የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ! 

ሁሉንም የፖለቲካ ሀይሎች ያላካተተ ውይይት ሲጀመር የከሸፈ ነው::  ከቶውንም አገራዊ  መግባባትን አያመጣም !!!
bALDERAS Hመንግስት ከሰሞኑ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚል የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ከመረጣቸው  /ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀልባቸው ከወደዳቸው/ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ንግግር ማድረጉን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ፖርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ተከታትሏል። በዚህም ጉዳይ ላይ ፓርቲያችን ተወያይቶ ተከታዩን ዕይታ እና አቋም ይዟል።
አገራችን ኢትዮጵያን፣ ወደ ብሔራዊ መግባባት እና ልማት ይወስዳታል ተብሎ በህዝባችን እምነት ተጥሎበት የነበረው ከ2010 ዓ.ም መጨረሻ የጀመረው የለውጥ ሽግግር የመቀልበስ አደጋ አጋጥሞታል። ትናንት የነበርንበትን ሁኔታ የሚያስንቅ ተረኝነት እና የዜጎች ሰላም ማጣት ውስጥ ገብተናል። በዓለም ሶስተኛ ታላቋ የዲፕሎማት ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ የህይወት መጥፋት እና ንብረት ውድመት ተጋልጣለች። ከትናንቱ ጉዳት ይልቅ የነገው ዕጣ ፈንታችን እጅግ ያሰጋናል። አገራችን በኦህዴድ/ብልፅግና ፓርቲ ዘመን፣ ዜጎች በላባቸው ያፈሩትን ሃብት በጠራራ ፀሐይ የሚያጡበት፣ ሴቶች የሚደፈሩበት እና ወንዶች የሚታረዱበት የምድር ሲኦል መሆኗን እየታዘብን ነው።
ከዚህ አሳዛኝ፣ አገራዊ እንዲሁም ትውልዳዊ ምስቅልቅል ውስጥ እንዴት መውጣት እንዳለብን ራዕይ አልባ የሆኑት ገዢዎቻችን፣ ትናንት የትህነግ ሎሌ የነበሩ እና ዛሬ ደግሞ ከመንግስት የሚሰጣቸውን አበል ብቻ የሚያስቡ የፖለቲካ አመራሮችን ፊት ወንበር ላይ አስቀምጦ የአገሪቱን ችግር ለመፍታት የተያያዘው ድራማ፣ የሽግግሩ ትልቁ ቀልድ ሆኖ አግኝተነዋል።
መንግስት በሃሳብ ገበያ ተወዳድሮ እንደማያሸንፈው የተረዳውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን፣ ሕግ ማስከበር ተስኖት በአዲስ አበባ ከተማ ለደረሰው ጉዳት በፈጠራ ወንጀል ያለአንዳች ማስረጃ ተጠያቂ ለማድረግ አመራሮቹን እስር ቤት በመከርቸም፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀልባቸው ከወደዳቸው ፓርቲዎች ጋር ብቻ ተሰብስቦ “ስለብሔራዊ መግባባት” ተወያየን መባሉ፣ ከመነሻው የከሸፈ ሂደት ሆኖ አግኝተነዋል። ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ልጆች መካከል ተለይቶ እንዳይሳተፍ መደረጉ፣ ዜጎች በማንነታቸው እና አመለካከታቸው ምክንያት በየቦታው በኦህዴድ/ብልፅግና ፓርቲ የሚደርስባቸው መድሎ ነፀብራቅ ሆኖ አግኝቶታል። ከሂደቱ መገለላችን ለአገራችን ሰላሟ የሚጠቅም እርምጃ ቢሆን፣ ፓርቲያችን በደስታ የሚቀበለው በረከት አድርጎ ይቀበለው ነበር። ነገር ግን ከ10 ሚሊዩን በላይ የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ልብ ውስጥ ያለውን ፖርቲያችንን በማሰርም ሆነ በማሸማቀቅ፣ የከተማውን እና የአገራችንን ችግር መፍታት እንደማይቻል የመጣንበት ሂደት በራሱ ይመሰክራል።
 በዚች አገር እውነተኛ ብሔራዊ መግባባት ለማምጣት ከተፈለገ፣  መንግስት የሚፈልገውን፣ የመሪዎችን ፊት እያዩ አቋሙን ከሚደግሙ ቡድኖች ጋር ሳይሆን፣ እንደ ባልደራስ፣ ለአገራችን የሚያስፈልገውን አማራጭ ከያዙ የህዝብ ድርጅቶች ጋር ለመነጋገር መንግስት ወኔው እና ቁርጠኝነቱ ሊኖረው ይገባል።
ከመጀመሪያውም፣ ብሔራዊ መግባባትን አጀንዳው አድርጎ የተነሳው ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፣ ከምርጫ በፊት እውነተኛ ብሔራዊ መግባባት ሊቀድም እንደሚገባ ሲወተውት ቆይቷል፡፡ አሁንም ለአገራችን የሚሻለው አማራጭ፣ በሃሳብ ከሚለዩን እና ከማንወዳቸው ኃይሎች ጋር ቢሆንም፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመሠረታዊ አገራዊ ጉዳዩች ዙሪያ ተነጋግሮ መግባባት ከመድረስ ውጪ አቋራጭ የሰላም መንገድ እንደሌለ  ፓርቲያችን አበክሮ ያሳስባል። ብዙ ዋጋም ተከፍሎ ቢሆን፣ ዞረን ዞረን የምንመጣው ወደ ድርድር መሆኑን አበክረን እንረዳለን፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አገራችን ከገባችበት ከፍተኛ ግጭት እና የፖለቲካ ውጥረት እንድትወጣ ከብሔራዊ መግባባት ውጪ አቋራጭ መንገድ የሌለ መሆኑን በመረዳት ተከታዩን ምክረ ሃሳብ ለመንግስት እና ለተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ያቀርባል፣
1ኛ. ከብሔራዊ መግባባቱ በፊት ካለማስረጃ የተያዙት የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ፣  አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም እና የፓርቲው አባል የሆነው ገነነው አበራ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣
2ኛ. በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ በቀኝም ሆነ በግራ የኃይል አሰላለፍ ውስጥ ያሉ ህዝብ የሚደግፋቸው የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ጥሪ ተደርጎላቸው የውይይቱ አካል እንዲሆኑ፣
3ኛ. ጉዳዩ የሚያገባቸው የሲቪክ ማህበራት እና የኃይማኖት አባቶች የሂደቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ እንዲደረግላቸው።
ከዚህ በተረፈ ግን መንግስት አሁን በያዘው አካሄድ እቀጥልበታለሁ የሚል ከሆነ፣ በአገራችን እውነተኛ ብሔራዊ መግባባት ካለማምጣቱም ባሻገር፣ ያለውን ፖለቲካዊም ሆነ የደህንነት ውጥረት የበለጠ እያባባሰው የሚሄድ መሆኑን ፓርቲያችን ማስገንዘብ ይወዳል።
            ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!
                        ሰኔ 27 ቀን 2012 ዓ.ም
                                   አዲስ አበባ

3 Comments

 1. “ከዚህ በተረፈ ግን መንግስት አሁን በያዘው አካሄድ እቀጥልበታለሁ የሚል ከሆነ፣ በአገራችን እውነተኛ ብሔራዊ መግባባት ካለማምጣቱም ባሻገር፣ ያለውን ፖለቲካዊም ሆነ የደህንነት ውጥረት የበለጠ እያባባሰው የሚሄድ መሆኑን ፓርቲያችን ማስገንዘብ ይወዳል።
  ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!”

  ማለትም እነ ጁዋርን፣ በቀለን፣ የብልፅግናን የውስጥ አርበኞች ፅዳት ፣ የአክራርያንንና ጨለምተኞችን ጉዳይ ሳተናዋ አቃቢት ጄኔራል የመዳኘቱን ሂደት ወይም አቢይ ከወገኖቼ ጦርነት አልሻም ምን ህውሀት ብትገፋፋኝ ያሉበቱ አካሄድ ማለታችሁም አይደል? እንድያ ይለይላችሁ እንጅ። እንግዲህ በዚህ አቋማችሁ ከመቀሌው ባይቶኔ ይሁን ሳልሳይ፣ ወይም ከአለቃቸው ህውሀት ምን ይለያችሁዋል? ይህ “በአስቸኳይ ይፈቱ” ቀጭን ትእዛዛችሁ ለዋናዋም የፅልመት ኤታማዦር ህውሀት ሳይበጅ ቀርቶ ሁለቱ ቱባ ባለስልጣናት መታሰራቸውን አልሰማችሁም ነበር? ። አገር እየፈረሰች ሲሆን በህብረትና ቅንጅት ምን እንርዳ የድርሻችንን መባል ሲኖርበት አሁንም ማስፈራራት? ቀሺሞች! መረራ ሆነ ዳውድስ አባሎቻችን ይፈቱ ከማለት ምን ብለው ኖሯል? ለምንድነው ህግ ይዳኝልን አባሎቻችንን ማለት የሚከብደው? የሚገርም ነው በውነቱ።

  • Abawirtu
   Here we go again “ሳተናዋ አቃቢት ጀኔራል” do you mean Adanech Abebe who gave 58 million bir of Ethiopian tax payer money to jawar’s omn so he can murder Ethiopians. You see hypocrisy is the mother of falsehoods. This is why balderas was targeted by abiy and Birhanu Nega combined. Everyone has a foot soldier so does abiy and Birhanu Nega, even though they are trying to put it under the rag. There is nothing wrong to tell like it is? Jawar was motivated and helped and financed by abiy’s opdo especially by Adanech Abebe. She was the one who enable Jawar to kill non Oromo Ethiopians. Lema megersa recruit and trained olf and kero thugs to join the Oromo lieu hayl and we saw the result as Amara genocide. How about Takele uma demolishing peoples house to change Addis Ababa’s demographic? Do I have to go on? Did we hear anything about amahara genocide and or Christian genocide by fanatic Oromo from abiy and his administration mouth? No, instead they arrested Eskinder Nega because he is an Amara but a defender of all addis residents. I don’t have enough space to mention other opdo fanatics like Shimelis abdisa. In all this abiy’s ear is blocked by what I don’t know. He became see no evil, hear no evil, speak no evil leader, for how long, time will tell. I am afraid people On the receiving end people are very sad and very angry. if and when they decide to start responding no one will be spared. So diminishing the victim and ignoring the glaring Truth will bring a lot of fire no one will have the ability to distinguish. On one hand admiring the sinister player “ሳተናዋ አቃቢት ጀኔራል” while hundreds of Amaras and Christians are murdered by her idol Jawar Mohammed’s followers, on the other people like you are against those who cry for the victims is amazing. All in all hiding Amara Genocide can not save either opdo, olf, tplf or abiy’s party itself. They are all responsible when judgment day arrive. I am confident sooner or later there will be a judgment day.

 2. PM Abiy Ahmed needs all the help he can get , he should accept the help they offered him to hold talks in a round table now before it is too late. PM Abiy Ahmed needs to join the national team , so far he played only for PP, same as the soccer player from St. George soccer club joins the national soccer team when it is time to do so, it is high time the Prime Minister takes the same type of step as a soccer player joins the national team .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.