ኦሞ የኢትዬጵያ አንድነትና ፍትሕ ማዕከል በወላይታ በተከሰተው ቀውስ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ – ሰሜን አሜሪካ

OMO Ethiopian Unity and Justice Center
August 11,2020

welayta 3ኢትዮጵያ ከ27 አመታት በላይ ካስቆጠረው ከአፋኙ የህወሀት ኢህአደግ አገዛዝ ተላቃ የተሻለ የለውጥና የሽግግር የሽግግር ሂደት ከጀመረች 3 አመታት ተቆጥሯል። ይሁን እንጂ በዚህ ሃያ ሰባት ዓመታት   ባስቆጠረው ረጅም ጊዜ ተወልደው በዚሁ ሥርዓት ውስጥ ያደገው ትውልድ በዘርና በቋንቋ በተቃኘው ክልልና ማንነት ራሳቸውን አቆራኝተው ከአገራዊ አንድነት ይልቅ ልዩነት እየተሰበከ ፅንፈኝነትን በሰፊው በመንገሡ በዚህ ስሜት በመጠመድ በህዝብ መካከል ጥርጣሬና ልዩነት እንዲፈጠር ተደርጓል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በእልፍ ወጣቶች መስዋዕትነት ዕውን የሆነው ለውጥ አንፃራዊ መረጋጋትና ዲሞክራሲና ነፃነትን በመስፈኑ በተገኘው አጋጣሚ በውጪው ዓለም ጭምር በስደትና የብረት ትግል ይሳተፉ የነበሩት አገራቸው ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ሁኔታዎች በመመቻቸታቸው በርካታዎች ከጎሬቤት አገራት ፣ አውሮጳና አሜሪካ ጥሪ የተደረገላቸው ጥሪውን ተቀብለው በአገራቸው የወደፊት ዕጣ ፋንታ ሚና እንዲኖራቸው ተደርገዋል፤ በዚህም አንዳንድ ድርጅቶችና ስብስቦች ዕድሉን ለጥሩ አገራዊ ግንባታ ማዋል ሲገባቸው ድርጅታዋዊ መዋቅራቸውን በተቃራኒው ዘረግተው ሕወኃት በዘረጋው መንገድ ሕዝባችንን በዘርና ሐይማኖት በማለያየትና ግጭት በመቀስቀስ በሀገራችን ከፍተኛ መፈናቀል ሞትና ንብረት ውድመት እንዲከሰት ተደርጓል! በወላይታ ዞንም የዚህ ፅንፈኛ ቡድን ቀስ በቀስ ሥር በመስደድ የወላይታ ለብቻው ክልል መሆን የችግሮች ሁሉ መፍቻ እንደሆነ ሕዝብንና ወጣቱን በመቀስቀስ አብሮት ለዘመናት ከኖረው የአካባቢውና አጎራባች ህዝቦች ጋር በማጋጨት፣  ከአብሮነት ይልቅ ለብቻ ክልል የመሆን ጥያቄ ብቻ እንዲጎላ ተደርጓል። ይህም መሆን ካለበት አገራችን የኮሮናን ተስቦ በመከላከል አደጋና በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ከግብፅ ጋር በገባቺው የፍጥጫ ውስጥ በምንገኝበት ምቹውን ጊዜ ጠብቆ እንደ አንድ ሁነኛ ዜጋ ሀገር ሲረጋጋ በሰላም እንዲፈታ ከመንግስት ጋር በመመካከር መፈፀም ሲቻል ጥያቄውን በጉልበት ለማስፈፀም እንቅስቃሴ መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። አክራሪ ፅንፈኛ ቡድኖች ዘጎቻችን በተለያዩ ቦታዎች እንደበግ አርደው በርካታ የሀገራችን ከተማዎች ተቃጥለው መንግሥት ይህንን ለማረጋጋት በሚሰራበትና ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ባለችበት ጊዜ የወላይታ ዞን አመራር የክልል መንግስት መዋቅር ለማፍረስ መሞከሩንና የእዝ ሰንሰለቱን ግኑኝነት ማቋረጡን የዞኑ አመራር በይፋ ማወጁ፣ ከዚያም ከፍ ብሎ ህጋዊ የመንግስት  ባንድራ በማውረድ የወላይታ ክልል ባንዲራ ከዞን እስከ ቀበሌ እንዲሰቀል መደረጉ፣ 38 የክልል ም/ቤት አባላት ጥለው እንድወጡ መወሰኑ የመንግስትን  ህጋዊ አሰራር ማደናቀፍ  አዝማሚያ የታየበት ነው። የኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማእከል ለአንድነትና ለፍትህ የሚሰራ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ማንኛውንም የህገወጥና አመፅ ተግባርን አጥብቆ ያወግዛል፣ መንግስት ሁኔታውን ለመቆጣጠር እጅግ የዘገየና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እስኪወጡ መጠበቁ ጉዳዩን ያወሳሰበ እንደሆነ ብንገነዘብም አሁን ህግን ለማስከበርና የዜጎችን ሰላምና ደሕንነት ለማስጠበቅና ለማረጋጋት የጀመረውን እርምጃ ጥንቃቄና በኃላፊነት መንፈስ አጠናክሮ እንዲቀጥልና ሁሉም ነገር በህግና በህግ ብቻ እንዲታይ ድጋፋችንን እየገለፅን የፀጥታ ሀይሎች በምንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ በህዝባችን ላይ ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ እርምጃ እንዳይወስድ አበክረን እናሳስባለን።

ሰፊው የወላይታ ህዝብም ራሱንና መላ ቤተሰቡን ለአደጋ ሳያጋልጥ ደህንነቱን በመጠበቅ በማስጠበቅ በዚህ ቀውስ ምንም ያላለፈለት የድሀ ልጅ እንዲሞት ከቶውንም ዕድል ሊሰጠው አይገባም! በተለይም በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ አገራት ሆነው የራሳቸውን ሰላምና ደህንነት አስጠብቀው በሚዲያ ቀውስንና ጦርነትን ከሚቀሰቅሱ አክትቪስቶችና ፓለትከኞች ፕሮፓጋንዳ ጆሮ ዳባ በማለት ፣ ለሰላምና አንድነት ዘብ እንዲቆምና ሰላምን  ከሚፈታተኑ ከማንኛውም ተግባር በመቆጠብ መንግሥት ህግን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ የተለመደውን ትብብር እንድያደርግ እንጠይቃለን።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትና የክብር ተሰናባቾች ለሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ስትታገሉ የቆያችሁ ስለሆነ የሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ከማንኛውም ጉዳይ በላይ በመሆኑ ለሕዝብ ሰላምና ድሕንነት ዘብ እንድትቆሙና ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በሚታገሉ ሀይሎች ጎን በመሆን ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ወጥተው በውስጡ የሚኖሩትን ሌሎች ኢትዬጵያዊያን ደህንነትና ንብረት ጥፋት ውስጥ እንዳይገባና የተከበረውን የወላይታ ሕዝብ ታሪክ እንዳያጠለሽ የበኩላችሁን ሚና እንድትጫወቱ ጭምር እንጠይቃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የኦሞ ኢት/ አንድነትና ፍትህ ማዕከል

ሴሜን አሜሪካ

 

OMO Ethiopia Unity and Justice Center.
4017 Harvest Run Clarkston, GA 30021 USA,
Phone 1+571- 470-2353, Email info@omoethiopia.org OR terotemamo@gmail.com,
Website OMOEthiopia.org

2 Comments

  1. Don’t tell us about your conspiracy politics, dead! Go away! We strongly believe in the unity of Ethiopia. We are Ethiopian! The question is only about the administrative issue. Omo is the name of the lake, but not the identity of people. You wish to merge again and establish unwanted administrative region to the people of Wolaytta without the need of the people. No way! This is conspiracy politics of PP. Where do you want to take Gamo, Gofa, Dawro, etc. Be right minded to think in the right way. These all people demand the autonomy to facilitate development soon.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.