ዝም አንልም – ከአባዊርቱ!!!

OLF 2የንፁሀን ደም ይጮሀል፣ እነ ጁዋር ፍርዳቸውን ያግኙ ዘንድ ዝም አንልም ።  የንፁሀን ድምፅ፣ በልፈታቸውም ፣ በህይወት የተረፉትም፣
አያስተኛም
አያስበላም
አያሳርፍም!
በአገራችን አሰቃቂ ግፍ ተፈፅሞ የዖሮሞ ወገኖቼ በውጭው አለም ጩኸትና ዋይታ ግራ ገብቶኛል። የሚጮኸውና የሚለቀሰው ደግሞ በግፍ ስላለቁት ወገኖች ሳይሆን ለጁዋርና በቀለ አይነቱ ከሀዲያን ደግሞ ሲሆን ጨርቅ አስጥሎ ሊያሳብድ ይከጅላል። ምን ጉድ ነው የመጣው በአገራችን? ነፍሰጡር፣ አዛውንት እየታረዱ ማንን ለመሸንገል ነው ጩኸቱ?
የአቃቢት ጄኔራልስ መግለጫ ምነው ቀዘቀዘ?
በውጭውስ የፅልመትን መንጋ ጨርሱ ብለው ወደ ህዝቡ ያስፈተለኳቸውን አውሬዎች የሚከታተል የጠበቆች ጉዳይ ከምን ደረሰ? ማስረጃ ነው ገና እየፈለግን ያለነው እንዳትሉና የባሰ አታሳዝኑን እንጅ ። ይህን ወንጀል የሚያቀናጅ መንግስት ጉልበቱን ቢያጣ ሙያተኞች እንደምን አስቻላችሁ? መዋጮ መጠየቅም ይቻላል እኮ። በቃ በየቤት እንደተላቀስን ዝም ሊባል ነው አሁንም እንደ ባለፈው ጥቅምቱ?
ክብርት አቃቢት ጄኔራል ሆይ!
አውቃለሁ የፍርድ ሂደቱ እየተካሄደ መሆኑን። ቢፈቀድልኝ በብሪፉ ጉዳይ መዘናጋት እንዳይኖር ነው። የሚያንዣብቡት ብዙ የአገር ጉዳዮች ስላሉ በየ ቀኑ እንኳ ባይቻል በየሰልስቱ ብሪፊንግ ህዝባችን ይፈልጋል – ከርስዎ መ/ቤት ካልተቻለ ቢያንስ ከ አቶ ንጉሱ አካባቢ። ከባለፈው ብሪፊንግ በሁዋላ እየሾለኩ የሚወጡ ሰቆቃዎች እንቅልፍ ይነሳሉና ነው። እንዲህ እያደረጋችሁ አቅጣጫ ካላስቀመጣችሁ በወሬ የተፈታው አገር መጨረሻው አያምርም። በውጭው የአገሪቱን ነፍሰገዳዮች መሪዎችና አስተባባሪዎች ላይ ምን አይነት አቅጣጫ ተቀምጧል? ይህ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ለምን? እነሆ ጩሀታችንን ቀሙ ሆኖ የጁዋር አሽቃባጮች ፍትህ ለገዳዮች እየጠየቁ ነው። ከዚህ በላይስ ሞት ምናለና ነው?
ኢትዮጵያ ከዖሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ ይሁን ማንም በላይ ናት!
እኔ እዚህ አነሳዋለሁ ፣ ህሊናዬን እያስጨነቀ ከሚያመኝ። የመከላከያው ሚኒስቴር ኦቦ ለማ ዝምታ ወገን እንዲህ አልቆ፣ ያኔም በጥቅምት አሁንም በሰኔና ሀምሌ በጭራሽ ልረዳው ያልቻልኩት ነገር ነው። በቦታው ከሌለ የለም ይበለን መንግስት። አለበለዚያ ምንድነው ዝምታው? The silence is deafening ይላል ፈረንጅ። ችግራችንን እንደ ሀገር በግልፅነት በመግለጫ እየተናበብን ካልሄድን ችግር እንኳ ቢኖር ነገርዬውን አስከፊ ያደርገዋል እንጅ ዝምታው መፍትሄ አይሆንም!!!
ወዴት እየሄድን ነው?!
ሌላው መልስ የሚሻ ጉዳይ የህውሀት የጦርነት ድንፋታ ነው። እሺ፣ የዶር አቢይን ” በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት አልከፍትም፣ ሰዎቹ ህዝቡን ምሽግ አድርገዋልና” የሚሉትን አባባል እጅግ አደንቃለሁ፣ እደግፋለሁም። ሆኖም ብቻውን በቂ አይመስለኝም። ለምን? ሰዎቹ ገፍተው ጦርነቱን ሸገር መሀል ወይም ዳርዳሩን ከጀመሩትስ? ምን ሊደረግ ነው? ለነገሩ እነሱው በቅጥረኞቻቸው ያስጀመሩልንን ስምሪት መጥፎ አዝመራ ነው በሻሻመኔና አካባቢው እየተቋደስን ያለውና በግልፅ መች ይወጉንና። ስለሆነም እንዲህ አንድ በአንድ እስኪጨርሱን ነው የምንጠብቀው ወይስ ምን አይነት ስትራቴጂ አለን እንደ ሀገር? አስጨናቂ ነው ያገራችን ጉዳይ። ምን ይሻለናል?ወይስ በቃ ፅልመቶቹ ሰመረላቸው፣ እንደ ህዝብ ተለያይተናል ብለን አምነን ተቀብለን ቁጭ ብለን እንለቅ? ምንድነው በማይረባ ነገር ወገን እርስ በርስ ተለያይተን የፅልመት መንጋ እንዲህ ይጫወትብን? ስለዚች አገር አለማወቅ ወይም የልጅነት ትዝታ አለመኖር እንደ እድል የሚታይበት ዘመን መድረሳችን እጅጉን ልብ ያደማል።
EegSXWoWkAATU2J

2 Comments

 1. ትክክል ነው አባዊሪቱ! ጥያቄዎትን ብዙ ህዝብ እንደሚጋራዎት ነው የምጠብቀው፡፡
  ጃዋር የሚሉት ዲያቢሎስ ህግም አያስፈልገውም ፀጉሩን በብርጭቆ ስባሪ ላጭቶ ክርቸሌ የግድ ይለዋል፡፡ ጊዜና ገንዘብም ማጥፋት የለብንም፡፡ አገር እያመስ ሊቅጥል አይችልም፡፡ እንደዚህ ሞት የቀለለበት ዘመን ደርሰን የህዝብን ዋይታ የማይሰማ መንግስት እጅጉን ያሳዝናል ያሳፍርራልም፡፡ የአቢይ መንግሥት ዛፍ መትከል ነው የበለጠበት፡፡ እውነቱን ለመናገር የጠ/ሚኒስትሩ የመሪነት ኃይል ይኑረው አይኑረው የሚያሳስብ ደረጃ ነው ያለነው፡፡ደካማ መሪነቱ ብዙ ቀዳዳ ክፍቶ እዚህ ሁሉ ጥፋት ላይ አድርሶናል፡፡ አሁን መንቂያው ሰአት ነው ብዬ ተስፋ አደርጌ ነበር፡፡
  ህግ አልባ የሆኑትን ወንጀለኞቹን ያሳዩናል እኮ! ሲዝቱ የህዝብን ሰላም ሲያቃውሱ እፊት ለፊት ካሚራ ላይ ወጥቶ የሚደነፋ ወንጀለኛን ማንቁርቱን እያነቀ እስር ቢት የሚያስገባ የጸጥታ ሃይል እንዴት የለም?? ማን ነው የልብ ልብ የሚሰጣቸው ከበስተጅርባ?

 2. አባዊርቱ ደግ ብልሃል !የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ላይ ይታወቃል ይላል የሀገሬ ስው!ጆሮ ያለውየሚስማ አእምር ያለው የሚያስተውል አይን ያለው አጥርቶ የሚያይ መሪ ክፉዘመን ሆኖ እማማ ኢትዮጵያ የላትም!ትውልዱም እንዲሁ የአእምሮ በሽተኛ አውሬ ውግዚአብሔርን የማይፈራ ገዳይ ሌባ ቀማኛ በተለይም እሮምያ ሆኑዋል ማለት ያስደፍራል በጅምላ ባይሆንብኝ!
  እየገዙን ያሉ ባለግዜ የኦሮሞ ባለስልጣን ብቃት አንሶአቸው አይደለም!ሁላችንም ስሞኑን የተለቀቀው አቶ ሽመልስ ምስጥራዊ ዲስኩር እውነታውን እየሆነ እየስሩት ያለው ሆን ብለው አዲስቱን በኦሮሙም የበላይነት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የህውሃትን ጭንብል ለብስው በዕቅድ አየስሩት መሆኑን ገልፀውናል!!ጁሀርም ኦነግም አውሬው ቄሮ መሳሪዎቻቸው ማደንዘዣ መድሀኒታቸው ህውሀት አድርገው በህውሀት እያሳበቡ እንጅ ባታምኑኝም ህውሃት እጁ የለበትም!አቶ ሽመልስ ሁሉን ነግሮናል ቄሮ ፈጣሪም አዛዥ እንደሆኑ!
  ዛፍ የሚቱክሉት አባይ አባይ የአዲስ አበባ ፕሮጀክት የአብይ ወይም የኦሮሞ ብልፅግና ማደንዘዣ ነው ሽመልስ እንዳለው እያደነዘዙን ነው!
  ኢትዮጵያ በታሪክ እንደዚህ አይነት አስመሳይ መሪ ገጥሞን አያውቅም ካልተሳሳትኩ!ዴር አብይ ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልምህሳቤ ስራዊቱ አልታዘዝኩም ሽፋን ወገኖች እየታረዱ ነው!በዚህ አይነት ጭካኔ ባይሆንም በኦሮምያ ክልል በሌላው ክልል ላይ የሚደረገውን መፈናቀል ሆነ አነስተኛ ይፈልጉታል ብዬ አስባለሁ !መረጃዬም የሸመልስ ንግግር ነው!
  አባዊርቱ!በንፁህ ህሊና እናስብ! አት እስክንድር ላይ ዶር ያን ሁላፉከራ ዛቻ ማሳደድ ማስር በሀስት ለምንአስፈለገ? የአዳነች አቤቤ ትዝብትና ቅሌት የሚጥል ዲስኩር ውንጀላው ለምን?ለምንስ ከእስክንድር ጋር አመሳስለችው?እራሱ ጁሀር እየተናገረ !ታድያ ለምን?መልሱ ሽመልስ ነገሮናል!
  አብይ የስኔ 15 ጉዳይ ሁኔታስ? ስራዊት እንዴት ቀድሞደረስ?የአብይ መገኘት በባህርዳር ለምን ተሽፈነ?የvoa ጋዜጣኛ ለአቶ ንጉስ የጠየቃቸው ነገር ቢኖር የስራዊቱ በዛ ቅፅበት ተገኝቶ እንዴት መፈንቅሉ አከሽፈ? ብሎ ሲጠይቃቸው መልስ አልስጡም!
  በፋኖ ላይ የአማራን አርሶ አደር ትጥቅ ለማስፈታት በሚል አእላፍ ስራዊትና ታንክ መላክ ለምን አስፈለገ?በኦሮምያ ለምን በኦሮምያ ሊሆን አልቻለም?
  ከዚህ ወጣ ስንልም ለንፅፅር አቶ ሙስጠፌ የስሞኑን ንግግራቸውና የሚመሩትንክልል ህዝብ እንዴት ስላሙን እድገቱ እየጠበቁለት እንዳለ አምና በቦታው ተገኝቼ አረጋግጬአለሁ ፍፁም ኢትዮጵያዊ እውነተኛ ስው ናቸው! እንደ እነዚህ ያሉ መሪዎች ወደ ፊት መጥተው የኢትዮጵያ መሪ እስካልሆኑ ድረስ አቶ ሽመልስ እንደነገሩን የቁማሩን ጨዋታ የተጫወቱ አገሪቱዋን ያጠፎታል!አመኑኝ አብይ ወይም ኦሮሞ ብልፅግና እየቆመሩ ነው!እናም እነ አብይን በአንቀልባ ይዘን እሽሩሩ የምንልበት ፈፅሞ አማራኝ እደሌለን ተቆጥሮ መሆን የለብትም!ቢያንስም በተክሄደው ጄኖሳይድ ተጠያቂ ነው የኦሮሞ ብልፅግና!!
  ሌላው ይህ ዘርን ማዕከልያደረገ ያለ ህዝብ ፈቃደ በወያኔ ና ኦነግ የወጣ ቤተሙከራ ጄኖሳይድ በቄሮ ያደረገን መንግስት እስካልተወገደ ድረስ ስላም አይኖረንም
  አባዊርቱ !ባለፈው ከአቶ ስርፀ ጋርኦሮሞ በሚለው ሙግትክን አንብቤ ነበር !አቶስርፀ እውነታ ያለው ይመስላል!ለምን ብትል እኔ በአደኩበት ክልል ስው ራሱንበጎሳ የሚጠራው ‘ ኢቱ ; ቆቱ : ኖሌ እያለ ነው እንጅ ኦሮሞ ነኝ አይልም!እኔ በሴት አያቴ ‘ ኢቱ’ ነኝ

  እግዚአብሔር ስላሙን አብዝቶ ይስጠን!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.