‹‹ ግምገማው ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ ያደርጋል›› – ታዬ ደንደአ

Taye ‹‹ ግምገማው ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ ያደርጋል››  ታዬ ደንደአ
– ታዬ ደንደአ በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አዲስ አበባ:- የኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ያካሄደው ግምገማ ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ግምገማው ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።በክልል ደረጃ ከለውጥ ሂደት ጋር ተያይዞ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመገምገም በቀጣይ መወሰድ ስለሚገባቸው ዕርምጃዎች ያመላከተ ነው።
በውስጥ ሆኖ ከብልጽግና ዓላማ በተቃራኒ እጁን ሌብነት ውስጥ በመክተት የብልጽግናን ስም የሚያበላሽ፣ የብልጽግናን ካባ ደርቦ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ውጤት የማያስገኝ መገምገሙን አስታውቀዋል።
ብቃት የሌለውን፣ ሌብነት ውስጥ የተሰማራውን፣ በአመለካከትም ችግር ያለበትንም ከብልጽግና መስመር በማግለል በቀጣይ ኃላፊነት የሚሰጣቸው በእምነት፣ በመርህና በብቃት ለተሻሉ አመራሮች መሆኑን በተጨባጭ ማሳየት ያስቻለ ጅምር መሆኑን ጠቁመዋል።
በግምገማው ለውጡን እያጋጠሙ ያሉ ውጫዊ እና ውስጣዊ ተግዳሮቶች በአግባቡ መታየታቸውን አመልክተው፣ እንደ ውጪያዊ ተግዳሮት የታዩት የክልሉንና የአገርን ሰላም ለማወክ ሆን ብለው እቅድ በማውጣት፣ በጀት መድበው የሚሠሩ አካላት መሆናቸውን ተናግረዋል።
እነዚህ አካላት በዋናነት የሚመሩት በህወሓት ነው ያሉት አቶ ታዬ፤ በክልል ደረጃ ደግሞ ኦነግ ሸኔ የህወሓትን ፍላጎት ለማስፈን በመንቀሳቀስ ከለውጡ ጋር ተያይዞ የተሠሩ ሥራዎች ጎልተው እንዳይታዩ የማድረግ አቅጣጫ መከተሉን ጠቁመዋል።ክልሉ የጸጥታ ችግር እንዲያጋጥመው፣ ህብረተሰቡም በትግሉ ያመጣውን ለውጥ እንዳያጣጥም የሚያደርግ አካሄድና ችግር በመሆኑ ጥልቅ ግምገማ እንደተደረገበት አመልክተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ክስተት የሆነው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) በአገርና በክልል ደረጃ ከጤና፣ ከማህበራዊ፣ ከኢኮኖሚና ከፖለቲካ አንጻር ያመጣቸው ተግዳሮቶችም በዚሁ አቅጣጫ መታየታቸውን ጠቁመዋል።
ውስጣዊ ተብለው የተለዩ ተግዳሮቶች ከአባሉ ጋር ተያይዘው እንደሚታዩ የገለጹት አቶ ታዬ ፣ በአንድ በኩል የጎራ መደበላለቅ መከሰቱን አስታውቀዋል። በብልጽግና ፓርቲ ደረጃ በአመለካከትም፣ በፍላጎትም ያንን የሚያንጸባርቁ አመራሮችና አባላት ከሌሎች ኃይሎች ጋር የመሰለፍ ሁኔታ መታየቱን ጠቁመዋል።የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለህዝብ ጥቅም ከማዋል አንጻር የታዩ ግድፈቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል።እነዚህ በደንብ ተገምግመው የተጀመረው የዴሞክራሲ፣ የብልጽግና፣ የአንድነት፣ የህብረ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ጉዞ በፈጠነ ዕርምጃ ወደፊት እንዲራመድ በሚደረገው ርብርብ ትልቅ ተግዳሮት በመደቀናቸው ተነቅሰው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህ ሲደረግም በህግ አንጻር የሚታየው እንደተጠበቀ ሆኖ በፓርቲ ደረጃ የተካሄደው ግምገማ እያንዳንዱ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ መሆኑንም ተናግረዋል።መሥራት ሲገባው ሳይሠራ የቀረውን፤ መሥራት ሳይገባው ደግሞ የፓርቲውን መርህ ጥሶ ሲሠራ የተገኘ የታየበት መሆኑንም አመልክተዋል።
ግምገማው በፓርቲው አካሄድና በመደመር መርህ የተንጸባረቀ ሃሳብ መሆኑን በመጠቆምም፤ በኢትዮጵያ በአንድነትና ብሄራዊ ፍላጎቶች ሚዛን ጠብቆ ፍላጎትን የማረጋገጥ፣ በፊት የመጣንባቸውን ታሪኮች የመገምገም፣ የተሠሩ ስህተቶችን በትክክል አርሞ ማስተካከል፣ መልካም እሴቶችንና የተገኙ ድሎችንም አጎልብቶ ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት የተንጸባረቀባት ኢትዮጵያ እንድትገነባ በማለም መሆኑንም ተናግረዋል።
አባሉ በፓርቲ ዲሲፕሊን እየተመራ የፓርቲውን የፖለቲካ አስተሳሰብ በአግባቡ እየተተገበረ፣ ፕሮግራሙን አምኖ ስለመቀበሉና በሚፈለገው ደረጃ እየተጓዘ፣ ከብልጽግና መርህ አንጻር ሥራውን እየገመገመ ስለመሆኑ በግምገማው መታየቱንም አቶ ታዬ ተናግረዋል።ከእዚህ አንጻርም ጉድለቶችና ግድፈቶቹ በማስረጃ፣ በማሳያ እየታዩ ጠለቅ ያለ ክርክር መካሄዱንም ጠቁመዋል።ሁሉንም አባላት ያሳተፈና ጠንካራ ግምገማ የተካሄደበት መሆኑንም አስታውቀዋል።
በሙስና የተካሄደውን ግምገማ አስመልክተውም ኮሚቴ መመስረቱን ጠቁመው፤ በአሉባልታ ደረጃ የተነሱ ነገሮች ተጣርተው ህጋዊ ዕርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቶ መሠራቱን ገልጸዋል። አመራሩም ይሁን በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ አባላቱ ከብልጽግና ጋር ለመቀጠል ከሙስናና ከሌሎች ህገ ወጥ ተግባራት እጃቸው ንጹህ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል።
‹‹ቀደም ሲል የኮንነውን፣ እጅግ በጣም የተጠየፍነውንና የታገልነውን ዝርፊያ በኢትዮጵያም በኦሮሚያም ክልል እንዲቀጥል ስለማንፈለግ የብልጽግና ፓርቲ አባልና አመራር እጁ ንጹህ መሆን አለበት›› ያሉት አቶ ታዬ፣ ‹‹በአመለካከቱም ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች፣ ክልሎችና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያም ታማኝነትና እምነት ሊኖረው ይገባል›› ብለዋል።ከእዚህ በዘለለ አመራር ሆኖ እስከቀጠለ ለዜጎች ክብር ባጎናጸፈ መልኩ በተሰለፈበት ተግባር አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል።
‹‹ጊዜያዊ እግድ›› ተብሎ የተወሰነውን አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ የሦስቱን አመራሮች ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩም፤ በአንድ መልኩ በኢትዮጵያ የዳበረው የፖለቲካ ባህል የመጠፋፋት፣ የመጠላለፍ፣ አንዱ ሌላውን ጥሎ የማለፍና መሰል ሁኔታዎች ይስተዋልበት እንደነበር በማስታወስ፤ ‹‹ጓዶቹ ለረጅም ጊዜ፣ በተለይም በአስቸጋሪው ጊዜ አብረው የታገሉ፣ ዋጋ የከፈሉ ናቸው›› ሲሉ ጠቅሰው፣ ስህተት ስለሠሩ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ዕርምጃ መውሰድ የግድ መሆኑንም አስታውቀዋል።ስህተታቸውን ግለሂስ አድርገው ጉዳያቸው በወንጀል የማያስጠይቅ ከሆነ ወደ ፓርቲያቸው መመለስ ዝግ እንዳልሆነም አስታውቀዋል።
የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በምዕራብ አርሲ ከተፈጠረው የህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደምና የሰላም መደፍረስ ጋር ተያይዞ ወይዘሮ ጠይባ በታችኛው ከመንግሥት መዋቅር ጋርም ስማቸው እንደሚነሳ አቶ ታዬ ጠቅሰዋል።የሚደረጉ ማጣራቶችን ተከትሎ የሚገኝ ውጤት ካለ በህግ እንደሚጠየቁም አስታውቀዋል።‹‹ከላይ እስከታችኛው መዋቅር ያለ አመራር የህዝብን ደህንነት መጠበቅ ኃላፊነቱ መሆኑን ማወቅ አለበት።ኃላፊነቱ የሚለካው ችግር ሲፈጠር በችግር እራሱ አለመሳተፉ ብቻ ሳይሆን ችግሩ እንዳይፈጠር፣ የዜጎች ሰብዓዊ ክብርና መብት፣ የንብረት ማፍራት፣ የመንቀሳቀስ መብት እንዳይገደብ ጥበቃ ማድረግንም ይጨምራል።ያንን ኃላፊነት መወጣት ያልቻለ ተጠያቂ ይሆናል›› ሲሉም ጠቁመዋል።
በእዚያው ልክ ሁሉም ሥራውን አውቆ መሥራት እንዳለበትም አመልክተው።እንደ ብልጽግና የምንሠራው በአንድ በኩል ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የተጀመረውን የብልጽግና እና የልማት ጉዞ ማሳለጥ መሆኑንም አብራርተዋል።ህብረተሰቡንም ከጸጥታ ስጋት መከላከል፤ ህግና ስርዓት እንዲከበር ማድረግ፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው በነፃነት ወጥተው እንዲገቡ ማስቻል፣ ይህንን ተልእኮ ማስፈጸም የእያንዳንዱ አባል ግዴታ መሆኑንም አስገንዝበዋል።ከተልእኮ ውጪ የሆነ እንደሚጠየቅም አሳስበዋል።
መዋቅሩን የማጥራት ሂደት የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች በታችኛው እርከንም ግምገማ ተጀምሯል።ችግሩ በተፈጠረበት፣ የዜጎች ህይወት በጠፋበት፣ ንብረታቸው በወደመበት ኃላፊነታቸውን ባልተወጡና በጥፋቱም ተሳታፊ በሆኑ የጸጥታ አካላት ጉዳያቸው ተጣርቶ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራቸውን አስታውሰዋል።በአመራርነትም ደረጃ በርካቶች ኃላፊነታቸውን ባለመወጣትና በመቀስቀስ እስከ ከንቲባ ደረጃ ተጠርጥረው የታሰሩ፣ የተጠየቁ መኖራቸውንም አመልክተዋል፡፡
አሁን በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የተጀመረው ግምገማ ቀጥሎ ወደ መካከለኛና እስከ ቀበሌ አመራ ደረጃ ይወርዳል።ያለው ችግር፣ በተለይም ሌብነቱ የቀበሌ መታወቂያን በሽያጭ እስከመሸጥ ይደርሳል፣ አገልግሎትን እስከ መሸጥ እስከ ተራ ሠራተኛ የደረሱ በመረጃ ደረጃ የሚደርሱን ችግሮች አሉ፣ እነዚህን ደረጃ በደረጃ አጥርቶ ፓርቲውን ሙሉ ለሙሉ በማፅዳት ይዘልቃል ብለዋል፡፡
(ኢፕድ)

1 Comment

 1. .It is very sad to the people of Ethiopia to continue to be victims of the very cynical and criminal ruling elites who have totally messed up the very social, moral, cultural. ethical, spiritual fabrics or values for about three decades and continued to do so.
  .It is deeply painful that the very stupid cadres of the ruling gangs such as Taye Denda throwing up the very nasty political propaganda over and over and over again without any common sense of shame !
  .It is so disturbing to hear this kind of extremely trash political hypocrisy and conspiracy while innocent citizens are murdered in unbelievably horrible manner and many of them left with nothing but despair and hopelessness!
  .It is painfully brutal to to keep playing a deeply nonsensical political orchestration in this very moment of inhuman action against innocent people in which members of the so called Prosperity party have participated both in terms of spreading hate propaganda and actions !
  . It is deeply disturbing to hear those cadres of EPRDF/Prosperity who themselves were active participants of politically motivated crimes for a quarter of a century and continued with a much more criminal way of doing politics blaming TPLF(their mentor) as if they were and are immune from!
  . Like it or not, a system that was built and continue to operate on the very basis of ethnic political identity , not ideas and policies will never be the an agent of peace and prosperity ! It will be good for you guys to get out of the criminal political system of three decades and create a situation in which a true transformation could take place !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.