ኤምባሲያችን ሀገርና መንግሥትን ወክሎ ለዘጎች ድህንነትና ጥቅም የቆመ የዲፕሎማሲ ምስዮን ውይንስ የእዝን አሰባሳቢ እድር ?

Embasyኤምባሲ በመሰረታዊነት በሁለት ሏላዊ ሀገሮች መካከል ሕግዊ ግንኙነት እንዲኖር የሚያደርግ ዲፕሎማሲያዊ ተቋም ሲሆን እንደ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስትመንት ፣ ባህል ፣ መከላከያ ፣ የልማት ትብብር ወዘተ ያሉ በርካታ ጉዳዮችን ይመለከታል ፡፡ እናም እነዚህ ኤምባሲዎች ግንኙነቶች በሚኖሩባቸው በሁለቱም አገራት ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ ኤምባሲዎች በሚገኙባቸው አገራት ለሚገኙ ዜጎቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት ይተባበራሉ ለሁገርና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትንም ለመፈጸም ዜጎችን ያስተባብራሉ ።

የጽሑፌ ዋናው ዓላም የኤምባሲን ተግባር ለመተንተን ፈልጌ ሳይሆን በምኖርበት ጀርመን አገር የሚገኘው ኤምባሲያችን የበተነው አንድ ደብዳቤ ይዘትና ትኩረት እጅግ በጣም አስገርሞኝ ነው ። ይሄውም ወንድማችን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ኢትዮጵያን ለመበታተን ባቀዱ ሴረኞች በለጋ እድሜው የጭዳ ዶር መደረጉ ሁላችንንም ያሳዘነና ያስቆጣን አረመኔያዊ ተግባር ነበር ። ድርጊቱ ተራ ወንጀል ሳይሆን የሀጫሉን ታዋቂነትና አወዛጋቢነተ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማፍረስና ሕዝቧንም ለመበታተን በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን የተሰረ አደገኛ ሴራ ነው ።

የአርቲስት ሀጫሉን ግዲያ ተከትሎ የብዙ ንጹኃን ዜጎቻችን ህይወት አልፏል ፣ ሀብት ንብረት ወድሟል ፣ ምግብና መጠለያ አጥተው የድረሱል ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው ። ታዲያ የዘር ማጥፋቱን መታደግ ቢያቅተው አሁን ሜዳ ላይ ተበትነው የሚገኙ ዜጎቻችን ጊዜ የማይሰጥ የነፍስ አድን እርዳታ የማቅረብ ጊዴታ ያለበት መንግሥትና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኤምባሲዎቻችን ለአንድ ግለሰብ ቤተሰብ እርዳታና ሀውልት ማሰሪያ ገንዘብ አዋጡ ማለት እጅግ በጣም አሳፋሪና መሀይምነት ጭምር ነው ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በዜጎቿ ትብብርና ርብርቦሽ ቢቻ ሊቀረፉ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስላሉ መንግሥትን የሚጠቀመው የኛ አንድ ላይ መሆን እንጂ እንዳለፈው መንግሥት እኛን ከፋፍሎ ጎራ ለይቶ በመደገፍና በማጥቃት ሊሆን አይችልም ።

ይህ ኤምባሲው የበተነው ደብዳቤ ከሰብአዊነትና ከቅን አሳቢነት ወይንም ለሟቹና ለቤተሰቡ ከማሰብ የቀረበ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ሰብአዊነትና ቅንነት ቢሆን ኖሮ አንደኛ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ። ሁለተኛ የአሁኑም ቢሆን ሁሉንም ተጎጂ ያካተተ በሆነ ነበር ።

ከሁሉም በላይ መንግሥትን ፣ ሀገርንና ሕዝብን ወክሎ በባኢድ ሀገር የሚገኝ የኤምባሲ ሰራተኛ ሆን ብሎ ሊከፋፍለን ካልሆነ በቀር ማንም ተራ ሰው ሊረዳው የሚችለውን ተሳስቶ ነው ብሎ መቀበል ይከብዳል ። ካልሆነም ድግሞ እንዳገር ቤቱ በመንግሥት መዋቅር ከተሰገሰጉ ጸረ ለውጥ ኃይሎች ጋር አብረው የሚሰሩ ግለሰቦች መኖራቸውን አመላካች በመሆኑ ዶክተር አብይ በነካ እጃቸው ቢጎበኙ ቢጠቅማቸው እንጂ የሚጎዳቸው አይመስለኝም ።

ለማጠቃለል በጀርመን የሚገኘው ኤምባሲ ገና ከፊታቸን የሚጠብቀን የድጋፍ ጥያቄዎች መኖራቸውን እያወቀ እንዲህ አይነት አስነዋሪና ከፋፋይ ተግባር ውስጥ ለምን እንደገባ ማብራሪይ እንዲሰጠን በአክብሮት እጠይቃለሁ ።

በቅንነት ኢትዮጵያን እንታደጋት

ከድሉ

2 Comments

  1. በያንዳንዱ ሀገር የሚገኙ ኤምባሲዎች በነገድ ተዋጽኦ ሳይሆን ምልመላው በችሎታና ሀገርን በመውደድ ላይ ያተኮረ ቢሆን መልካም ነው። ከትያትሩ በላይ ትያትር የሆነው ግን የውጭ ጉዳይ የተሾመው አምባሳደሮቹና ሰራተኞቹ በኦሆዴድ ከተሞሉ በሁዋላ ነው።
    እግዚሀር ያሳያችሁ ሱሌይማን ደደፎ የግብጽ አምባሳደር ነው ወይስ የኢትዮጵያ
    ? ደሞዙን ግን የምንከፍለው እኛ ነን መታሰሩንም ሆነ ወደ ሀገር መጠራቱንም አልሰማንም። ውጭ ጉዳይ በሱ በኩል ያለውን መግለጫ ይሰጥበታል ብለን እንጠብቃለን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.