የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በስፔን መግለጫ

spain

የስፔን መንግሥት በቅርቡ የተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፣ የጎሳ እና ሀይማኖትን መሠረት ያደረጉ ግድያዎችን በትኩረት እንዲከታተል እና ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ጋር እንዲቆም ጥሪ ስለማቅረብ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ታዋቂው የኦሮምኛ ዘፋኝ እና አክቲቪስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ፣ አዲስ በአዲስ አበባ ከተማ እና ኦሮሚያ ክልል ከሰኔ 29 ቀን 2020 ጀምሮ ከፍተኛ የጎሳ እና የሃይማኖት ጥቃቶች ተከስተዋል፡፡ እነዚህ ጥፋቶች በዋናነት ኦሮሞ ባልሆኑ እና /ወይም የተቀላቀሉ ማህበረሰቦች/ ጎሳዎች በሆኑ ሰዎች ሀብትና ንብረት እንዲሁም የሰው ነፍስ ላይ ነው ፡፡ ይህን የጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሌሎች የሰብአዊ መብት ቡድኖች የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት 167 በላይሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፣ ከ 200 በላይ ቆስለዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል 500 የሚሆኑ ሆቴሎች ፣ ፋብሪካዎች ፣ የንግድ ሕንፃዎች እና ቢሮዎችን ጨምሮ የንብረት ውድመት ደርሷል ፡፡ በዋነኝነት የመንግሥት ንብረት ፣ ትምህርት ቤቶችና የመኖሪያ ቤቶች የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ዋጋ ግምት ያላቸው ናቸው ፡፡ እነዚህ ጥቃቶች በጥሩ ሁኔታ የተደራጁ እና በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ ከ 10 በላይ ከተሞች በሚገኙ የአክራሪ እና የጥፋት ቡድኖች አባላት በሆኑ የኦሮሞ ወጣቶች አማካኝነት የተፈፀሙ ጥቃቶች ናቸው ፡፡

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዲሳ ላይ የተፈጸመው ግድያ እና ከዚያ በኋላ የተፈፀመው የዘር-ነክ ጥቃት በተወሰኑ የፖለቲካ ቡድኖች ፣ በተለይም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አማካኝነት በትግራይ ህዝብ ስም በሚነግደው ህውሃት ድጋፍ እንደተደረገ ይታመናል ፡፡ ይህ ቡድን በኢኮኖሚ እና በትምህርት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ወጣቶችን በተሳሳተ መረጃ ወደ አልተፈለገ የብሔር እና የጎሳ ግጭት ውስጥ እንዲገቡ ከፍተኛ የሆነ ቅስቀሳ የተደረገበት እና በተግባር እንዲገለጽ የተደረገበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በጎሳ እና በሃይማኖት ቡድኖች መካከል የሰላም አብሮ የመኖር ረጅም ታሪክ እና ባህል አለ ፡፡ በኦሮምያ ክልል ለብዙ ትውልዶች በሰላም አብረው የኖሩ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ ብዙ ማህበረሰቦችየሚ ኖሩባት ስትሆን ለሌሎች ክልል ምሳሌ ናት ፡፡ አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብ ከቅርብ ጊዜ ግጭቶች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፡፡ በተቃራኒው ብዙዎች ጎረቤቶቻቸውን እና የሌላ ጎሳዎች ጓደኞቻቸውን በመጠበቅ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነበር።

የቅርብ ጊዜዎቹን ክስተቶች በመጥቀስ መንግስት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ ህጋዊ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን

በሕዝቡ እና በንብረታቸው ላይ ጥቃት ያደርሳሉ ተብሎ የተጠረጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ያልዋለ መሆኑን እና ጠንካራ አክራሪነት አሁንም ለኢትዮጵያ መረጋጋት ፣ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ላይ ትልቅ አደጋን ለመፍጠር የሚችል ከመሆኑም ባሻገር አደጋው ለአፍሪካ ቀንድም ጭምር አስጊ የሚሆን ነው ፡፡ በጣም የሚያሳስበዉ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች በሀሳብ ነጻነት ጃንጥላ ስር በመጠለል በሚያራምዱት አጀንዳ በሰዎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ላይ የማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ጥላቻን እና ዓመፅን የሚያነሳሱ የሐሳቦችን ፣ ዜናዎችን እና ንግግሮችን ማሰራጨት እና እርስ በእርስ አለመግባባትን ብሎም ብጥብጥን ማሰራጨት አላማ ያደረገ ነው ፡፡ አብዛኛዎቹ እነዚህ መልእክቶች ነፃ በሆነ መልኩ ያለ ተጠያቂነት ከአውሮፓ ህብረት ሀገራት ውስጥ ይሰራጫሉ ፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቅርብ ጊዜ በአገራችን የተከሰቱት ዓይነት ማህበራዊ ብጥብጦች በብዙዎቹ የአፍሪካ አካባቢዎች መታየት ከሚገባቸው በላይ በጣም በተደጋገመ ሁኔታ እየታዩ ይገኛል ፡፡ ይህ ብዙውን ጊዜ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኩል በግዴለሽነት ታይቷል ፡፡ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በጣም የከፋ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል አፅንኦት መስጠት እንፈልጋለን ፡፡ የማኅበራዊ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ እንዲጣሳ እንዲሁም የጅምላ ጭፍጨፋ ድርጊቶችን ጨምሮ ሌሎች ኢሰባአዊ የሆኑ ክዋኒዎች ሊቀጥሉ እንዲምችሉ የሚታይ ሀቅ ነው፡፡

ከዚህ ሁኔታ በመነሳት እኛ በትውልድ ኢትዮጵያውና የስፒን ዜጎች እና በስፔን የምንኖረው ኢትዪጵያን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የትብብር ሚንኒስትር ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር አልቤርቶ ሴሬዞ ጋር ተገናኘተን ተወያይተናል፡፡ የውይይቱም ዓላማ ለሚኒስትር መስሪያ ቤት ስለሁኔታው አጭር መግለጫ በመስጠት ለክብርት ሚንስተር አራንቻ ጎንዛሌ ኦፊሴላዊ ደብዳቤ በማስገባት በአሁኑ ሰዓት በኢትዪጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እንዲከታተሉ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ ህብረት እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆኑ በአገሪቱ ላይ እየተካሂደ ያለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች እና ማሻሽያዎች እንዲደግፉ ከዛም ባሻገር በአገሪቱ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ለሚደረገወ ጥረት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለመጠየቅ ነው ፡፡

 

Contacts: Ayalkibet Hundesa Gonfa, Email: ayalkibcn@gmail.com, Tel. +34-675903697

Kaleab Getaneh Zewelde, Email: kalgetaneh@gmail.com, Tel. +34-645310645

Berihanu Chimdi, Email: berhanu.chimdi@gmail.com; Tel. +34-626760190

1 Comment

  1. What change? What improvement? Are you guys unable to see & understand what’s going on? Or are you just trying to get support for the govt. regardless. Need to come out clean. Are you with Ethiopians or with the repressive and murderous regiem?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.