ጋኔሉን የጠሩት ከብልቃጡ ውስጥ አሰሩት! ጅዋር‹‹የአባገዳዎች አባገዳ፣ስዩመ-ሜንጫ ዘአሩሲ!›› (ክፍል ሁለት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

Jawarየወያኔ፣ ኦነግ ሸኔና ጅዋር ህገወጥ  የሳተላይት መቀበያ የስለላ መሣሪያና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት!!!››
ያሰብከው ዓላማ አልሆን ብሎ ቢከሽፍ፤
ሁኔታው ሲጠጥር፤ ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን  ወጥር፡፡
(ኃይሉ ገብረዮሐንስ(ገሞራው)

በኢትዮጵያ ከወያኔ ወደ ኦነግ የዲጂታል ዘመን ባርነት በጁዋር ቄሮ አባ ሜንጫ!ኢትዮ ሳት ብሔራዊ ደህንነት ስጋት!

‹‹በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ኮሙኒኬሽን ሳይንስ ‹‹መረጃ›› ከዘይትና ወርቅ ማእድን ኃብት በላይ ዋጋ ያለው ሆኖል፡፡ መረጃ የዘመናዊ ኢኮኖሚ ነዳጅ ነው፡፡ መረጃ እንደማንኛውም ሸቀጥና የንግድ ዕቃ ነው፡፡ መረጃ እሴት ያለው፣ ዋጋ ያለው የሚሸጥ የሚገዛ ዓለም አቀፋዊ የሸቀጥ ሲሆን፣ ለሃገራት ስትራቴጅክ ኃብት ነው፡፡ በዘመናችን የዲጅታል መረጃ ንብረት ከማንኛውም የቁስ ሸቀጥ የበለጠ ሆኖል፡፡” Indeed, digital assets now matter far more than physical ones” በዓለማችን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ኮሙኒኬሽን መረጃን የተቆጣጠሩት አሜሪካና ቻይና ልዕለ ኃያል አገራት ለመሆን የቻሉት በመረጃ ኃብታቸው አማካኝነት ነው፡፡››https://zehabesha.info/archives/105500

ጅዋር መሃመድ በዚህ በመረጃ ቅኝ ግዛት ዘመን፣ የዲጅታላይዤሽን አንባገነንነት! (Data Colonialism and Digitalization Dictatorship) የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ከባህር ማዶ በመመሥረት ብዙ ተከታዬች በማፍራት የኦሮሞ ወጣቶች ቄሮ የእንቢተኝነት ትግልና የአማራ ወጣቶች ፋኖ አልገዛም ባይነት ትግልን አመራር ሰጭነት አንዱ በመሆን የወያኔ ኢህአዴግን ገናዥና ሥርዓተ ቀብር ቆፋሪ ነበር፡፡

 • ጅዋር በሃገር ቤት በዘረጋው የመረጃ መረቡ የአስራ ሁለተኛና የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናን ቀድሞ ይፋ በማድረግ የወያኔን የጸጥታና ደህንነት ሹም ጌታቸው አሰፋ፣  የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ዶክተር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ  የኢንሳ መረብ በመበጣጠስ ኪሳራ ያደረሰ   የተፈታተነ ምጡቅ የመረጃ ሰው ነው፡፡
 • ጅዋር መሃመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን)፣ የቴሌቪዝን ጣቢያ በመመሥረት የህወሓት ኢህአዴግ ሥልጣን በመሸርሸርና በማጋለጥ ትልቅ ሚና ተጫውቶል፡፡
 • ጁዋር መሃመድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ኮሙኒኬሽን መረጃ አገልግሎት ሠጪ እቃዎችን ወደ አገር ቤት በድብቅ ይዞ በመግባት የድርጅቱን የግንኙነት መረብ ብቃት በማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውቶል ለቄሮ አባሎቹ ያበረከተው ብዛቱ የማይታወቅ የእጅ የሞባይል ስልክ፣ ኦኪ ቶኪዎች፣ ላፕቶፕዎች ወዘተ ናቸው፡፡
 • ጁዋር መሃመድ ‹‹ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ!!!›› በማለት ለማ መገርሳ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ከማል ገልቹ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያው ሠበሰባቸውና አለቃቸው ሆነ!!!፡
 • ‹‹ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም›› የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)፣ ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኦብሳ፣ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያው አደራጃቸው!!!፡
 • ጁዋር መሃመድ በነደፈው ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያውን በገንዘብ፣ በወርቅ፣ በመሬት፣ በጦር መሣሪያና፣ በፀጥታና ደህንነት መረጃ ኃብት አሰባስቦ የኦሮሞ የክልልና የፌዴራል መንግሥትን ለመቆጣጠር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ነደፈላቸው፡፡
 • ጁዋር መሃመድ በአጭር ጊዜ የኦሮሚያ የገዳ አባቶችን፣የኦሮሞ ሚሊየነር ኃብታሞች ድንቁ ደያስ(የሶደሬ ሪዞርትና ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የሃገር ገንዘብ ዘርፎ አሜሪካ የኮበለለ)፣ አለማየሁ ከተማ (ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእራሱ ያደረገ ሙሰኛ በደረቅ ቼክ ወንጀል ተከሶ ኡጋንዳ ኮብልሎ የነበረና በምህረት ዶክተር አብይ ወደ ሃገር የመለሱት  በልጁ ስም አራት መቶ ሚሊየን ብር በብድር የወሰደ)፣ አቶ ገምሹ በየነ የኢሊሊ ሆሌል ባለቤት በዝርፍያ ና ሙሰኛነት ኮብል የነበረና በምህረት የተመለሰ፣ አቶ ዓለም ተፈራ  ወዘተ ጅዋር ኦሮሞ የሆኑ ሃብታሞቹን አስገብሮና በስሩ አደራጅቶ ለኦኤምኤን ገንዘብ እንዲያዋጡ በማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ ሰብስቦል ዋናው የገንዘብ ምንጩ አድርጎቸዋል፡፡ ነጋዴዎቹና ምሁራንም ገበሩለት፡፡
 • ጁዋር መሃመድ የኦህዴድና ኦዲፓ ሹማምንት በመዘወር  ከታከለ ኡማ  ጋር በየአዲስአበባ መሬት ለቆሮ ያድላል፣ በአንድ በኩል፣ የህዝብ ቤቶች እየፈረሰ፣ በሌላ በኩል፣ ለወደዳቸው ቤት መገንቢያ መሬት ይሰጣል ከንቲባው የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአርሶአደሮች ስም ግማሽ ያህሉ ያለዕጣ ለከንቲባ ታከለ ኡማ ብሎገሮችና የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች እንደተሰጠ ተጋልጦል፡፡
 • ጁዋር መሃመድ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳሰ ጋር በመዶለት የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ስነህዝብ ስብጥር (ዴሞግራፊ) ለመቀየርና ለሚቀጥለው ምርጫ ለማሸነፍ የኦሮሞ ተፈናቃይ ህዝብን በአዲስ አበባ ለማስፈር ስውር ሴራ በመዘርጋት በአስሩም ክፍለ ከተማ መታወቂያ እየወጣላቸው  የንዋሪነት መታወቂያ ተሠጠ፡፡ ታከለ ኡማ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያውን  ከአዲስ አበባ መሬት ላይ ቸክሎ ዴሞግራፊውን ለመቀየርና ለቀጣዩ ምርጫ ኦነግ እንዲያሸንፍ ስራውን እንዲሰራ ተመድቦል፡፡
 • ጁዋር መሃመድ የኦሮሚያን ክልል መንግሥት በመቆጣጠር ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ በጁሃር ፍራቻ በእሬቻ በዓል ላይ ‹‹እንደሰባበሩን ሠባበርናቸው›› እንዲሉ በማድረግ የጥላቻ ፖለቲካ እንዲሰብኩ አስደረገ፡፡
 • ጁዋር መሃመድ በኦሮሞ አባ ገዳዎች የተሠየመ የሃገሪቱ ዋና አድባር ‹‹የአባገዳዎች አባገዳ፣ ስዩመ-ቆሮ ሜንጫ ዘአሩሲ›› እየተባለ ይካደም ጀመረ፡፡ በፌዴራልና በክልል መንግሥቶች ባለስልጣኖችና ጀነራል መኮንኖች ከእሱ ጋር ያልተሞዳሞደ እርባና የለውም፡፡
 • ዶክተር አለሙ ስሜን ከሥልጣናቸው ነቀለ፣ አዲሱ አረጋን በማስፈራራት፣ በሃገሪቱና በኦሮሚያ ክልል ሾሚና ሻሪ አማካሪ በመሆን በሹማምንቶቹ ዘንድ ተፊሪ ሰው ሆነ፡፡
 • ጅዋር መሃመድ በሃገሪቱ ያሉትን መገናኛ ብዙሃን በመቆጣጠርና በተለይ የኦሮሚያ ጋዜጠኞችን እንደ ኦኤም ኤን አባሪና ተባባሪ እንዲሆኑ በማድረግ፣ የሚሚ ስብሃቱን ዛሚ ሬዲዩ ጣቢያን ለምግዛት ሲያንዛብብ፣
 • ጅዋር መሃመድ የኦሮሞ ፊዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ፓርቲ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና ኦቦ በቀለ ገርባ በተራቸው ገርባዎቹ ገበሩለት፣ ድግምት ይሁን አስማት፣ ሰርግ ይሁን ለቅሶ፣ በሰመመን ይሁን አደንዝዞ አይታወቅም ጅዋር ኦፌኮን ተቆጣጠረ፣ ‹‹ አባ ቢዮማ!!!›› የሃገሩ ባለቤት አንተ ነህ አሉት፡፡
 • ጅዋር መሃመድ ጠባቂ ጋርዶቼን በሌሊት አነሱብኝ ሊገሉኝ ነው ብሎ የድረሱልኝ ጥሪ ባረገ ሌሊት ምድር ቁና ሆነች ፣የሰማንያ ስድስት (የሞች ቁጥር 97 ደርሶል) የደሃ ልጆች ታረዱ በዘርና ኃይማኖት ተኮር ፍጅት ነበር፣ ንብረት ወደመ ‹‹መጤ፣ ሠፋሪ›› ነፍጠኛ ውጣ ነበር መፈክሩ፣ ደሞቸው ደመ ከልብ ሆኖ አለፈ፡፡ ባንዲራም አልወረደ፣ የሃዘን ቀንም አልታወጀ!!! ግፍ ሞልቶ ፈሠሠ፡፡ ጅዋር መሃመድን ለመታደግ ሁሉም የኦሮሞ ጃርሳ ፖለቲከኞችና አባገዳዎች፣ የሃገሪቱ ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች ከጅዋር ቤተመንግሥት ጉዝጎዝ ተጎዝጉዞ፣ ቀይ ምንጣፍ እንደ ቄጤማ ተነጥፎ፣  ሠንጋ ተጥሎ፣ ጠጅ ተጥሎ፣ ጠላ ተጠምቆ  ከቤቱ በፍርሃት ታደሙ፣ ጅዋር መሃመድ ስልጣኑን ያሳየበት፣ ግማሽ መንግሥትነቱን ያረጋገጠበት ወቅት ነበር፡፡
 • ዶክተር አብይ አህመድ ሁሉን እንደማያውቅ አርጎ ተወነ፣ እንኳን ይሄን የዝንብ ጠንጋራ ያውቃል፣ በኢንሳ ዋናው ስራው ስለላ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ጊዜ የሰጠው ጅዋር መሃመድ በመሆኑ እሱም  ገበረለት በአደባባይ በእኛ አገር በሻሻ ‹‹ስኳርት››ማለትና በእነጅዋር አርሲ  ‹‹ስኳርት›› ማለት ትርጉሙ ተለያይቶ ሳንግባባ ቀረን እያለ የተሳካለት ድራማ አሳየ፡፡  የዛ ቀን በኢትዮጵያና በዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ሲወገዝ በሌላ በኩል በኦሮሞ ብሄርተኞችና ብሄር ብሄረሰቦች አራማጆች ሲወደስ አደረ፡፡ ለዶክተር አብይ እቺ ቀን ለህይወቱ ወሳኝ ቀን ነበረች፡፡  እርካብና መንበር!!!
 • ዶክተር አብይ አህመድ በአንድ በኩል በብሄር ብሄረሰብ የዘርና የቌንቌመታወቂያ ካርድ  የሚሸጡ ነጋዴ የፖለቲካ ካድሬዎች የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ለፍርድ ይቀርባሉ ወይስ እንደተለመደው ተድበስብሶ ያልፋል፡፡ የህግ የበላይነት በኢትዮጵያ ይሰፍናል ወይስ አይሰፍንም፣ ፍትህ የሰጣል አይሠጥም፡፡ በሌላ በኩል አብይ በአዲስ ህገ-መንግስት በኢትዮጵያዊነትና በዜግነት ፖለቲካ ከሁሉም በላይ የህግ የበላይነትን የሚያሰፍን መንግሥት ታላቅ ድጋፍ የሚያስገኝለት ዘመን ይመጣ ይሆናል  እንላለን፡፡ እውነተኛ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ህዝብ በእኩልነት፣ በሰላምና በነጻነት ዴሞክራሲያዊና ስብዓዊ መብቶቹ ተጠብቀውለትና  እራስን በእራስ ማስተዳደር፣ በቌንቌ መማርና መዳኘት፣ ባህሉን ማሳደግ፣  ወዘተ መብቶች ይጠበቅለታል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ በቀጭን ገመድ ላይ እየተጎዙ ይገኛል ወይ ብሄር ብሄረሰብ አሊያም ኢትዮጵያዊነትን መምረጥ አማራጮች ሲሆኑ ሁለቱን አጣምሮና አስታርቆ አገር መምራት ሦስተኛ አማራጭ የሚያደርጉ ምሁራንም ይገኛሉ፡፡
 • ‹‹ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ ከአቶ ጃዋር ቤት ማግኝቱን ፖሊስ ተናገረ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘውና በቅርቡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) የተቀላቀለው የአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ሲበረበር፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ መገኘቱን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ የምርመራ ቡድኑ ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በተፈቀደለት የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜያት የሠራውን የምርመራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፣ የአቶ ጃዋር ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ሲበረበር የተለያዩ ሲዲዎች፣ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፍላሾች፣ ኢንተርኔት ለየት ባለ ሁኔታ የሚጠቀሙበት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጪ የሆነ የሳተላይት መሣሪያ ተገኝቷል ብሏል፡፡››1
 • በጅዋር መሃመድ በኢትዮጵያ ሁለት መንግስት አለ፡፡ አንደኛው የዶክተር አብይ አህመድ ሁለተኛው የቄሮ መንግሥት እንደሆነ ነግሮን ነበር፡፡ በአለው መሠረት ጅዋር መሃመድ አካውንታቸውን የጠለፈባቸው ባለሥልጣናት ውስጥ ዶክተር አብይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ ዳንኤል ክብረት፣ ዶክተር አለሙ ስሜ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ሺመልስ አብዲሳ፣ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ ኢታማጆር ሸም፣ ምክትላቸው ብርሃኑ ጁላ፣  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ እስክንድር ነጋ፣ እንዲሁም የህወሓት ሹማምንቶችን መረጃዎች በመጥለፍ፣ የስልክ ምልላሳቸውን በማዳመጥ የስለላ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ታውቆል፡፡ የሃገራችን ‹‹የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ›› (Information Network Security Agency) ብሔራዊ ደህንነታችንን ሊያስጠብቅ አልቻለም፡፡ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኔሽን ቴክኖሎጅ መገናኛ  ብቃት ባላቸው ባለሙያተኞች ባሉበት አገር በጅዋር መሰለል ለጠላት አገራት መረጃ የማይሸጥበት ምንም ምክንያት ስለሌለ በብሄራዊ ደህንነት ወንጀል ሊጠየቅ ይገባል እንላለን፡፡
 • ጅዋር መሃመድ ‹‹ኦሮሞ ፈርስት!›› በ‹‹ኦሮሞ ላስት››ነት አከተመ፡፡ የኦሮሞ ኢኮኖሚን ከአንደኛነት ወደ መጨረሻነት ከቶታል፣ የኦሮሚያን መሰረተ-ልሞቶች አውድመዋል፣ መንግሥታዊ ድርጅቶች ጋይተዋል፣ ሆቴሎች፣ ትራክተሮች፣ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፋብሪካዋችና የእርሻ ቦታዎች ተቃጥለዋል፣ የኦሮሞ ሠራተኞች ጉሮሮን ዘግተዋል፡፡ በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌና በሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች 181 ሰዎች መሞታቸውንና ጠቅላላ ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙን ጠቁሞ፣ የቡድኑ ዕቅድ የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ለአሥር ቀናት አዲስ አበባ በማቆየት ቀጣይ አመፆችን ለማቀጣጠል እንደነበር የሚያረጋግጡ ምስክሮችን ቃል መቀበሉንም አስረድቷል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  “ህውሓት በህገ መንግሥቱ አርቃቂ ኮሚሽን ተወካይ አልነበረውም” - ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ

የጅዋር ካልኩሌተር ደነበሸ! በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት መጨረሻው አያምርም፡፡

‹‹በሦስት የመገናኛ ብዙኃን ላይ የወንጀል ምርመራ ተጀመረ›› በተለያዩ ጊዜያት ብሔርን ከብሔር ጋር በማጋጨት ተጠርጥረዋል በተባሉ ሦስት የመገናኛ ብዙኃን ላይ ምርመራ መጀመሩን፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ፀጋ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስቱዲዮ ባላቸው የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን)፣ ድምፀ ወያኔ (ዲደብሊዩ) እና አሥራት ሚዲያ ላይ የብርበራ ፈቃድ ከፍርድ ቤት በመውሰድ ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን)፣ በሌላ ሳተላይት ስርጭቱን በመጀመር  የአቶ ጅዋር መሃመድ ባይኖርም ያዋቀረው ድርጅት በአጭር ጊዜ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ፅናታቸውን ያሳያል፡፡

እብሪተኞቹ  የአቶ ጅዋር መሃመድና ኦቦ በቀለ ገርባ በሃጫሉ ሁንዴሳን የጦስ ዶሮ አድርገው በመሰዋት ያቀዱት የፖለቲካ ሴራ ከመቶ ዘጠና ዘጠን በመቶ ሴጣናዊ ሥራቸው የተሳካ ነበር መላት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብን የአዲስ አበባ ህዝብን የተደገሰለትን የህዝብ እልቂትና የንብረት ውድመት የታደጉት የሃጫሉ እናት ልጄ አንቦ ነው የሚቀበረው ያሉ ጊዜ ነው፡፡ የእናትዬው ቆራጥ ውሳኔ ከመቶ አንድ እጅ ሆኖ የፖለቲካ ሴራውን የነደፉት ጅዋርና በቀለ 99 ከመቶ እጅ ይዘው ተሸነፉ፣ ጅዋርና በቀለ እግዜብሄር ሲያጋልጣቸው አስክሬኑን ለመመለስ ከቦታው ድረስ ሠንጋ ፈረሳቸውን ጭነው፣ ነጭ ለባሽ አንጋቾቻቸው መሳሪያ ደግነው አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ መለሱ፡፡ ጁዋርና በቀለ ደም አሰከራቸው ያቀዱት ሁሉ ከሸፈ፡፡  ሃጫሉ ሁንዴሳ አዲስ አበባ ቢቀበር የቀብሩ ሥነሥርዓት  ለአስር ቀናት የሚፈጅ በማድረግ ከተለያዩ ኦሮሚያ ክልል ህዝብ ወደ አዲስአበባ አምስት አቅጣጫ አስገብቶ መንገድ በመዝጋት የዘርና ሃይማኖት ፍጅት በማድረግ፣ መንግሥት ለመገልበጥ የታቀደ የፖለቲካ ሴራ እንደነበር ተጋልጦል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል

የፖለቲካ ሴረኞቹ ያልገባቸው ነገር፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ በኩል የሱማሌ ክልል፣በስተ ሰሜን በኩል የአማራ ክልል፣ አፋር ክልልና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ይዋስናሉ፤ በስተምዕራብ ደግሞ  ደቡብ ሱዳን፣ የጋምቤላ ክልልና፣ የደቡብ ክልል ሲሆን በስተ ደቡብ አቅጣጫ ከኬንያ ጋር ኦሮሚያ ክልል በስምንት ክልሎች ተከብቦ መገኘቱን በመዘንጋት አዲስ አበባን በአምስት አቅጣጫ የኦሮሞ ክልል ከበናታል በማለት ህዝብን የማስፈራራት ቀረርቶ ጊዜ ያለፈበት ፋሽስታዊ የዘርና የሃይማኖት ፍጅት ራዕዩ ያደረገ ብሎም የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን  የሥነ-ህዝብ (ዴሞግራፊውን) ለመቀየር እነጁሃር መሃመድና ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦነግ ኦፌኮ ወዘተ የፖለቲካ ሴራ በምንም መንገድ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ያልተረዱ በእንሰሳዊ ደመነፍስ የተሰባሰቡ ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ያደረጉት ሴራ ለዘላለም ከሽፎል እንላለን፡፡ የጅዋር መሃመድን ቄሮ  የገንዘብ ዝውውር፣ የመሣሪያ ዝውውርና የሚዲያ መገናኛ መረብ እንዲሁም የጅዋር ቄሮን የመረጃ መረብና ድብቅ የሳተላይት መገናኛ የስለላ መገልገያ እቃዎች በመቐለ ህወሓት ሹሞች እጅና በኦነግ ሸኔ እጅ በተጨማሪ ሊገኝ ስለሚችል አስፈላጊው ክትትል በማድረግ ሃገርን ህዝብን ከጥቃት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል እንላለን፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹አጋንቱን የጠሩት ከጠርሙሱ ውስጥ መለሱት!!!››

የዶክተር አብይ፣ የብልፅግና ፓርቲ የሃጫሉን አስክሬን በኢሉኮፕተር ጭኖ አንቦ ለወላጅ እናቱና አባቱ አደረሰ፡፡ ጅዋር መሃመድ የዶክተርን ቢጫ ኢሊኮፕተር ከመቐለ ወንጀሎኛ ጭና ለመምጣት ብቻ የተመደበች መስሎት ስለነበር የአስክሬን መኪናው በቆመበት በሌላ መኪና ወደ ኢሊኮፕትሮ ከዛም ወደ አንቦ አጎጎዙት፡፡ ጅዋር እንደሰማ በቁጣ አስክሬኑ ዳግም ወደ አዲስአበባ እንዲመጣ አዘዘ በዛም የአጫሉ አጎት ተገደሉ ሌሎችም ቆሰሉ ብሎም የአጫሉ ስርአተ ቀብር በትግል ተፈፀመ መጽናናት ለመላ ቤተሰቡ ይስጥ እንላለን፡፡ የጅዋር አንጋቾች ‹‹መርማሪ ቡድኑ በሰጠው መግለጫ ታጣቂዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባል ሆነው እያሉ ፈቃድ ሳይጠይቁ ወይም ሕጋዊ መልቀቂያ ሳያስገቡ ስለመቅረታቸው የገለጸው ትክክል እንዳልሆነ፣ መንግሥት ራሱ ለአቶ ጃዋር የመደበላቸው ጥበቃዎች መሆናቸውን፣ በኋላ ጥበቃውን መንግሥት ሲያነሳ በስምምነት የቀሩ እንጂ በሕገወጥ መንገድ የተቀጠሩና የተደራጁ እንዳልሆኑም ጠበቆቹ አስረድተዋል፡፡ የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ለአሥር ቀናት በማቆየትና የምንሊክን ሐውልት በማፍረስ የሃጫሉን አስከሬን እዚያ እንደሚቀብሩ ሲያደናግሩ እንደነበርም መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡ አቶ ሐምዛ በማኅበራዊ ድረ ገጽ መልዕክት በማስተላለፍ ድምፃዊ ሃጫሉ እንደተገደለ መግለጹንም አክሏል፡፡›› 1

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደውሉ ለማን ነው የሚደውለው! በህይወት የመኖር መብት የሌላቸው ዜጎች ምርጫ ሌላ መታረጃቸው ነው!

ህዝብ ግብር ለመንግስት የሚከፍለው በህይወት የመኖር መብቱ እንዲጠበቅለት፣ ኃብትና ንብረቱ እንዲከበርለት፣ በሰላም ገብቶ እንዲወጣ፣ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት መብትና ነጻነቱ እንዲጠበቅለት በአጠቃላይ በእኩልነት፣ በሰላምና በነፃነት አብሮ ለመኖር ነው፡፡ ለዚህ ነው ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ ለፖሊስ ሠራዊቱ፣ ለፍርድ ቤቶች፣ ለመንስታዊ መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች፣ ለምርጫ ቦርድ ወዘተ ደሞዝ በመክፈል በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ህዝብ የሚጠይቀው፡፡

‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ፣ በኢትዮጵያ አንድነትና ጥቅሞች ላይ እንደማይደራደሩ አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያን ማፍረስም አይሞከርም ብለው፣ ‹‹ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የህግ ሉዓላዊነት ሲከበርና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ሲሆን አንዱን ልጅ አንዱን የእንጀራ ልጅ ማድረግ ቀርቶ፣ ማንም ሰው ነህግ ፊት በእኩልነትና ነፃነት የሚቀዳጅበት ዘመን በተግባር ሲመጣ ነው እንላለን፡፡

የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ልደቱ አያሌው፣ ምስራቅ ክፍሌ፣ አስቴር ስዩም  ከጁሃርና በቀለ የዘርና ሃይማኖት ፍጅት ጋር ለማዛመድ መሞከር በጣም አሳዛኝ ድርጊትና አሁንም  ህዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት  እንዲያጣ ደርጋል ህሊናዎን በእውነት ያዳምጡ እንላለን፡፡ ይፈቱ!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!! የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!

ምንጭ

1 https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19366/ ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ ከአቶ ጃዋር ቤት ማግኝቱን ፖሊስ ተናገረ /19 July  2020

2 https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19189/ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን መንግሥት ገለጸ 24 June 2020

 • https://www.youtube.com/watch?v=dnJ6b07ToTc/ ጥብቅ መረጃ (ምሥጢር)፦ በጃዋር አካውንታቸው የተጠለፈ ባለሥልጣናት እነማናቸው?-“ዐቢይ ከአዲሳባ ቅያሬ ልብሴን እንዳላመጣ ከለከለኝ”-“እቴጌ ጣይቱና ደራርቱ

 

 

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.