‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!›› ፀ/ትፂዮን ዘማርያም

ET 89

‹‹የክልል ልዩ ታጣቂ ኃይል ይፍረስ፤ በዘር ተደራጅቶ፣ በዘር የታጠቀ፣ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል…!!!››

ያሬድ ሀይለማርያም

ኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው፣ ሸነሸነው፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስት ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት እየጣረ ይገኛል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ለስልጣኑ ሲል ሃገር በማፍረስ  ሠራዊቱን  ተባባሪ ማድረግ አልተቻለውም፡፡ ትግራይ ክልል የሚኖር የኢትዮጵያ ሠራዊት የወያኔ ተባባሪ አይሆንም የወያኔ መሪዎችን አስሮ ለፌዴራል መንግስት እንደሚያስረክባቸው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

‹‹የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ሰማይ በነካበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር ውስጥ በብሔር የተዋቀረ የክልል ታጣቂ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሻ ማደራጀት ማለት የተጠመደ ፈንጅ በጀርባ አዝሎ እንደመዞር ነው። ክልሎች በአገር ውስጥ ያሉ አገሮች ሆነው ተዋቅረዋል። በዛ ላይ አወቃቀራቸው ቋንቋና ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው። የብሔር ፖለቲካው እያመሳት ላለች አገር በብሔር የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች እያሰለጠኑ እና እያስታጠቁ በየክልሉ ማስቀመጥ ካየነው በላይ ብዙ ግፍ እንድናይ እና ኢትዮጵያንም በቀላሉ ወደ ዘር ተኮር ግጭት ከመውሰድም በላይ የአክራሪ ቦድኖች መፍለቂያነት እና ወደ ሽብር ቀጠና ሊለውጣት ይችላል። ከወዲሁም አንዳንድ ምልክቶች በግላጭ እየታዩ ነው፤

– በክልሎች መካከል ያለው ውጥረት እና ትከሻ መለካካት በየጊዜው ግጭቶችን አስከትሏል። አሁንም ተፋጠው፣ ጉድጓድ ምሰው እና ቃታ ስበው ለፍልሚያ ቀን የሚጠብቁ አሉ። ለዚህም የትግራይና የአማራ ክልል ፍጥጫ ጥሩ ማሳያ ነው።›› ይላሉ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም፡፡

የትግራይ ክልል ወታደራዊ ትዕይንት ባደረገ ማግስት በርካታ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ የታጠቀ ኃይል ወደ አማራ ክልል ድንበር በማስጠጋት አላማጣ፣ ራያ ቆቦ፣ ጨርጨር  አካባቢ እየሰፈረና ምሽግ በመቆፈር የጦርነት ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ወንድማማቾችን በጦርነት የማፋጀት የፖለቲካ ፖሊሲና ሴራ  በማጋለጥ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ  የኢትዮጵያን ጦር ለመቀላቀል ወደ አማራ ክልል እየገቡ እንደሆነ ታውቆል፣ ለዚህ ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!›› የሚሉት፡፡ ህወሓት /ኢህአዴግ በዘርና ቌንቌ በማካለል በአንድ ዘር ላይ የተዋቀረ የፖሊስ ኃይል፣  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ በማስታጠቅ በክልሎች መኃል የማያባራ የድንበር ግጭትና ጦርነት የሰው እልቂት፣ የንብረት ውድመትና በወንድማማቾች ጦርነት ደም በከንቱ ሲፈስ ቆይቶል፡፡

ወያኔ ኢህአዴግ ‹‹– በብሔር የተዋቀረ ጦር የብሔር ግጭት በተበራከተበት አገር ወግኖ ባይሰለፍ እና ከሱ ብሔር ውጭ ያለውን ወገኑን ባያጠቃም እንኳ ከጥቃት አያስጥልም። ምክንያቱም እሱ የሰለጠነው፣ የተማረው፣ የተነገረው እና የታጠቀው የራሱን ብሔር ሕዝብ ለመከላከል ብቻ ነው። ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተደጋጋሚ እንዲሁም በአንዳንድ ክልሎች አልፎ አልፎ የተስተዋለው ይሄው ነው። በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸመው ብሔር እና ኃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ የክልሉ ታጣቂዎች ጥቃቱን ከማስቆም ይልቅ በተለያየ ደረጃ ተሳታፊዎች እንደነበሩ መረጃዎች አረጋግጠዋል፤ መንግስትም መስክሯል። የክልሉ ታጣቂዎች ትዕዛዝ አልደረሰንም በሚል ጥቃቱን ቆመው አይተዋል፣ አንዳንድ ስፍራ ነዋሪዎች እራሳቸውን ከጥቃት እንዳይከላከሉም የነዋሪዎቹን ሕጋዊ መሳሪያ ከሰዓታት በፊት ቀድመው አስፈትተዋል፣ አንዳንድ ቦታ ለቄሮዎቹ መሳሪያ በመስጠት ጥቃት አስፈጽመዋል፤ እንዲሁም ለአጥፊዎቹ ከለላ መስጠት እና ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ የማድረግ ተግባርም ፈጽመዋል።እነዚህን መሰል ችግሮች እዛው ኦሮሚያ ክልልም ሆነ ሌሎች ሥፍራዎች ዳግም ላለመፈጠራቸው ምንም ዋስትና የለም።››

ከትግራይ ክልል መከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ ቃል ኪዳን የገባው ለኢትዮጵያ እናት አገሩ እንደሆነ በማወቅ   ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!››  በማለት ከትግራይ ክልል የወያኔ መሪዎች ሊጫር የታሰበውን የድንበር ግጭት በመቃወም ትግራይ የሚገኘው ሠራዊት ወደ አማራ ክልል፣ ወደ አፋር ክልል፣ ወደ ኤርትራ በሠላም እንዲገባና ለእናት ሃገሩ ታማኝነቱን እንዲያሳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቃልኪዳኑን እንዲጠብቅ፣ የሃገር ሃሌንታነቱንና የህዝብ ወገንተኛነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል እንላለን፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን እምዬ ኢትዮጵያን በባዶ እግራቸው ያለጫማ፣ ያለደሞዝና ያለ ዘመናዊ ጦር መሣሪና መጎጎዣና ያለስንቅና ትጥቅ ያቆዬት ሃገር መሆኖንና ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀው ደማቸውን አፍሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡህ ሃገር ከህወሓት በላይ ናትና እናት አገርህን ለሚያልፍ ዝናብ ብለህ አትክዳ እንላለን፡፡ መንግስታት ይሄዳሉ፣ ይመጣሉ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ  ሠራዊት ግን ዘላለማዊ ነውና፡፡

መቐለ የመሸገው ህወሓት መሪዎች የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማጋጨት፣ ደም ለማፋሰስ፣ የትግራይን ህዝብ አማራ ሊወርህ ነው ተነስ፣ አፋር በዚህ በኩል መጣል፣ ኤርትራ ጦር ሠበቀብህ እያሉ የሥልጣን እድሜቸውን ለማራዘም የአዞ እንባቸውን ሲያፈሱ አመታት ተቆጠረ፡፡ ህወሓት ለክልሉ ሠራዊት ደሞዝ የሚከፍለው  ቤሳቤስቲን ገንዘብ የለውም፣ የትግራይን ህዝብ ኃብት እየዘረፈ ውጭ ሃገር በልጆቹ ስም ቪላቤት ሲገዛ ከርመዋል፡፡ ወያኔ  በንዋይ ፍቅር ሃገር ሲበዘብዙና ዴሞክራሲ ለ27 አመታት ሲያፍን ሠንብቶ ዛሬ ምርጫ ካላደረግሁ ብሎ ይፎክራል፡፡ ወያኔ የትግራይ ህዝብ ንፁህ ውኃ፣ መብራት፣ ህክምና መኖሪያ ቤት ለመስራት  ወዘተ ነፍገውት በፍርሃት ሲገዙት ዘመናት ተቆጥሮል፡፡

ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን አልፈን አዲሲቶን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡ ‹‹መፍትሔ…!!!

1ኛ/ ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣

2ኛ/ በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣

3ኛ/ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣

4ኛ/ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

ክልሎችም ያንጃበበውን አደጋ ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች እጅ የወደቀ ዕለት የመጀመሪያዎቹ የጥቃት ኢላማዎች እነሱ መሆናቸውን ሊያጤኑት ይገባል። በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል። ይህን ለማድረግ ግን ወሳኙ ነገር የአገዛዝ ሥርዓቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ያንጃበበውንም አደጋ በበቂ ሁኔታ መረዳትን ይጠይቃል። ይሄን የተጠመደ ፈንጂ ሳያመክኑ በጀርባ አዝለው እየዞሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለት ብቻውን አደጋውን አያስቀረውም።›› የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ሊታደጉት ይገባል እንላለን፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ፣ ፈጣሪ ይርዳዎት፡፡

ምንጭ፡-

(1)  የክልል ልዩ ታጣቂ ኃይል ይፍረስ፤ በዘር ተደራጅቶ፣ በዘር የታጠቀ፣ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል…!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

EegSXWoWkAATU2J

የትናንቱ ውጊያ ከኮረብታው ላይ፣ ሲያውድ የባሩድ ሽታ፣
በዛ ቅዝቃዜ! ሆድ ሲንቦጫቦጭ፣ ሙቀት በብርድ ሲረታ፣
የጠመንጃ ጩኸት፣ የተኩስ እሩምታ ሰማየ ሰማያቱን ሲነድለው
በዛ ውጊያ የጦር ጀነራሎቹ ትክክል ነበሩ …ማን አለና?
ለባድማ መሬት ብሎ ሰው ይሞታል፣ ግን ለምን? እነሱም አያውቁማ!!!
ያመረቀዘ ቁስላችን፣ ለእነሱ ክብርና ኩራት ሆናቸው!!!
በባድማ! ያ ሁሉ የደሃ ልጅ ረግፎ፣ የአምስቱ የጦር መኮንኖቹ ሲሳይ፣
በሹመት ላይ ሹመት፣ በሜዳልያ ላይ ሜዳልያ፣ በበላይ ላይ በላይ፣
የእብደትና ህመም ደዌችንን፣ በእርግጥ ያውቃሉ ያሳለፉነውን ስቃይ፣
ታዲያ! ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ካጠፋ፣
የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ
ታዲያ ደውሉ የሚያቃጭለው ለማን ነው? ኩኩሉ ሳይል አውራ ዶሮው፣
የደሃ ልጅ የሆናችሁ፣የእናንተን ዕጣ ፈንታ ልንገራችሁ፣
ከመሞታችሁ በፊት፣ ቀኑን ተሠናበቱ፣ ሰማየ ሰማያቱን እያያችሁ፣
በመጨረሻ እስትንፋሳችሁ፣ ትሁን ንዛዜችሁ ለእናታችሁ!!!
ነፍሳችሁ ስታርግ፣ ትሰወራለች ቀስ ብላ ጥላችሁ፣
በድቅድቁ ጨለማ፣ በነጎድጎዳማ መብረቅ ሲርድ ሰማይ፣
ለተቀጨ ዓላማችሁ ብካይ፣ አጎሩ ለረገፈ መንፈሳችሁ ታላቅ ራዕይ፣
ነፍስ ረቂቅ ሚስጢር፣ እንግዳ ነገር ሆነች ዐይናችሁ ላይ፣
ፀጥታው ባርቆ ይሰማል፣ በዝምታ አድምጥ የልብህ ትርታ ካንተ ስትለይ፣
የብርሃን ጨረር ፈንጥቃ ለስንብት፣ በዚህ ዓለም ከተስፋ ሌላ አረ ምን ሊታይ?
ሞታችሁን ባናይ እንኳን፣ ያዩት ይመሰክሩ የሌት ጨረቃ የቀን ፀሃይ
የዓይነ ስውር ዓይን ሲበራ፣ ሞት በህይወት ልትረታ ትንሳኤ ላይ፣
ታዲያ እማማ፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ከገፋ፣
የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ
ድህነትና ርሃብ፣ በሽታና ሰደት ሳናጠፋ
በቌንቌ ተካለን፣ ማኛ ጤፍ ዘር ስንነፋ
ጦርነት አርግዘን ስናናፋ፣ ድንቁርናችን ምነው ከፋ
ዛሬም ወገን በወገን ላይ፣ በዘር ጦር ሰብቀን ስንነሳ፣
የባደማ ፆረና ሞት አልፈን፣ በወልቃይት፣ራያና አፋር ጦር ሜዳ ደንገላሳ፣
ታዲያ እማዬ ደውሉ የሚደወለው ለእኛ ሞቾች ነው? ትንቢተ ትንሣዔ ራቀ ምነው?
ጦርነት ‹መቼም የትም አይደገም!!!› ሳንል! መፈናቀላችን ስለምን ነው! ሰደቱንስ መች ለመነው?
የሰው ልጅን ከኃጢያቱ እንፈውሰው፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
(እኔና አንተ ለምናውቀው፣ በባድማ ጦርነት ለቀበርከው ማሙሽና፣ ለኩኩሻ መታወሻ ትሁን)
ለኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የጦርነት ሠማዕታት ትሁን!!! ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

1 Comment

 1. If holding an election is deemed to be an extremely dangerous Coronavirus health hazard as the Federal government says it is, then the federal government needs to take all measures even military actions to stop the election from taking place in Tigray.

  People of Tigray should not be exposed to the extremely dangerous CoronaVirus spread just because the federal government is scared to use military force now.

  If election is held in Tigray and if in the future the federal government tries to not acknowledge the results of this election by voiding the results of this election which the regional government is about to hold in Tigray, it is a recepie for an all our civil war which will bring huge losses in the future that is why currently it is highly needed to
  properly address it rather than just letting this Tigray election controversy go on without resolution. Also CoronaVirus does not have any boundaries, in notime the extremely dangerous spread of the CoronaVirus will travel to other parts of Ethiopia out of Tigray if this election will be held, bringing huge proportion of deaths in all parts of Ethiopia.

  That is why if the Federal government fails to stop the election in Tigray it shows that the Ethiopian federal government is weak unable to perform it’s duties and needs to form a stronger transitional or care taker government ASAP, a government who can better handle the duties of the federal government.

  Between the Oromia regional government’s Liyu Hayil and the Tigray regional government’s Liyu Hayil more than 75% of the total Ethiopian military personnel is accumulated, a huge increase percentage wise from just two years ago, the federal government needs to ask for Oromia Liyu Hayil’s assistance to stop the regional government of Tigray so the Tigray regional government will be forced to cancel the election knowing the federal government is not budging.But if the federal government fails to stop this election from being held in Tigray it would be the final straw for PM Abiy Ahmed’s administration, history will remember him for his failures .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.