ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን ያበስራሉ

Dam 1ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ በያሉበት ሆነው ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን የሚያበስሩ መሆኑ ተገለጸ።
የሁነቱ አዘጋጆች “ድምጻችን ለግድባችን” በሚል መሪ ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይህ ዓለም አቀፍ ሁነት ኢትዮጵያውያን ግድቡ አሁን የደረሰበት ደረጃ በመድረሱ የተሰማቸውን ደስታ እንዲገልጹ የተዘጋጀ ነው።
የሊፍት ኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ አባል አቶ አብርሃም ስዩም እንደተናገሩት፤ የግድቡ የመጀመሪያ ዙሪያ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ እንደ ቀላል ነገር መታየት የለበትም። የዓለም ዐይንና ጆሮ የሚከታተለው እጅግ ትልቅ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በከፈለው መስዋዕትነት እና በመሪዎች ቆራጥ አመራር እዚህ መድረሱ እጅግ የሚያስደስት ነው።
ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ እየፈለገ ኮሮናን በመፍራት ሊያደርገው ስላልቻለ የህዝቡን ፍላጎት ለማሳካት ከጽህፈት ቤቱ ጋር በመሆን ሁነቱ መዘጋጀቱን ያብራሩት አቶ አብርሃም፤ በቤታቸው ያሉ ሰዎች በራፍ ላይ በመቆም፣ መኪና የሚነዱ ሰዎች መኪናቸውን ጥግ አስይዘው በማቆም፣ መንገድ ላይ የሚሄዱ ሰዎች ባሉበት ቆመው፣ ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን እንዲገልጹ ታስቦ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።
ለኮሮና ወረርሽኝ በማያጋልጥ መልኩ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ድምጻችን ለግድባችን በማለት፣ እጃቸውንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ በማውለብለብ እንዲሁም በብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት ተውበውና አምረው ደስታቸውን መግለጽ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እስከ ግድቡ ፍጻሜ ድረስ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያ የምትከተለውን የልማት አቅጣጫ ማህበረሰቡ የሚደግፈው መሆኑን ለዓለም ማህበረሰብ መልዕክት የሚተላለፍበት ነው።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም እንደተናገሩት፤ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ስኬት ነው። የውሃ ሙሌቱ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በሚዲያዎች በተሰራጨው የሀሰት መረጃ ምክንያት ስጋት ውስጥ ወድቀው ለነበሩ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ህዝቦችም ትልቅ ብስራት ነው። ግድቡ ጉዳት እንደማያደርስባቸው በተጨባጭ ያረጋገጡበት ነው ። በዚህም መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ደስ ብሏቸዋል።
ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድምጻቸውን የሚያሰሙት ግድቡን እየተገነበ ያለው ማንንም ለመጉዳት ሳይሆን ለፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ከድህነት ለመውጣት መሆኑን ዓለም እንዲያውቅ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ፤ ከዚያ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንደጀመሩት እንዲጨርሱት መልዕክት ለማስተላላፍ ያለመ ነው። በተለይም ዲያስፖራው ካለው አቅም አንጻር የሚጠበቅበትን ስላልተወጣ ለማነቃቃት ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሀይሉ ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ ግድብ የምትገነባው በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ በፍትሃዊነት ለመጠቀም እንደሆነ የውሃ ሙሌቱ ያረጋገጠ ነው። የውሃ ሙሌቱ ዓለም የኢትዮጵያን ፍላጎት እንዲረዳ እድል የፈጠረ ነው። ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነው። የውሃ ሙሌት ቀጣይ ድርድር በመተማመን ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የህዳሴ ግድብ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ከሸራተን አዲስ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ መርሃ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012
መላኩ ኤሮሴ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የዘመናችን አድዋ ዘመቻ - ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የትብብር

3 Comments

 1. In time of severe genocidal acts taking place when dead bodies got dragged around for miles with the blood stains still seen from Ziway , Arsi , Shashamane , Addis Ababa , Guba …. , when mourning is silenced with thousands including the victim’s family members in jail, how can celebrating be suggested?

  Are those thousands recently put in jails allowed to celebrate too since they are presumed innocent until they are proven guilty? Is Dawud Ibssa celebrating too?

  When a few distance away from the dam fourteen farmers got slaughtered days ago with tens of thousands displaced from Guba area, how can celebration be suggested.

  Personally I celebrate if I Ilve long enough to get the GERD bond I have invested returned to me.

  The Medemer freaks might next ASK US TO CELEBRATE EACH TIME WHEN WE TURN OUR WATER FOSSIL ON, WITHIN OUR HOMES.

  Ethiopia currently got the 65th highest number of Covid-19 infections in the world due to the failed Medemer freak in power.

  We need a transitional government or a care taker government ASAP because the Medemer freaks are not in touch with the reality on the ground.

 2. In time of severe genocidal acts taking place when dead bodies got dragged around for miles with the blood stains still seen from Ziway , Arsi , Shashamane , Addis Ababa , Guba …. , when mourning is silenced with thousands including the victim’s family members in jail, how can celebrating be suggested?

  Are those thousands recently put in jails allowed to celebrate too since they are presumed innocent until they are proven guilty? Is Dawud Ibssa celebrating too?

  When a few distance away from the dam fourteen farmers got slaughtered days ago with tens of thousands displaced from Guba area, how can celebration be suggested.

  Personally I celebrate if I Ilve long enough to get the GERD bond I have invested returned to me.

  The Medemer freaks might next ASK US TO CELEBRATE EACH TIME WHEN WE TURN OUR WATER FAUCETS ON WITHIN OUR HOMES.

  Ethiopia currently got the 65th highest number of Covid-19 infections in the world due to the failed Medemer freak in power.

  We need a transitional government or a care taker government ASAP because the Medemer freaks are not intouch with the reality on the ground.

 3. Dictator Abiy Ahmed is squashing his oppositions competitors. The country is under siege , Ethiopians are being forced to support PP to escape prosecution.

  The only political party cadres that are not imprisoned in the current arrests in Addis Ababa are PP’s cadres, all other political parties got some of their members or leaders arrested in Addis Ababa, many Addis Ababa residents are scared for their lives are seen chanting “Abiy Abay Nieww!!!” Just to escape being arrested by Abiy Ahmed in Addis Ababa .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.