የህሊና ጥሪ ለሰብአዊነት አስቸኳይ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በፍራንክፈርት  

Saturday 29 August 2020 11:30 Hauptbahnhof

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የክልል አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በድብቅ ተቀድቶ በቅርቡ በብዙሃን መገናኛ በተሰራጨው ንግግራቸው ስለ ፓርቲያቸው ስራ እና ፓርቲያቸው የሄደበትን አካሄድ እና የሚሄድበትን “በማደናገር እና በማሳመን” ባሉዋቸው መንገድ በአማራ ላይ በፕሮግራም የተያዘ ታቅዶ የተፈጸመ እና እየተፈጸመ ያለ ዘር ማጥፋት በአማርኛ ቋንቋ ላይ የሚካሄደውን ቋንቋ ማጥፋት እናወግዛለን።

ይህንን ታቅዶ የሚካሄድ የዘር ማጥፋት መርሃግብር ለጀርመን ህዝብ እና መንግስት ለአውሮፓ ህዝብ እና መንግስታት እንዲሁም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እናሳውቃለን።

በአማራ ላይ እስካሁን ሲካሄድ የቆየው እና በመካሄድ ላይ ያለው የሚፈጸመው ጄኖሳይድ እንዲቆም።

በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ላይ የሚፈጸመው ጄኖሳይድ እንዲቆም።

በጋሞዎች በወላይታዎች በጉራጌዎች ላይ የሚካሄድ ጀኖሳይድ እንዲቆም።

ያለ እውነት የተወነጀሉ የህሊና እስረኞች

1.ወይዘሮ አስቴር ሥዩም  2.አቶ እስክንደር ነጋ  3.አቶ ስንታየሁ ጨኮል

4.አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂኒየር)  5.አቶ ልደቱ አያሌው

እንዲሁም የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞች  1.አቶ በላይ ማናዬ

2.አቶ ሙሉጌታ አንበርብር  3.አቶ ምስጋናው ከፈለኝ  4.አቶ ዮናታን ሙሉጌታ

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈቱ።

በእስረኞች ላይ የተፈጸመውን ድብደባ እና ማስራብ እናወግዛለን።

የዘርማጥፋት ወንጀለኞች ቀስቃሾች አደራጆች አስፈጻሚዎች ፈጻሚዎች አለማአቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

በኢትዮጵያ ዘርማጥፋት እንዲቆም ለጀርመን ህዝብ እና መንግስት ለአውሮፓ ህዝብ እና መንግስታት እንደዚሁም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እናሳውቃለን ጥሪ እናደርጋለን።

የተፈጸመው ዘር ማጥፋት እና እየተካሄደ ያለው ዘር ማጥፋት በአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል እንዲጣራ እንጠይቃለን።

ሰልፉ ከ HAUPTBAHNHOF  FRANKFURT a.M.  11:30 ይጀምራል

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን

+49 160 4357232

[email protected]\

45

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.