የኤርትራ ጉዳይ እና የእንግሊዝ ሴራ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ     

Eriteria zehabeshaሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ/ም

የእንግሊዝን ሴራ እንኳን ኢትዮጵያውያን ሌላው የዓለም ሕዝብም ቢሆን መረዳት የሚገባውን ያህል አያውቀውም። የእንግሊዝን ሴራ ጠንቅቀው ያውቁ የነበሩት በቅድሚያ አፄ ቴዎድሮስ፤ በቀጣይም ዳግማዊ አጼ ምኒልክ እና ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ። ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በነበሩበት ወቅት ብዙ ኋላ ቀር አሠራሮችን በዘመናዊነት ለመተካት የተቻላቸውን ያህል ጥረዋል። ከዚህም ውስጥ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ የነበረውን የተንዛዛ አሠራርም መልክ ለማስያዝ አዋጅ እስከ ማወጅ ሄደዋል። በወቅቱ መሬት በሙሉ የቤተ ክርስቲያን ነበር። ታዲያ ማንኛውም ገበሬ አርሦ ከሚያገኘው ምርት ላይ ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ማድረግ ነበረበት። በተጨማሪም፤ የማርያም ባርኪ፤ የበረድ፤ የድመት፤ ክፈል እየተባለ ባላገሩ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫና ነበረበት።

ታዲያ ቀሳውስትና ካህናት ያንን ምርት እየተከፋፈሉ ይተዳደሩበት ነበር። ከዚህም የተነሣ ካህናት የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ እንዳይታጎል በሰሞን (በፕሮግራም) ተከፋፍለው አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ምክንያት በማድረግ አጃቸውን አለስልሰው ሥራ አይሠሩም ነበር። አፄ ቴዎድሮስ በጣና ሐይቅ በሚገኘው ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም እየተማሩ ያደጉ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያኑን ሥርዓት በሚገባ ያውቁታል። እርሳቸው መንበረ መንግሥቱን ከያዙ በኋላ ዘመናዊ ወታደር ለመገንባት ዕቅድ አወጡ። ነገር ግን በዚያን ዘመን፤ አሁን እንዳለው ሁኔታ ብር ቆጥሮ ደመወዝ መክፈል የሚቻል አልነበረምና ይህንን በሚያካካስ መልኩ፤ በሰላም ጊዜ አርሦ የሚበላ፤ በችግር ጊዜ ደግሞ ፈጥኖ የሚደርስ፤ የመንግሥት ጦር ለማደራጅት ያስችል ዘንድ የመተዳደሪያ ቦታ መምራት ነበረባቸው።

ይህንን ቦታ ለማደላደል ሲነሱ ቀሳውስትና ካህናት በተቃውሞ ቆሙባቸው። ሰሙ፤ የታቦት መሬት ስለሆነ አይወሰድም የሚል ሲሆን፤ ወርቁ ግን መተዳደሪያችንን አንስጥም ዓይነት ነበር። በዚህ ጊዜ አፄ ቴዎድሮስ እስከ አሁን እየተሠራበት ያለውን ራሡን የቻለ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አዋጅ አወጡ። በዚህም በያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ከሁለት ቄስና ከሦስት ዲያቆን በላይ እንዳይቀድስ አደረጉ። ከዚያ በላይ ያሉ ካህናት ግን እንደማንኛውም አርሦ አደር እያረሡ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲያስተዳድሩ የሚደነግግ አዋጅ ነበር።አርሦ አደሩ እዋጁን በደስታ ሲቀበለው፤ ካህናት ግን ተደፈርን በማለት እጅግ በጣም ተቆጡ አድማም አደረጉባቸው።

በዚያን ጊዜ እንግሊዝ ኢትዮጵያን በመክበብ የቅኝ ግዛቷን አያስፋፋች ነበር። ምናልባት ኢትዮጵያንም ከዕቅዷ ውስጥ ሳታስገባት አልቀረችም። ምክንያቱም በምሥራቅ  ፑንት ላንድን (ሐርጌሳን)፤ በደቡብ ኬንያን፤ በምዕራብ ደግሞ የታችኛውን የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ማለትም ሱዳንና ግብጽን እያስተዳደረች ነበር። በእነዚህ መሬቶች ጥጥን ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎቿ፤ ሰሊጥን ደግሞ ለምግብ ዘይት በገፍ እያመረተች ትጠቀም ነበር።

ለዚህ ሁሉ የምርት ኃይል ዋና የሆነው የዓባይ ወንዝ መሆኑን በመገንዘብ፤ ይህንን ወንዝ በበላይነት ለመቆጣጠር ፍላጎት አደረባቸው። ከዚህም የተነሣ በወቅቱ የአገሪቱ የበላይ በነበረችው ንግሥት ቪክቶሪያ ‘የዓባይን ምንጭ ቃኝቶ ለተመለሰ እንግሊዛዊ ከፍተኛ ሽልማት እንደምትሰጥ’ በአዋጅ ተነገረ። በዚህ ጊዜ ጥቂት የማይባሉ ወጣቶችና ጎልማሶች እየተሰባሰቡ በቡድን በቡድን በመሆን እልህ አስጨራሽ የሆነውን ጀብድ የተሞላበት ዘመቻ ወደ አፍሪካ አደረጉ።

ዘመቻውን አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተመዘገቡ አንዳንድ የጉዞ ዘዴዎችና መመሪያዎች ያሉበት ቅድመ ሥልጠናዎች እንዲወስዱ ተደርጓል። አንዳንዶቹ መጠነኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት እንዲኖራቸው ሆኖ ካባ በመልበስና ጺማቸውን በማሳደግ የሃይማኖት ሰው በመምሰል፤ ወደ ኢትዮጵያ ሠርገው እንዲገቡ ሆነዋል። ሌሎችም እንዲሁ መጠነኛ የሕክምና ሙያ እንዲኖራቸው ተደርገው ተልከዋል። የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አንድን አገር ለመውረር ሲያስቡ በቅድሚያ በዚያ አገር የከብትና የሕፃናት በሽታን በማስገባት የነዋሪውን ሞራልና ቅስም ለመስበር ይሞክራሉ። ከዚያም ሕዝቡ የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጥቶ በሐዘን በሚቆዝምበት ሰዓት፤ እነርሱ የተደራጀውን ኃይላቸውን ያስገቡና አገሪቱን በሞላ ይቆጣጠራሉ።

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥትም የተደረገው ይኸው ነበር። አጥኝዎቹ (ሰላዮቹ) በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ መግባት ጀመሩ። በወቅቱ በነበረው የአገዛዝ ሰንሰለት አማካይነት አንድ የውጭ አገር ዜጋ ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወዲያውኑ ለበላይ የመንግሥት አካላት የማሳወቅ ኃላፊነት ስለነበር እንግዶቹ ለአፄ ቴዎድሮስ ይቀርቡ ነበር። እርሳቸውም በንጉሥ ሰሎሞን የተሠራው የኢየሩሳሌሙ ታላቁ ቤተ መቅደስ በቱርኮች ተወሮ ወደ መስጊድ ተቀይሯል፤ የሚባል አሳዛኝ ዜና ሰምተው ስለነበር፤ ያንን ነፃ ለማውጣትና እንደ ቀድሞው ለመመለስ ሐሳብ ነበራቸው።

ታዲያ የእንግሊዝ ሰላዮችን ‘ለምን ወደ ኢትዮጵያ ምድር መጣችሁ? ምንስ ይዛችሁ መጣችሁ?’ ብለው ሲጠይቋቸው ‘እኛ የመጣነው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሲሆን፤ ያመጣነውም መጽሐፍ ቅዱስና መስቀል ነው፤’ በማለት እንደመለሱላቸው ታሪክ ያስረዳል። ንጉሡም ክርስቲያን ከሆናችሁ ታዲያ የኢየሩሳሌሙ ቤተ መቅደስ ወደ መስጊድ ሲለወጥ እንዴት አልቆጫችሁም? በማለት እንደመለሱላቸው ይታወቃል።

‘አሁንም’ አሉ አፄ ቶዎድሮስ ‘የእኛን ወዳጅነት የምትፈልጉ ከሆነ፤ የዕደ ጥበብ አዋቂዎችንና የመሥሪያ ዕቃዎችን ብታመጡልን ለሰዎቹ ጥሩ መሀያ (ደመወዝ) እንሠፍርላቸዋለን’ በማለት ሲናገሩ፤ ከእንግዶቹ አንዱ ‘ይህንን ማድረግ የምትችለው የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ቪክቶሪያ ነች፤ ስለዚህ ደብዳቤ ቢጽፉ መልካም ነው’ በማለት ሐሳብ አቀረበላቸው።

አፄ ቴዎድሮስም ደብዳቤውን ጽፈው ላኩ፤ ነገር ግን በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው መልስ በወቅቱ ሊደርስላቸው አልቻለም። ሰላዮቹ ግን ከንግሥቲቱ የሚሰጠውን ሽልማት ለማግኘት በማሰብ ወደ ኢትዮጵያ መጉረፋቸውን አላቆሙም። በዚህ የተናደዱት አፄ ቴዎድሮስ ለደብዳቤያቸው ተገቢ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ፤ የእንግሊዝ ሰላዮችን በግዞት እንዲቆዩ አዘዙ። በዚያን ወቅት እንግሊዞች (The Sun will never set down in the British Empire) በግዛታችን ፀሐይ አትጠልቅም፤ እያሉ የሚኩራሩበት ዘመን ነበር።

እንግሊዝ በዓለም ላይ እንዲህ ያለ ዝና በተጎናጸፈችበት ሰዓት 154 እንግሊዛውያን በኢትዮጵያ ምድር የመታገታቸው ዜና ለእነርሱ ታላቅ ውርደት እንደሆነ ተቆጠረ። ይሁን እንጂ ታሪኩ እውነት ስለሆነ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ፤ በእንግሊዝ ታሪክ ውስጥ፤ ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ሲተረክ ይኖራል። ከዚህም የተነሳ ሻለቃ ናፒር የጄኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቶት ወደ ኢትዮጵያ እንዲዘምትና የእንግሊዝ እስረኞችን እንዲያስለቅቅ፡የኢትዮጵያንም ማዕከላዊ መንግሥት እንዲያፈርስ መመሪያ ተሰጥቶት ከሕንድ ተነስቶ ዘመተ።

ይህ ተልዕኮም በስኬት እንዲፈጸም የአገር ውስጥ ባንዳዎችን በጥቅም ገዛ። ለዚህም የትግራዩ ካሣ ምርጫ በኋላ አፄ ዩሐንስ አራተኛ ዋናው ሲሆኑ፤ አስከ መቅደላ አምባ ድረስ ያለምንም ችግር እየመሩ ማድረሳቸውን ታሪክ መዝግቦት ይገኛል።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እንግሊዞች፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር ብዙ የተወሳሰቡ ዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎችን ወስደዋል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ‘አቢሲኒያ’ በሚል እየቀየሩ የዓለምን ካርታ ሠሩ፤ መጻሕፍትንም እያሳተሙ አሰራጩ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ባሕረ ኤርትራ እየተባለ ይጠራ የነበረውን ባሕር፤ ወደ ‘ቀይ ባሕር’ (Red Sea) በማለት ከለወጡ በኋላ፤ ባሕር ነጋሽ በመባል የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ግዛት፤ ኤርትራ የሚል ስያሜ በመስጠት፤ ማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ከውጭ አገር ጋር የሚያገናኝ የባሕር ወደብ እንዳይኖረው ካርታ በመንደፍ፤ በጣሊያን መንግሥት በቅኝ ግዛትነት እንዲያዝ፤ጉትጎታ እና ድጋፍ ማድረጋቸውም መታወቅ አለበት።

በወቅቱ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ምንም ዓይነት ዕቅድና ዝግጅት አልነበራትም። ነገር ግን ጣሊያን ‘የሦስቱ ቃል ኪዳን አገሮች’ ዓባል ስለነበረች (እንግሊዝ፤ ፈረንሣይና ጣሊያን) እንግሊዝ ለጣሊያን ያሰባች በመምሰል፤ ጣሊያን በአፍሪካ ውስጥ ያሏት የቅኝ ጋዛቶች ሊቢያና የበረሃማዋ ሶማሌ መቋድሾ ብቻ ስለነበሩ እኒህም ከእንግሊዝና ከፈረንሣይ ቅኝ ግዛት አገሮች ጋር ሲነጻጸር በጣም ዓነስተኛ ስለሆኑ ‘ኤርትራ’ ብለው የሰየሟትን የኢትዮጵያ ግዛት እንዲይይዙ፤ ለዚህም አስፈላገውን የፖለቲካና የማቴሪያል ድጋፍ እንደሚሰጡ በማግባባት አደፋፈሯቸው።

ትንሽ ዓመታት ቆይተውም አቢሲኒያ ብለው የሰየሟትን ዋናዋን ኢትዮጵያ እንዲጠቀልሉ ከፍተኛ የሆነ ጉትጎታና የመረጃ ልውውጥም ሲያደርጉ ቆይተው፤ ይህንኑ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የነጭ ኃይል በዕብሪት በተንቀሳቀሰበት ወቅት፤ በአፄ ምኒልክ ጥበበኛ አመራር የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ/ም አድዋ ላይ ከፍተኛ ሽንፈት ተከናንበዋል። ይህ ጥቃት የጣሊያን ብቻ ሳይሆን የእንግሊዝም ጭምር ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ኪሣራ ነበር። ምክንያቱም አውሮፓውያን የነጭ ወራሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች ድል የሆኑበት ክስተት በመሆኑ ከፍተኛ ቁጭትና ንዴት አሳድሮባቸዋል።

ከዚያም በሁሉም አቅጠጫ ኢትዮጵያ የውጭውን ዓለም የሥልጣኔ ብርሃን እንዳታገኝ ዙሪያውን ከበው በመቆጣጠር በፖሊሲ ደረጃ ነድፈው ዕድገቷን ሲያቀጭጩ ቆይተዋል። በዚህ ብቻም አላበቃም ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ባደረጉት የተራድዖ ውል መሠረት ዓባይን ለመገደብ ስምምነት ተፈራረሙ።

ይህንን ተከትሎ በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የአሜሪካ መሐንዲሦች ኢትዮጵያ በመግባት ከ1925-27 ዓ/ም ባለው ጊዜ የዓባይ ወንዝ አሁን እየተገደበ ያለበትን ቦታ ሲያጠኑና ሲቀይሱ መቆየታቸው ግልጽ ነው። በሚቀጥለው ዓመት ማለትም በ1928 ዓ/ም ግድቡ እንደሚጀመር የተረዳችው እንግሊዝ፤ አንደኛ ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ብርሃን እንዳታገኝ፤ በቀጣይም እራሷ በቅኝ ግዛት በምታስተዳድራቸው በሱዳንና በግብጽ ያላት ጥቅም አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል በመገመት ሁለት ስለት ያለው ሠይፍ ሆና ቀረበች።

አንደኛ ጣሊያን ከአርባ ዓመታት በፊት አድዋ ላይ የደረሰባትን ሽንፋት እንድትበቀልና፤ ከኤርትራ በመሻገር አቢሲኒያን እንድትገዛ እንግሊዝ አስፈላጊውን ዕርዳታ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። በሌላው ወወገን ደግሞ ለአሜሪካ መንግሥት ወዳጅ በመምሰል ወደፊት አቢሲኒያ የሰላም ቀጠና ሳትሆን ችግር አያንዣበበባት የምትገኝ ሀገር መሆኗን በመረጃ ያረጋገጠች በመሆኑ፤ ዜጎቿን በአስቸኳይ እንድታስወጣ በማለት መወትወት ያዘች።

ከዚህ በኋላ አሜሪካ፤ የዓባይን ግድብ ከመጀመር ይልቅ የእንግሊዝን ምክር በመቀበል፤ መሐንዲሶችን ማስወጣት መረጠች። በቢንቶ ሙሶሎኒ ጠ/ሚንስትርነት የምትመራዋ ጣሊያንም የአድዋን ጦርነት የመበቀል እርምጃዋን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በዓለም የተከለከለ የመርዝ ጢስ ጭምር በአውሮፕላን በመርጨት ኢትዮጵያን ለመውረር ወሰነች።

ይሁን እንጄ እንግሊዞች፤ ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ፤የልጅ ኢያሱን የአመራር ስልት በመፍራት፤ ‘እኛን በማግለል ከጀርመኖች ጋር እየተወዳጁ ነው’ በማለት በረቀቀ ሤራ ልጅ ኢያሱን ከሥልጣን እንዲወርዱ ካደረጉ በኋላ፤የተኩት ራሥ ተፈሪም ከጀርመኖች ጋር ጥሩ ወዳጅነት በመፍጠራቸው፤ የእንግሊዞችን መሠሪ ተንኰል ከጀርመኖቹ ለመረዳት አስችሏቸዋል። ከዚያም ኅልቆ መሣፍርት የሌለው የጦር መሣሪያ ከጀርመን መንግሥት በመግዛት ከጠላት የሚሠነዘርባቸውን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ነገር ግን ከጀርመን ተገዝቶ ጅቡቲ የተራገፈውን መሣሪያ ወደ መሃል አገር ለማስገባት ሲሞከር፤ የፈረንሣይ መንግሥት በቅድሚያ የእንግሊዝ መንግሥት ካልፈቀደ በስተቀር መሣሪያውን አንለቅም የሚል አቋም ያዘ። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴም የእንግሊዝን መንግሥት ሲጠይቁ መሣሪያው እንደማይለቀቅ ተነገራቸው። ይሁን እንጂ ንጉሡ ከአገር ለመውጣት ቢፈልጉ ምንም ዓይነት ጥቃት ሊደርስባቸው እንደማይችል ቃል ተገባላቸው። ንጉሡ ግን በሁኔታው እጅግ በማዘን ከሕዝባቸው ጋር ለመሞት ቁርጠኛ አቋም በያዙ ጊዜ፤ መኳንንቱና ቀሳውስት ተመካክረው ታቦት በመሸከም የአገሪቱ አርማ የሆነው የዘውድ መንግሥት ሳይነካ እንዲቆይ በማሰብ ንጉሡ ወደ ጄኔቫ በመሔድ በዓለም መንግስታት ማኅበር እንዲሟገቱ ለመኗቸው። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴም በሁኔታው አዝነው መኳንንቱና ካህናቱ በጠየቁት መሠረት እንዲፈጸም ተስማሙ።

ከአምስት ዓመታት የቢሮክራሲ መጉላላት በኋላ በመጨረሻ ጣሊያን በዕብሪት የወረረቻትን ኢትዮጵያን በአስቸኳይ ለቃ እንድትወጣ ሲወሰን፤ እንደገና እንግሊዝ ተገልብጣ ይህንን ለማስተባበርና ለማስፈጸም ጣልቃ ገባች። እነ ጄኔራል ዊንጌት፤ ጄኔራል ካኒንግሃምና ጄኔኔራል ካሜሮን የተባሉት የእንግሊዝ ጄኔራሎች ጣሊያንን ለማስወጣት ከንጉሡ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። በዚህ ጊዜ እነዚህ ጄኔራሎች ማንኛውንም የጣሊያን ፋብሪካ እና ቁሳቁስ በምርኮ መልክ ወደ ግዛታቸው አሻገሩ። ለምሳሌም በጎንደር አካባቢ አዘዞ የነበሩትን የሚስማርና የእርሻ መሣሪያ ፋብሪካዎችን ወደ ሱዳን ወሰዱ። ከዚህ ውስጥ ጎንደር ከተማ የነበረውን የሪድዮ ጣቢያም ወደ ሱዳን ኡምድርማን መውሰዳቸው ይታወቃል።

በመሃል አገርና በደቡብ የነበሩትን የቆሙ መኪናዎች ሳይቀር ወደ ኬንያ ሲወስዱ፤ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘውንም ወደ ሐርጌሣ አሽሽተዋል። በአጠቃላይ ማንኛውንም ብረት ነክ የሆነ ነገር ሁሉ እየሰበሰቡ ምንም ሳያስቀሩ ዘርፈዋል። ለዚህም ዋናው ዓላማ ኢትዮጵያን ኋላቀር አድርጎ ለማቆየት በእንግሊዝ መንግሥት የተነደፈውን ምሥጢራዊ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ የተሠራ መሆኑን ያመለክታል።

ቀጥሎም የዓለም መንግሥታት ማኅበር በኢትዮጵያ ላይ በያዘው አድሏዊ አቋም ምክንያት ፈርሶ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲቋቋም፤ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በዓለም አካባቢ በቅኝ ግዛት የተያዙት አገራት ሁሉ ነፃ እስካልወጡ ድረስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ተመሳሳይ ስህተት ከመፈጸም ነፃ ሊሆን እንደማይችል በአሳሰቡት መሠረት፤ አስተያየታቸው በሁለቱም ኃያላን መንግሥታት (በአሜሪካና በሶቪየት ኅብረት) ድጋፍ አገኘ። ነገር ግን የእንግሊዝ መንግሥት የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎችን  በማስተባበር ያፈሰሱትን ንብረት የሚሰበስቡበት የአሥራ አምስት ዓመት ጊዜ እንዲሰጣቸው፤በቅኝ ግዛት ዘመን የተሠሩ የአገሮች ካርታዎችም ባሉበት እንዲቀጥሉ ጠየቁ።

በዚህም መሠረት ከ15 ዓመታት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን ሲወሰን፤ ጣሊያንም የኢትዮጵያ አካል የሆነችውን ኤርትራን ለቃ እንድትወጣ ሆነ። ነገር ግን ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ከመቀላቀሏ በፊት የሕዝቡን ስሜትና ምርጫ ለመረዳት እንዲቻል፤ በቅድሚያ ለተወሰነ ጊዜ በሞግዚት አስተዳደር እንድትቆይ የሚል በእንግሊዝና በፓኪስታኑ ተወካይ ተጠንስሦ፤ ስለአካባቢው ፖለቲካና ባህል ሠፊ ዕውቀት ያለኝ እኔ ነኝ በማለቷ እንግሊዝ ኤርትራን እንድታስተዳድር ተመደበች።

እንግሊዝ የኤርትራን ሕዝብ ለአሥር ዓመታት ያህል በሞግዚትነት ስታስተዳድር፤ የኤርትራን ሕዝብ ስሜትና ምርጫ በሚገባ ተረድታለች። ይኸውም የኤርትራ ሕዝብ ወደ እናት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመቀላቀል የሚፈልግ መሆኑን በአቋቋመው ጠንካራ ‘የአገር ፍቅር ማኅበር’ አማካይነት በየቀኑ እያረጋገጠ መጣ። እንዲህ ያለው አቋም እንግሊዝ የያዘችውን ኢትዮጵያን የማዳከም ፖሊሲ የሚጻረር በመሆኑ አገሪቱን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት፤ ስውር አጀንዳቸውን የሚያስፈጽም ሌላ አፍራሽ አማራጭ አዘጋጁ። ይኸውም ‘ጀበሐ’ የተባለውን የአማፂ ቡድን ፓርቲ በማቋቋም፤ ሥልጠናና የማቴሪያል ድጋፍ በመስጠት አደራጅተው ወጡ።

ነገር ግን በጊዜ ሂደት ‘ጀብሐ’ ወደ ሻዕብያ ተቀይሮና አድጎ በግብጽና በሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ሲረዳ ቆይቶ፤ እንደ መለስ ዜናዊ በመሰሉ የአገር ውስጥ ባንዳዎችና የግብጽ ዜጋ በሆነው በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በነበረው ‘ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ’ አጽዳቂነት የማታ ማታ የአሰቡት ተሳክቶ የኤርትራ ሕዝብ ሳይወድ በግድ በተጠነሰሰበት ሴራ ከኢትዮጵያ እንዲነጠል ተደረገ።

ለዚህ  የተቀነባበረ ተንኰልና ሤራ ዋናው ተጠያቂ በእናቱ ኤርትራዊ ሆኖ በአባቱ የአድዋ ባንዳ ልጅ እንደነበር የሚታወቅው መለስ ዜናዊ ነው። መለስ እጅግ በጣም ሥልጣንና ገንዘብ የሚወድ የሠይጣን ደቀመዝሙር ነበር። ሥልጣን በያዘ ማግሥት ኢትዮጵያ በነበረችበት ሁኔታ የምትቀጥል ከሆነ፤ገና ለገና ኢሳያስ ሥልጣኔን ሊጋፋኝ ይችላል በማለት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይመክርበት ኤርትራ ነፃ አገር መሆኗን በመግለጽ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደብዳቤ መጻፉን በቁጭት የምናስታውሰው ጉዳይ ነው።

አያይዞም ‘የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል’ እንደሚባለው ‘ነፃነት ወይም ባርነት’ የሚል በማር የተለወሰ ምርጫ በማቅረብ የራሡን ፍላጎት ለማሳካት ሲል የኤርትራን ሕዝብ ሆነ ብሎ አታሏል። ከዚያም በኋላ በሁለቱ አገሮች የተፈጠረውን ጦርነትና የተከሰተውን ከመቶ ሺህ በላይ የሆነ የሕዝብ ዕልቂት ምንጊዜም በሐዘን ሲቆጨን ይኖራል።

ጦርነቱ ከተካሄደ ከ20 ዓመታት በኋላስ? የኤርትራ ሕዝብ እስከ አሁን ድረስ በውጭ አገራት ጣልቃ ገብነት ሲሠራበት የቆየውን ተንኮልና ሴራ በሚገባ የተገነዘበው መሆኑ ተረጋግጧል። በአሁኑ ሰዓት የኤርትራ ሕዝብ በኃይል ተይዞ እንጂ፤ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ባለው ፍቅርና ጉጉት፤ እንደ ቀድሞው ወደ እናት ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመዋሃድ እንደሚፈልግ በስውር ከተደረገ ጥናትና ቃለ ምልልስ ለመረዳት ተችሏል።

ምንም እንኳ የተሟላ ባይሆንም የጥናቱ ዘርፍ ያካተተው እንደሚከተለው ነበር።

ተራ ቁጥርዘርፍየተጠየቁት ብዛትበአዎንታበተቃውሞ
1የመንግሥት ሠራተኞች21619818
2ነጋዴዎች134134
3የከተማ ነዋሪዎች32128734
4ተማሪዎች44337172
5የገጠር ነዋሪዎች1971916
6ወታደሮች88817
7ፖለቲከኞች261115
8ጋዜጠኞች22202
9መምህራን1039211
10የሕክምና ባለሙያዎች77752
                         ጠቅላላ ድምር16271460167

 

እንግዲህ ካላይ ከተደረገው የጥናት ውጤት እንደምንረዳው 89.7% የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብ በውጭ አገር ጣልቃ ገብነት እየተሠራ ያለውን ሤራ የተገነዘበ ይመስላል። ይህንን ጉዳይ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈርቂም ቢሆን፤ ኢትዮጵያን በማይወዱ የውጭ ኃይሎች እየተሠራ ያለውን ተንኮልና ሴራ በሚገባ ያውቁታል። አንድን አልበገርም ያለ ታላቅ ሕዝብ፤ ከፋፍሎ፤ አሳንሶና አዳክሞ እንደሚፈለጉት ለማድረግ የሚሸረበውን ሴራ ፕሬዚዳንቱ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ የማይታበል ሐቅ ነው። ከዚህም የተነሳ ኤርትራ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አገሪቱን እንደ ታይዋን እና ሲንጋፖር ለማድረግ ያወጡትን እስትራተጂ፤ ተግባራዊ እንዳይሆን በመንግሥታቸው ላይ የተለያዬ ማዕቀብ ሲጣልባቸው እንደቆየ ለማንም የተሰወረ አይደለም።

እንዲያውም የትግል አጋራቸው በነበሩት በወያኔ ሕወሃት መሪዎችና በሻዕብያ መካከል ጦርነት እንዲቀሰቀስ ሆኖ በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል የሚገኙ፤ ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ አገር ገንቢ ትኩስ ኃይል ወጣት ዜጎች ሰለባ እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህን አሳዛኝ ሁኔታ አስመልክቶ፤ የተከሰተውን ትራጀዲ፤ የመንፈስ ጠባሳና የኅሊና ወቀሳ፤ ሊታደግ የሚችል ምንም ዓይነት ሥራ ሊኖር አይችልም።

ምናልባት አለ የሚባል ከሆነ፤ እነዚህን ሳይወዱ በግድ የተለያዩ ሕዝቦችን እንደገና በማገናኘት የኢትዮጵያን ገናናነትና የሕዝቦቿን አንድነት የማይሹ ሴረኞችን፤ ቅስም በመስበር እየተነፋፈቁ ያሉ ሕዝቦችን በደስታ ማስፈንደቅ ይሆናል።

ምንጊዜም ቢሆን የኅሊና ዳኝነትን ማዳመጥ ተገቢ ነው። ተንኮል መጥፎ በሽታ ሲሆን በተለይ ደግሞ እልከኛነት ከክብር ያዋርዳል። ሟቹ ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ በሰው አእምሮ ሊታሰቡ የማይችሉ ብዙ ተንኰሎችንና መሠሪ ሴራዎችን ሲፈጽም ነበር። ነገር ግን ዕድሜው አጭር ሆነና የሚታወሰው በጥሩ ሥራው ሳይሆን በተንኮለኛነቱ ብቻ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ለአንዳንድ ቅን ሰዎች ቢሳሳቱ እንኳ የማሰቢያና የጸጸት ጊዜ በመስጠት ስሕተታቸውን እንዲያርሙ ዕድሜ ይቸራቸዋል።

እንደ ጸሐፊው እምነት ፕሬዚዳት ኢሳያስ አፈወርቂም ከእነዚህ ሰዎች እንደ አንዱ መስለው ይታዩታል። ምናልባት አንድ ቀን ወደ ኅሊናቸው ተመልሰው በሕይወት እያሉ የኤርትራንና የኢትዮጵያን ወንድማማች ሕዝቦች አንድነትን አረጋግጠውና የጠላቶቻችን ቅስም ሲሰበር በማየት ታሪክ የማይረሳው ታላቅ ሥራ ሠርተው የበለጠ ክብርና ሞገስ ይጎናጸፉ ይሆን? የሚል ግምት አለው። በዚህም ቆራጥ ውሳኔያቸው የዓለም የሰላም ኖቬል ተሻላሚ ሊያደርጋቸው ይችላል። ለማንኛውም ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ይርዳቸው!

-//-

 

8 Comments

 1. ቢሆን በጣም ደስ ይላል የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት እሰከ ዝምድና አስከ መዋለድ የደረሰ ግንኙነት ነው ያላቸው ለሚያውቀው እና ፈጣሪ ሁለቱን ህዝቦች ይርዳቸው

 2. ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ
  Are you joking………wake up. tewleden atasastu manem eritrawi mekelakel ayfelegem …………we know our history .
  take care for your words and be wise.

 3. “ለሰዎቹ ጥሩ መሀያ (ደመወዝ) እንሠፍርላቸዋለን’ በማለት ሲናገሩ፤” አባባሉን ትንሽ አወናበድከው እንጅ ለነገሩ ምሃያ ነው የሚባለው:: በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ እንዲሉት ግን፣ በዚህ አባባልህ ቴዎድሮስ ትግራዋይ ለመሆናቸው እና እስከ ቛራ ድረስም ወደ ትግራይ ገቢ መሆን እንዳለበት ይሄው ማረጋገጫውን አቅርብሃል::

  የአፄ ቴዎድሮስ ተቀናቃኞችን በስነስርአቱ አልቆጠርካቸውም፣ ቢያን የወሎዋን ወርቂት እና የላስታውን ገበዜን (በኋላ ንጉስ ተክለጊዮርጊስን) መጥቀስ ነበረብህ::
  ኢትዮጵያን ሳይሸጡ ተቀናቃኞቻቸውን እንዲወገዱ የፈቀዱ ከሚባሉ ተግባራት የካሳ ምርጫን የቴዎድሮስ አሳልፎ መስጠትን በመሰከርክበት አፍና ህሊናህ የተፈሪ መኮንንን ወደ አውሮፓ ከመሰደዳቸው በፊት ወደ ሰላሌ ድረስ ሄዶ በገዛ እጅ የእያሱን መግደልን አለማውሳትህ፣ tendentious የሆነ ትንተናን እንደምታካሂድ ያሳያል፣:: አናሊስስ ሲካሄድ ከወገንተኛነት ፈንተት ማለት እንድሚያስፈልግ አልደረክበትም ?

  የአውሮፓውያን ለንጥረ ሃብት አሻጥርን ግን በስነስርአቱ durchschauen አድርግሃል!

 4. ምን ኣይነት የቀን ሕልም ነው!!!! first the country of ethiopia was not established in the time of minelik (coz most of the land of oromia was not part of that abyssinia). Eritrea was legally established at the time pf italian coloniazation (1901-. ). so, stop writing a false history. And if u r thinking eritrea is a part of ethiopia, you are still asleep. Wake-up wake-up from your day dream.

 5. its fabricated and manipulated story…if the writer thinking that he is Ethiopian i would say shame on you. becouse even your own history written corruptly..i belived becouse of fabricated history of ethiopia may behalf million people have died in the past 60 years,and still people who are inferior complex creation un real nationalism in ethiopia as a result the country face great desaster
  So that please when you lies considered tomorrow ,becouse what are you write now is hold your future. Also when you write about eritrean history is a long jorney not as you metion star with italians colony . With out mention of previous history of Eritrea(Bahri negasi) it was a strong kingdom who help the abisenian kings during turkey invation egyption invation,and other civil war among war lords who realy assist and support and they had constitution since 1100 g.c .as well as we got the archiological evidence that pre history of egypt and the main land of kings residential places called puntland. So that there are many hidden history out of public but known by historian and politian…let me challenge you my brother do you know who is king theodros ..?hisotical evidences and books also found in uk.which is part of british stollen books and other real evidence.so that please dont fabricate history even if you hidden the truth but never stay hidden,you betten face the reality and give the people of ethiopia the truth of their back ground.may God bless Eritrea and Eritrea.

 6. The article is only for people who want to know true history as written. Not for those who have no ability to learn or who love falsehood. By the way the name oromo is foorcefully bestowed by Melese Zenawi when he drafted a law that punishes any one who does not use the word oromo in reference to those people by six months of jail. There was no oromo or oromia berore Melese, need to thank him for creating oromo oromia. Oromo and oromia has only a short life and history. The rest of the history belongs to the Ethiooian Galla and dont try to claim it. When eritrea was let go Ethiopia new it would loose little if any. Eritreans should also thank Melese for his contribution.

 7. የቀን ቅጀት (በህልም) የታየህ የውሸት ተረተረት የመሰለ እውነታ የሌለው መጻፍህ ያሳዝናል ታሪክ መርምር።።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.