለይህ አድግ ተንኮል ገብረህ፣ የአማራ ክልል የምትል፤
እንደ ብአዴን ካድሬዎች፣ የምትሸጥ ያያትህን ክብር፤
በታረደችው እርጉዝ ግማዴ፣ ልሳን ጉረሮህ ይታሰር፡፡

እንደ ክልል አምላኪ ጪራቆች፣ ፅንስን ተናቱ አያርድም፤
እንደ ጋማ ከብት ተነድቶ፣ እንደ አውሬ እሬሳ ጎትቶ አያውቅም፤
አማራ ሰፊ አገር እንጅ፤ ክልል ከልሎት አይኖርም፡፡

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

1 Comment

 1. ማንም በቋንቋ አና በብሔር የተደራጀ በኢትዮጵያ ውስጥ የኔ ብቻ የሚለዉ ክልል የሁላችንም መጥፊያ ይሆናል እንጂ እንደ አንድ ኢትዮጵያ አብሮ የማያኖረን ስለሆነ መንግስት መዉሰድ ያለበት እርምጃ :
  1.ይህ በመጠፋፋት የተመሰረተ ህገ አራዊት በማገድ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሊያኖር የሚችል አዲስ ሕገመንግስት ማዉጣት
  2.ልዩ ሐይል የተባሉትን መንደርተኞችን በመበተት ወደ ሌላ ስራ ማሰማራት
  3.የኦሮሚያ;የአማራ;የትግራይ ;የትግራይ የሚባሉት የፖሊስ አደረጃጀት በማፍረስ እና መመሪያ በማውጣት በየትኛው አካባቢ በመሔድ ፍትህን ይለአድሎ ሊያስተገብር የሚችል “የኢትዮጵያ ፖሊስ”ማደራጀት
  4.ፌደራሊዝሙን የአንዳቸዉንም የኢትዮጵያ ብሔር ስያሜ ያልያዘ አደረጃጀት መፍጠር ለምሳሌ ሰሜን ኢትዮጵያ ;ደቡብ ኢትዮጵያ ;ምስራቅ ኢትዮጵያ ;ምዕራብ ኢትዮጵያ እና መሐከለኛ ኢትዮጵያ ምክንያቱ የማን ብሔር በምን ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ብሔር ተሽሎ ነዉ በብሔሩ ሲደራጅ ሌላዉ ለምን በአቅጣቻ የሚሰየመው ።ይህ ፍትሐዊ አይደለም
  5.ሌላዉ ቋንቋ በተመለከተ ቋንቋ ከመግባቢያ በስተቀር ሌላ ትርጉም ሊሰጠዉ አይችልም ።ስለሆነም የኔ ቋንቋ በስፋት ካልተነገረ እንዲለሁም የፌደራል ቋንቋ ካልሆነ የኔ መብት አልተከበረም የሚለዉ ድንፋታ የትም የሚያደርስ አይደለም ።እንደ መፍትሔ ሊሆን የሚችል የፌደራል መስሪያ ቤቶችን ሁሉ እንግሊዝኛ እንዲጠቀሙ ማድረግ ።ሌላዉ በአዲስ በሚዋቀሩትን states ከሁለት ባልበለጡ በአከባቢዉ ከሚነገሩት ቋንቋዎች የስራ ቋንቋ ቢሆኑ የሚሻል የመስለኛል ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.