የአቶ ሽመልስ ንግግር የለውጡን አነሳስና የለውጡን ሂደት ለውጡን የሚያይበት አተያይ ትክክል አይደለም ስህተት ነው የሚል ሃሳብ አለኝ

nigusu
ለውጡ የመጣው በሁሉም ፍላጎትና ተሳትፎ በተለይም ደግሞ በወቅቱ የኦህዲድና የብአዴን አመራሮች ጥምረት እንዲሁም በኦሮሞና አማራ ህዝቦች ትግል በሌሎችም ብሄር ብሄረስብ ህዝቦች ግፊት ነው ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያውያን ፍላጎት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ለመመለስ ከለውጡ በፊት የተነሱ አንኳር ጥያቄዎች ለውጡን የግድ ያሉት አንኳር ጥያቄዎች የሁላችንም ጥያቄዎች ስለነበሩ በሁሉም ረገድ ለውጡን የግድ ያሉት መገፋቶች ሁሉንም የገፉ ስለነበሩ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ቤተኛና አልፎ ሂያጅ የሌለባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ፍትሃዊነትን እኩልነትን አላማው ያደረገ ህብረ ብሄራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ ትግል የተደረገበት እንጂ ከየትኛውም ወገን በተናጠል ከፍተኛ ሚዛን የወሰደበት ትግል አልነበረም ።
እኩል ርብርብ የተደረገበት የሚናና የቦታ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በመናበብ የመጣ ለውጥ ነው ። በኦሮሚያም የነበረው የትግል መነሻ ይኸው ነው ። አንድነት ነው አብሮነት ነው ። ኦሮሚያም ደግሞ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ እንድትሆን ነው ። እኩልነት የተረጋገጠባት እንድትሆን ነው ። በባህሪውም እሳቸውም ሲገልፁት እንደነበረው አቃፊና ደጋፊ ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲሉ እንደነበረው ይህንን በአንድነት የመኖርን አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን በአንድነት የመገንባት ሃሳብን ያጠነጠነ ለውጥ ነው ። ከዚህ ለውጥ የገቀዳው ለውጡ የወለደ የፓርቲያችንም ውህደት ይህንኑ ማእከል ያደረገ ነው ።
የፓርቲያችንም መስመር የሚመራበት የመደመር አስተሳሰብ እሳቤ የሚነሳው ከአንድ ብሄር ከአንድ ማንነት ሳይሆን ከሰው ልጅ ነው የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው ። ኢትዮጵያ ለሰው ልጆች ሁሉ እኩል የምትሆንበት አብረን የምናድግበትና የምንበለፅግበት የአንዱ ባይተዋር ሌላኛው ቤተኛ የማይሆንበት ኢትዮጵያ መገንባት የሚል ሃሳብ ያነገበ ለውጥ ነው ስለዚህ ከነዚህ መመዘኛዎች አኳያ ሳየው በርካታ ስህተቶች ያሉበት ሆኖ አግኝቼዋለሁ ።
ጥያቄ. .. በሁለቱ ፓርቲዎች መሃል መሻከርን ሊፈጥር ይችላል ሃገሪቷንም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ነገር ይሰማልና እንደዛ አይነት ነገር ሊኖር ይችላል ?
በመጀመሪያ ደረጃ ብልፅግና የሁለቱ ፓርቲዎች የሶስት ፓርቲዎች አይደለም ። ፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፡ ከምእራብ እስከ ምስራቅ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ነው ። ስለ አጠቃላይ ሃገራዊ ሁኔታ ስንነጋገርም ኢትዮጵያ ለሁሉም የምትመች አድርገን የምንሰራት ሃገር ትሆናለች ስንልም 86 ቱን ብሄር ብሄረሰቦች የሚመለከት ነው ።
በምንም መልኩ ግን ከተረጋጋን ከሰከንን በማንኛውም ሂደት ስህተት ይፈፀማል ። ማንም አካል ከስህተቱ ሊማር ይችላል ። ትግል ያድናል፡ ይህንን ሃገር የሚያድነው ትግል ነው ። አመራሩ ይታገላል አመራሩ ይታረማል የሚሻሻለው ይሻሻላል በመሆኑም ኢትዮጵያ ከያንዳንዳችን በላይ የኢትዮጵያ ህዝቦችም ከያንዳንዳችን አመራሮች በላይ ስለሆኑ እኛ አመራሮች በምንሰራው ስህተት ህዝብና ሃገር አይፈርስም ። ግጭትም አይፈጠርም ግን ደግሞ ይህን ስም ብሎ መናገር ሳይሆን ማስተዋል መረጋጋት ከስህተት መማር ይጠበቃል ።
( የጠ/ሚኒስትር ቢሮ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአቶ ሽመልስን ንግግርን በተመለከተ በኢሳት የዜና ፕሮግራም ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ ። )

3 Comments

 1. .Are you saying it is seriously dangerous and stupidly arrogant or just a mistake or unfair ?
  . I know you have no any moral and political ground to call a spade a spade and get It right !
  .I know that a very horrible way of doing politics by your ruling circle does not allow you to do so or to be what you to be !
  .I know you are one of the most self- disgraced and self- dehumanized cadres of EPRDF which now calls itself Prosperity !
  . you call it the way you want to, the rotten political system of ethnic and parochial politics will never take the people to the destination they desperately want be!
  . I do not know what kind and content of dangerously idiotic political statement or discussion you want to hear if you try to undermine or underestimate your body , the governor of The Oromo Regional state , Shimeles Abdesa?
  . It is good for you and for the people to get back to your very common sense and work hard to pave the way for the realization of true democratic system. If not , forget your monotonously nasty political propaganda !!!

 2. ወዳጄ አሁን ዝም ብትል ይሻልሀል ወንጀል ወንጀሉን እንድታነብ ሲሰጡህ ስታነብላቸዉ ነበር በመግለጫ ስም ያልተፈቱ ህጻናትን የሀሰት መረጃ ሰጥተዉ መቀለጃ ሲያደርጉህ ነበር። ሺመልስ እንዳለዉ ቁማሩ ተበልቷል ልብ ካለህ የአሳምነዉን ምሳሌ ተከተል አለበለዚያ የምትናገረዉን ሰዉ ይሰማኛል ብለህ አትድከም።

 3. የአማራ ህዝብ ታሪካዊ እና አደገኛ የህልውና ጠላቶች በቅደም ተክተል፤
  1ኛ፡ ብአዴን/ትህነግ ወይም አዴፓ/ኦነግ/ኦነግ ሽኔ
  2ኛ፡ የብአዴን ካድሬዎች
  3ኛ፡ ትህነግ ወያኔ
  4ኛ፡ ኦህዴድ/ትህነግ ወይም አዴፓ/ብልግና
  5ኛ፡ ኦነግ/ኦነግ ሸኔ/ኦነግ ወዘተ
  6ኛ፡ የውሸት የአንድነት ሃይሎች ለምሳሌ ኢዜማ፤ ግም ዜሮ ወዘተ
  7ኛ፡ ሆዳም አማራዎች ለምሳሌ፤ ግብዝ ኢትዮጵያዊ፤ ጉራኞችና እወደድ ባዮች እንደ ታማኝ በየነ አይነቱ ደንቆሮ ወዘተ
  8ኛ፤ ሆዳም የአማራ ምሁራን
  9ኛ፤ ሆዳም ተክፋይ የፌስ ቡክ አክቲቪስቶቸ
  10ኛ፡ ደከመኝ ……
  እንግዲህ አማራ ከፈጣሪህ ጋር ሆነህ እነዚህን አረሞች ካልታግልክ እንደ ዳይኖሰር ከምድረ ገጽ ትጠፋና በጠፉ ህዝቦች ስም ዝርዝር ውስጥ ትካተታለህ ማለት ነው፡፡ ሞት ለአሳማዎቹ ብአዴኖች፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.