አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ

dawud Ibsa 300x267 1ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ተመልሰው የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ። አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው ። ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ የነበረው ስብሰባ ዓላማውን ባልተረዱ ሰዎች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶበት በግንባሩ ላይ ብርቱ ጉዳት ማስከተሉን አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።

«አሁን ከስብሰባው ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዥንብር ብዙ ጥፋት ተከስቷል። መጠነ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲከፈት ነበር። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጠላትነት የመፈረጅ ስራ ውች ሀገር ባሉ በግንባሩ አባላት እና ደጋፊዎች ሲከናወን ቆይቷል። «አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየን ነው በጣም አጥፊ ተግባር ነው » በግንባሩ ውስጥ ተፈጠረ ችግርም አቶ ዳውድ ኢብሳ ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታልም ብለዋል አቶ ቀጄላ ፡፡

አያይዘውም አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ከግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ ጋር መወያየታቸውን ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።ዶይቼ ቨሌ ዛሬ ከሰዓቱን ጉለሌ ከሚገኘው የግንባሩ ጽህፈት ቤት አከባቢ እንደተመለከተው በቢሮው መግቢያ በር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተቀምጠው ከመጠበቃቸው ውጭ ምንም እንቅስቃሴ አላስተዋለም፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በአቶ ዳውድ ስልክ ላይ ደውሎ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ የእጅ ስልካቸው ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዞን ዘጠኝ ተከሣሾች ላይ ዶሴ የአቃቤ ሕግ ምስክር ተሰማ - VOA

2 Comments

  1. He should be jailed than stay hostage at his home. He has committed at log crime, may be the government searching evidence for the crime he did. I hope he would be at prison where he deserve.

  2. ይሄ ሰውዬ አርባ አመት በስልጣን ላይ ነበር። ዶር አብይ ደክሞታል ይብቃህ ማለቱ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው?እኔ አዝኖለት መሰለኝ ይሄ ሰውዬ ስልጣን ላይ ቢወጣ እንዴት ነው የሚለቀው? የኣነግ ሙጋቤ ማለት ነው። ባይሆን ብቻውን እንዳይሆን አረጋዊ በርሄን ብርሀኑ ነጋን መራራ ጉዲናን ሌንጮ ለታን አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ይብቃችሁ እጅ እጅ አላችሁ ብሎ ራቅ አድርጎ መውስድ ነው እንዳይመለሱ። እነሱ እያሉ ያ ሀገር ሰላም ያገኛል ማለት ዘበት ነው ትግሬዎቹን እግዚሀር በጥበቡ እንዳይመለሱ አድርጎ ልኳቸዋል።እነዚህ ግለሰቦች አእምሯቸው ያለ መከራ የሚያፈልቀው የለም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.