በአዋሽ ወንዝ መሙላት ምክንያት በአፋር በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል

አብመድ
የአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ኩልሱማ ሩሃባ በተለይም ለአብመድ እንደገለጹት የጎርፍ መጥለቅለቅ በዝናብ ወቅት የሚጠበቅ ቢሆንም ዘንድሮ ግን በአዋሽ ዳርቻ በሚገኙ ወረዳዎች ላይም ጎርፍ እየተከሰተ ነው፡፡ በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅም ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ዝናቡ በዚሁ ከቀጠለ ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው ተለይተዋልም ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችልም ነው የጠቆሙት፡፡
117121623 1640226092809964 3118827842167869359 o.jpg? nc cat=109& nc sid=8bfeb9& nc ohc=nPi9SHHr8VEAX8vOd5m& nc ht=scontent otp1 1
በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሰው ሕይወት አለመጥፋቱን የተናገሩት ወይዘሮ ኩልሱማ፣ ነገር ግን ነዋሪዎቹ በብዛት አርብቶ አደር በመሆናቸው በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተጎድተውባቸዋል ነው ያሉት፡፡ አስቀድመው ሰውነታቸው የተዳከመ በርካታ እንስሳት በዝናቡ መክበድ ምክንያት መሞታቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡
በጎርፍ መጥለቅለቁ 16 ወረዳዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የተናገሩት ምክትል ኃላፊዋ አሁን ላይ በሰባት ወረዳዎች ጎርፍ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሲሰራ እንደቆዬና በቂ ነው ባይባልም ለተጎጂዎቹ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ለፌደራል መንግሥት የድጋፍ ጥያቄ እንዳቀረቡና ድጋም በአስቸኳይ እንደሚላክላቸው ቃል መገባቱንም ተናግረዋል፡፡
117327262 1640226396143267 3988911935415020493 o.jpg? nc cat=108& nc sid=8bfeb9& nc ohc=uZ5HUvatjVkAX BJvyi& nc ht=scontent otp1 1
በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከአካባቢው መውጣት ያልቻሉ ሰዎችን በሄሊኮፕተር በመታገዝ የማውጣት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዜጎችን በዘላቂነት ለመደገፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአደጋው ጊዜም ሆነ ከአደጋው በኋላም ርብርብ እንዲያደርጉ ወይዘሮ ኩልሱማ ጠይቀዋል፡፡
ተጎጂዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋምም የክልሉ መንግሥት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ሚትዮሮሎጂ በሚያሳዬው ትንቢያ ዝናብ እየጨመረ ይሄዳል ያሉት ወይዘሮ ኩልሱማ የወንዙ የመሙላት መጠኑም እየጨመረ እየሄደ ነው ብለዋል፡፡ በሚደረገው የአስቸኳይ እርዳታ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ተጎጂ እንዳይሆኑና ለውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይጋለጡ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.