ኢትዮጵያዊያንን ለመታደግ የኢትዮጵያዊያን ወቅታዊ ሥራችን ልናደርገዉ የሚገባዉ

ethiopiaቀን 27/11/2012ዓ.ም

ምዕራብ አዉሮፓዊያን አፍሪካን ተቀራምተዉ ህዝቡን በባሪያነት ለመግዛት ዓልመዉ ሢሠሩ ዓላማቸዉን የአከሸፈችዉ ኢትዮጵያ መሆኗ ግልጽ ነዉ፡፡በዚህም የጥቁር ዓለም ሕዝብ መመኪያ እና የአፍሪካ የነፃነት ቀንዲል እንድትሆን አስችለዋታል፡፡ይህን ድል ግን ድል ተመችዎች በበጎ አላዩዋትም፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ጊዜዎች በግልጽ እና በስዉር ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ኢትዮጵያ ለማጥፋት ተደጋጋሚ ጥረት አድርገዋል፡፡

ከአደረጉት ጥረት አንዱ እስ በሱ ሥጋን በኩበት ጠበሱ እንዲሉ የባንዳ ልጆችን አሰልጥነዉ እና አደራጅተዉ በብሄር ነፃነት ስም ዐማራዉን በገዥነት፣ በጨቋኝነትእና በነፍጠኝነት ፈርጀዉ እሱን በማጥፋት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ አደረጉ፡፡ የዚህ ዓላማ ግብ ዐማራዉ በሁለንተናዊ መልኩ ከተዳከመ ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል አትችልም፡፡ትበተናለች፡፡ በዚህም የምዕራባዊያን ፍላጎት ይሳካል የሚል ነዉ፡፡

ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቅድሚያ የሥልጣን ምንጭ የአንድነት ምልክት የሆነዉን ዘዉዳዊ ሥርዓት ርዕዮተዓለማዊ ክንድ የሆነዉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ዐማራ የተሰኘዉን ነገድ ማጥፋት እንደሆነ ሰበኩ፡፡ አስተማሩ፡፡ይህ ሂደት ባለፉት 60 እና 70 ዓመታት በስፋት በመሥራት ይኸዉ እና ዛሬ ዘዉዳዊ ሥርዓቱ ፈርሶ ሊያንሰራራ ከማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ሃይማኖቱ የነበረዉን ሥልጣን እና ተሰሚነት አጥቷል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ዉስጥ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰዉ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም ፡፡ ዐማራዉ በኢትዮጵያ የመኖር ዋስትና አጥቶ በደቡብ በደቡብ ምዕራብ የመኖር ዋስትናዉን ተነጥቆ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ጽዳት ወንጀል ተፈጽሞበታል፡፡ በዚህ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማራ ተገድለዋል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፡፡

ሰሞኑን የኦሮሞ ጽንፈኖች ለዘመናት ቀድሞ የአቀዱትን ዐማራን ኦርቶዶክስ ተዋህዱ ሃይማኖትን የማጥፋት እና ኢትዮጵያን ኦሮሙማ የማድረግ ዓላማ በሀጫሎ ሁንዴንሳ ግድያ ስበብ ተደርጎ በዝዋይ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በአዳሚቱሉ፣ ዴራ፣ አጋርፋ፣ ባሌ ወዘተ ማንነትን እና ሃይማነትን መነሻ በማድረግ በዐማራ እና በኦርቶዶክስ ተዋህዱ ሃይማኖት ተከታይዎች ላይ ያነጣጠረ ፍጅት ተፈጽሞአል፡፡ይህን ድርጊት በስሙ ላለመጥራት ጥረት ሲደረግ ይስተዋላል፡፡ይህን የዘር ማጥፋት መግለጫ የሆነዉ ክህደት ነዉ፡፡ ክህደት ደግሞ ለሌላ ዙር ፍጅት ከመጋበዙ ሌላ እዉነተኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ይህን ፍጅት በሰሙ በመጥራት ዳግም የዘር ፍጅት እንዳይፈጸም ለማድግ ከመጣር ባሻገር የዘር ማጥፋት ዓለም አቀፍ ወንጀል የፈጸሙ ወንጀለኞች ለፍትህ እንዲቀርቡ ማድረግ የዕለት ተግባራችን ልናደርግ ይገባናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ተፈታታኝና ወጣሪ ሁኔታ ኢ.ሕ.አ.ፓን መተንኮስ ለምን አስፈለገ? (ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!)

ኢትዮጵያን ለማጠፋት የተሰለፉ ኃይሎች ይኸዉና ባደራጇቸዉ እና በመሯቸዉ የነገድ ነፃ አዉጭ ድርጅቶች አማካኝነት በዐማራ እና በኦርቶ ዶክስ ሃይማኖት ላይ የከፈቱት የጥፋት ዘመቻ ወደ መጨረሻ መድረሻቸዉ እያመራ እንደሆነ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተባለዉ አካባቢ የተፈጸመዉ የማንነት እና የሃይማኖት ፍጅት በግልጽ ያሳያል፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ ዐማራን ማጥፋት ብለዉ ዓልመዉ እና ተደራጅተዉ መጀመሪያ የተሰለፉት የባንዳ ልጆች እና የልጅ ልጆች እነመለስ ዜናዊ ናቸዉ፡፡መለስ እና ቡድኖቹ ኢትዮጵን ለማጥፋት የነደፉት መርሀ ግብር ከግብ ለማድረስ የተጠቀመበት ሥልት ዐማራን እና ኦሮሞን እሳት እና ጨድ አድርጎ እየቆሰቆሱ በማያያዝ ዓላማቸዉን ከግብ ማድረስ ነበር፡፡

ለዚህም የኦሮሞ አድርባይዎችን በግንባር ወያኔዎችን በጠባቂነት በጀርባ አሰልፎ ሰርቷል፡፡ መለስ ዜናዊ ለተከታይዎች አበክሮ እና አጠንክሮ በመመሪያ ያስተላልፍ የነበረዉ ዐማራ እና ኦሮሞ አንድ የሆኑለት ድርጅቴ ህወሀት ያልቅለታል የሚል ነበር፡፡ ስለዚህ ከካቢኔዎች እሰከ ደህንነቶች የአሉት ሁሉ የመጀመሪያ ስራቸዉ መሆን የአለበት በተለያየ ቦታ እና ሥልት ዐማራ እና ኦሮሞ አንድነት የማይፈጥሩበትን ሥራ መሥራት ነዉ፡፡ለዚህም ሥራ ብቁ አድረጎ የመረጠዉ ደ/ር ገብረ ፅዮንን ሲሆን ሲሞትም የማጣላት ስራዉ እንዲቀጥል ተናዞለት በዚህ ሥራዉ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡የነመለስ ዜናዊ ሕዘብ ከሕዝብ ማጣላት፣የህገመንግስት መጣስ፣ሕዝብን ያለጥፋት እየአሰሩ መደብደብ፣ሽባ ማድረግ፣ መግደል፣ ንብረት መዝረፍ ወዘተ ሥራቸዉ የአንገፈገፈዉ ኢትጵያዊ ሁሉ ተረባርቦና ተጋድሎ የአመጣዉን ለወጥ አክሽፎ የወያኔን ሥርዓት ለመመለስ በሚከተሉት ሥራዎች ተጠምደዋል፡፡

1ኛ ከኢትጵያ ታሪካዊ ጠላት ከሆችዉ ግብፅ ጋር በማበር የዐባይን ግድብ እንዳይገደብ ማድረግ፤በኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት እንዳይኖር ማድረግ፣

2ኛዐማራ እና ኦሮሞ እሳት እና ጭድ ሆነዉ በአጥፊ እና ጠፊነት እንዲቆሙ በማድረግ ወያኔ ወደፖለቲካ ማማዉ እንዲመለስ የሚቻለዉን የጥፋት ተግባር ሁሉ መስራት ናቸዉ፡፡ አይሆንምን ትተሸ ይሆናልን ባሰብሽ እንዲሉ የባንዳ ልጆች የጀመሩትን የማፍረስ ሥራ ወደ መጨረሻዉ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን አጢነን ኢተዮጵያ እንደ አገር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንደሃይማኖት ዐማራ እንደ ዐማራነቱ ተጠብቆ መዝለቅ አለባቸዉ የምንል ወገኖች ከምንጊዜዉም በበለጠ በአንድነት ተጠናክረን መሥራት የሚጠበቅብነ ዛሬ ነዉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም

ሙላት በላይ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.