“በኢትዮጵያዊነቴ ሁሌም እኮራለሁ…” ኦባንግ ሜቶ

Obang“ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼን እና እትዮጵያዬን በፍጹም ልቤ እወዳለሁ።ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ሆይ:- እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ፣አንዱ ለሌላው አክብሮት ፣ ዋጋ እንዲሰጥ እና ሰብአዊነትን እንዲያሳይ እጠይቃለሁ።ይህ ማለት ደግሞ በኢትዮጵያ ስለሚኖሩ ለዘመናት ለተረሱ እና አናሳ ለሆኑ ወገኖች ሁልጊዜ በግልጽ የመቆም አላማው ማለት ነው።
እኔ እሰተዳደጌ እና በእግዚአብሔር ፍቃድ መፈጠሬ ፣የእርሱን ህይወት የማግኘት ጽኑ የግል እምነቴ ፣የቱንም ያህል ባጠፋ ፍቅሩ ሳይለየኝ፣ስብራቴን፣ቁስሌን በሙሉ የሚጠግንልኝ፣ለጥፋት የሚመጣብኝ ክፉ ኃይልን ወደ ነጻነት የሚለውጥልኝ፣ሀሰተኛ ከሳሾቼን በሙሉ እንዳሸንፍ እረድቶኛል። ኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ ሰው መሆኔ ያኮራኛል።
የቱንም ያህል እንኳን በብሔር ተኮር ፌደራሊዝም እና ዙሪያ ገባው ብሔር ተኮር በፖለቲካ ውስጥ ብኖርም እራሴን ኩሩ ኢትዮጵያዊ አድርጌ ስጠራ ትልቅ ክብር ይሰማኛል። መሰዋት በመክፈል የራሴ የሆነ አገር እንዲኖረኝ እና ኢትዮጵያዊ ተብዬ እንድጠራ የሚያስችለኝ መብትን እንዳግኝ ላበቁኝ ውድ ኢትዮጵያዊያን አባቶቼ እና እናቶቼ ዘለአለማዊ ክብር ይገባቸዋል።
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር…!!!”
(የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ፣የትብብር እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ካሰፈሩት በከፊል የተወሰደ)
/ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ/

1 Comment

  1. OBANG METO,

    What a great individual!!!! I am always proud of you and appreciate what you do to help fellow Ethiopians subjugated by their own government and ethnofascists.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.