/

“ስልጣን ላይ እያለን የምንዘርፍበት ስንወርድ የምንሸሽበት ሳይሆን አገልጋይነትን ለትውልድ የምናስተምርበት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

abiyየምንገነባው ስርዓት ” ስልጣን ላይ እያለን የምንዘርፍበት ስንወርድ የምንሸሽበት ሳይሆን አገልጋይነትን ለትውልድ የምናስተምርበት ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሲቪክ ማህበራት አመራሮችና ተወካዮች ጋር ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።
በመድረኩ ላይ ከተሳታፊዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ብዙም ሳይቆዩ “አሳሪ ነው” ሲባል የሚተቸውን የሲቪክ ማህበራትና የበጎ አድራጎት ህግ እንዲሻሻል ማድረጋቸውን በበጎ ጉኑ አንስተዋል።
ነገር ግን አዋጁ እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር አውርዶ ስራ ላይ በማዋል ረገድ አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ አንስተዋል።
የህግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ መንግስት በተደጋጋሚ የሚያሳየው “ሆደ ሰፊነት ትእግስት” ገደብ ሊኖረው እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።
የሲቪክ ማህበራትና መንግስት የሰላምን ጉዳይ ለድርድር ሳያቀርቡ በቅንጅት መሰራት እንዳለባቸውም ነው ተሳታፊዎቹ ያነሱት።
ውይይት እየተደረገበት ባለው የመንግስት የ10 ዓመት መሪ አቅድ ላይ በሚገባው ልክ እየተሳተፈ አለመሆኑንም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው የጀመርነው ሪፎርም ተቋማት ሳይፈርሱ ባሉበት የመለወጥ ሂደት ነው ብለዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ አልፎ አልፎ ችግሮች ማጋጠማቸው የሚጠበቅ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የተሻለችና ሁሉንም ዜጎቿን በእኩል የምታቅፍ ሀገር እንገነባለን ብለዋል።
መንግስት ቀለል ብሎ በመቅረቡ አቅሙ የተዳከመ የሚመስላቸው አካላት እንደሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።
ነገር ግን የምንገነባው ስርዓት ስልጣን ላይ ስንወጣ የምንዘርፍበት፤ ስንወርድ የምንሸሽበት ሳይሆን አገልጋይነትን ለትውልድ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል።
በቅረቡ በኦሮሚያ ክልል ለመናገር በሚያሳፍር መልኩ በርካታ ዜጎቻችን ሞተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት ይህን ተከትሎ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አብራርተዋል።
በድርጊቱ ላይ የተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጠር ስር ውለዋል ብለዋል።
ትናንት የተጸየፍነውን በደል ዛሬ ላይ የምንደግመው ከሆነ ከግጭት አዙሪት ልንወጣ አንችልም ሲሉም ነው የተናገሩት።
ግጭቱን የብሔር መልክ እንዳለው አድርጎ የሚያራግቡ አካላት እንዳሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በግጭቱ በርካታ ኦሮሞዎች መሞታቸውን በአስረጂነት አንስተው፤ “ዋናው ነገር ግጭት ከተከሰተ መጀመሪያ የሚያጠቃው እኔን ነው የሚለውን መገንዘብ ያስፈልጋል” ብለዋል።
ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትወከል ሳይሆን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ሀገር መሆኗንም ነው የገለጹት።
ከዚህ አንጻር ጥቂት ሰዎች ሲያጠፉ ማህበረሰብን ጠቅልሎ መውቀስ አይገባም ሲሉም አብራርተዋል።
የሲቪክ ማህበራት ይህን በመገንዘብ በከተማ ሳይወሰኑ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በመዘዋወር ለሰላም መስፈን ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

3 Comments

 1. According to Medemer freaks EPRDF got dissolved and became PP to bring all ethnicities under one national umbrella . At the same time generations students in Oromia’s schools are being thought ANOLE until today found in children’s history books , the Anole history was put in Oromia’s schools while student in other parts of Ethiopia do not get thought this Anole history .

  Abaye Abiy start teaching the Oromo generations the true history of Ethiopia . In Oromia’s middle school and junior high schools, the Oromo children in Oromia had been thought officially in schools that Emperor Menilik committed savage acts cut Oromo women’s breasts , with his nephtegna settlers cutting breasts of Oromo women known as the Anole for decades Oromia ended up drinking milk from dobkeys according to these Smile history, detailed in children’s history books as part of the Oromia region’s curriculum .

  If this Anole is thought in schools within Oromia only and not thought in other parts of Ethiopia , it shows it was done to divide Oromos from other Ethiopians, purposely done to exacerbate the ongoing genocide in Ethiopia which lasted for close to three decades.

  Reform the curriculum !
  Tear down the anole monuments in Oromia!
  Call the ongoing genocide “an ongoing genocide”!

  Serve Ethiopian generations right by reducing cost of living , Abaye Abiy take economic reforms with poor Ethiopians in mind , the economic reforms should not always only be dictated by lobbyists sent by billionaire business investors !

  Abaye Abiy mogne nehh telala
  EPRDF ayaschilewum serqo kalbela

  Tamwal telekfwal EPRDF/PP besirqot
  Tana endetelekew beimboch Mela teft

  Medemer freak honenal bil EPRDF
  Kalserequ tezegajitewal lamakuref

  Abaye Abiy Medemeru qertobachew beqitu koninachew
  Enquwan leserequt leasaredutim alqoreqorachew

  Minew Geda Construction Plc. tekaw METECin
  Abaye Abiy erasu temesateo shomot liyasborebur GERDin

  Minew Takele Uma afenaqele Amaran ke Addis Ababa
  Querron begef metaweqiya iyadele endiwer endiyadeba

 2. ላም አለኝ በስማይ
  ወተቱዋን አላይ!

  ቃል በሰራ ይፈተናል
  ወሬ ምን ያደርጋል

  ካቢኔዎ የሚሠራውና እርስዎ የሚሉት ይፋለሣሉ

  እኔ በበኩሌ አገሪቱ በፈሪሐ እግዚአብሔርና fairness እየመራችሁ አይመስለኝም:: ከለማ ጋር መስመራችሁ ይለያይ እንጅ ሁለታችሁም oromizers ትመስላላችሁ:: የተበደለውን ህዝብ ኣንድ አድርጎ ከማስተዳደር ይልቅ እንዲታረድ ተደርጎአል: ይህም አንድ ቀን ሁሉም ይጠየቅበታል: በስውም በእግዜር ፊት:: የኢትዮዽያ renaissance በዘመናዊ ሳይንስና ሥልጣኔ : አለም ሞክሮ ባደግበት መንገድ እንጂ ልጆችን ገዳ በማስተማር እና ዘረኝነት በማስፋፋት አይደለም::

  ተቃዋሚዎችን እና ህዝቡን ያላስተፈ sensitive ዘረኛነት ፓሊሲ መተለምና መቱግበር ህጋዊ አይደለም::
  ያገሪቱ ቁልፍ መስርያ ቤቶች በዘር መሙላት አግባብ አይደለም::

  እግዚአብሄር ይርዳን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.