የወያኔ፣ ኦነግ ሸኔና ጅዋር ህገወጥ የሳተላይት መቀበያ የስለላ መሣሪያና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት!!!›› (ክፍል አንድ) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ET67ያሰብከው ዓላማ አልሆን ብሎ ቢከሽፍ፤ ሁኔታው ሲጠጥር፤ ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን  ወጥር፡፡

(ኃይሉ ገብረዮሐንስ(ገሞራው)

የኢትዮጵያ ሃገራችን ብሄራዊ ደህንነት National Security በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ ሃገራት ድጋፍ የሚከወን የፖለቲካ ሴራ በሃገራችን አመፅ ብጥብጥና ሁከት እንዲስፋፋ የሚያደርጉ መኃል ሁለት ዓይነት ህገወጥ ዝውውሮች ውስጥ የገንዘብና የመሳሪያ ዝውውር ኡደቶችን የሚያሳዩ የከረሙ ዜናዎች በናሙናነት እንጠቅሳለን፡፡

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፡-በህገወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 10 ሚሊዮን ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ›› ሀምሌ 14/2010 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ከማል በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ዘመቻ  በሞጆና አዳማ መካከል በተካሄደ ዘመቻ 570 ሽህ ዶላር ተይዞል፡፡ በተመሳሳይ አንበሳ ባንክ  ደሴ አካባቢ 24 ሚሊዮን ብር መያዙንና ተጠርጣሪዎቹ ‹‹ከአንድ ባንክ አውጥተን ወደ ሌላ ባንክ ልናስገባ ነው›› በሚል ስበብ ወደ መቐለ ለማሸሽ የተደረገው  ዘረፋ በህብረተሰቡ፣ በፖሊስና በጸጥታ አካላት ተይዘዋል፡፡

ህገ ውጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፡-ከአንድ ሽህ በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና ከ80 ሽህ በላይ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደ ዘመቻ 234 ሽጉጥ፣ 17 ሽህ ጥይት ተይዞል፡፡ አርማጭሆ 298 ሽጉጥ፣ሸኞ 53 ሽጉጥ፣   ሰሜን ሸዋ 20 ሽጉጥ 1 መትረየስ መያዛቸውንና ተጠርጣሪዎቹ  በቁጥጥር ስር ውለው ምርምራ እየተካሄደ ነው፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር ምስረጋና ይገባቸዋል፡፡ መቐለ የመሸገው ፀረ-ዲሞክራቲክ የህወኃት ኃይል የጦር መሳሪያ ዝውውር በኢትዮጵያ ውስጥ እያደረገ ይገኛል!!! በተመሳሳይ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ቡን ውዊ ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ካለው ሰፊ የድንበር ወሰን ጋር ተያይዞ ህገ ውጥ የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ፣ ደምቢዶሎ በኩል እየገባ ይገኛል፡፡ በሃምሌ 14/2010  በጋምቤላ ክልል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ  ዝውውር 10 የእጅ ቦንቦችና 69 የጦር መሳሪያ እንዲሁም  32 ክላሽንኮቭ፣ 2 መትረየስ፣ 3 የብሬን መትረየስ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር ውሎል፡፡ መቐለ የመሸገው ፀረ-ዲሞክራቲክ የህወኃት ኃይል የጦር መሳሪያ ዝውውር በኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ ይገኛል!!!  ከዚህ ህገወጥ የገንዘብና መሣሪያ ዝውውር በኃላ የህዝብ ግጭት፣ የድንበር ግጭት፣ የብሄር ብሄረሰብ ግጭትና የኃይማኖት ግጭት የተነሳ የሰዎች ሞት፣የንብረት ውድመት፣ የህዝብ መፈናቀልና ሰደት ይከተላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ መንግሥት በፍቅራቸው ጊዜ ለጅዋር መሃመድ ጠባቂ አንጋቾች መደበለት፣ በፀባቸው ጊዜ ጠባቂዎቹን በድቅድቅ ሌሊት ሊያነሱበት መሆኑን በድብቅ ባስገባው ሚስጢራዊ የሰለላ ሳተላይት መገናኛ  በስለላ ሲደርስበት  ጅዋር መሃመድ ተከብቤለሁ ድረሱልኝ ቄሮን አለ፡፡ በዛን ምሽትና በማግስቱ  86 ሰዎች  በዘር ፍጅት /ጀኖሳይድ ተገደሉ፡፡ ጅዋር የኢትዮጵያ መንግሥትና የግል ተቋማትን በመሰለል ባገኘው መረጃ ‹‹እኛም አውቀናል ጉድጎድ ምሰናል!!!›› ብሎ ፎክሮ ነበር፡፡   የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) አንድም ጁሃር እንዴት ይህን መረጃ እንደአገኘ ከአወቀ በኃላ እንዳላወቀ በማስመሰል የሳተላይት መቀበያ እንዳለው አውቀው አዘናግተውታል፡፡ ለዚህ ፍንጩ የጅዋር ቤት በፍርድ ቤት ትእዛዝ በድጋሚ በእንዲፈተሸ የተደረገው ሌላም መገናኛ እናዳለው ያውቁ ስለነበር ይመስላል፡፡

‹‹ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ ከአቶ ጃዋር ቤት ማግኝቱን ፖሊስ ተናገረ

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘውና በቅርቡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) የተቀላቀለው የአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ሲበረበር፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ መገኘቱን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የምርመራ ቡድኑ ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በተፈቀደለት የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜያት የሠራውን የምርመራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፣ የአቶ ጃዋር ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ሲበረበር የተለያዩ ሲዲዎች፣ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፍላሾች፣ ኢንተርኔት ለየት ባለ ሁኔታ የሚጠቀሙበት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጪ የሆነ የሳተላይት መሣሪያ ተገኝቷል ብሏል፡፡››1

ሚሥጢራዊ የሰለላ ሳተላይት መገናኛ ያላቸው ፓርቲዎች

ህገወጥ የስለላ መገናኛ መሣሪያዎች ያለ ቴሌኮሙኒኬሽን ፍቃድ ወደ ሃገር ቤት በሚስጢር መግባት የጀመረው በህወሓት ኢህአዴግና ኦዲፓ ብልፅግና ፓርቲዎች ዘመን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ በግለሰብና በፓርቲ ደረጃ በህቡዕ የሳተላይት መገናኛ አገር ውስጥ በተለያዩ ጊዜ መግባታቸውን ኢህአዴግና ብልፅግና መንግስት በተለያየ ጊዜ በመገናኛ ብዙሃንና በሚዲያዎች ገልፀውልናል፡፡  በግለሰቦች (ኢያሱ በርሄና በጅዋር መሃመድ) እንዲሁም  ዛሬም የአገሪቱ ኢትዮ ቴሌኮም የማያውቀው ህገወጥ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ  በህወሓትና ኦነግ ሸኔ እጅ እንዳለ ፍንጭ ያሳያል፡፡ ወያኔና ኦነግ ሸኔ ከሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ኢንባሲዎች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ የስለላ መገናኛ መሣሪያዎች ደብቆ በመጠቀም የሃገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት (National Security ) ያናጉ በመሆኑ በህዝብና የሃገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም በፍርድ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡

የፖለቲካ ሴራ በህወሓት፣ ኦነግ ሸኔና በጀዋር መሃመድ በጋራና በተናጥል የተቀነባበሩ ሴራዎች እጃቸው እንዳለበትና እንደሌለበት በዚህ ህገወጥ የስለላ መገናኛ መሣሪያዎች ምን እንደተሰራ መጣራት አለበት እንላለን፡፡

(1) የሰኔ 15 ቀን 2010ዓ/ም ከአንድ ዓመት በፊት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ በዶክተር አብይ አህመድ ግድያና የቦንብ ፍንዳታ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ወንጀለኞች እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረቡም፡፡

(2) የሰኔ 16 ቀን 2011ዓ/ም በአማራ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ላይ ባህር ዳር የተፈጸመ ግድያ የዶክተር አንባቸው መኮንን፣ ምግባሩ ፣ እዘዘው፣ ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣  የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄኔራል ገዛዒ አበራን በመኖሪያ ቤታቸው በጠባቂያቸው  በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል የተባሉት   ወንጀለኞች እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረቡም፡፡

(3 ) የሰኔ 22  ቀን 2012ዓ/ም  ከምሽቱ 3፡30 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ያለፈው ሃጫሉ ሁንዴሳ በምርመራ መጣራት ይኖርበታል፡፡ በዘህ የተነሳ የተካሄደው የዘርና የሃይማኖት ተኮር ፍጅት/ ጀኖሳይድ በተደጋጋሚ ጊዜ እየተድበሰበሰ ማለፉ ለቀጣይ ጀኖሳድ እያዘጋጅን ነው የሚል  እምነት በተጠቂው ህብረተሰብ ዘንድ ዓለም ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ሆኖል እንላለን፡፡ ከ1983ዓ/ም የወለጋ የአማራ ሰፋሪዎች እልቂት ጀምሮ፣ በሐረር ኢንቁፍቱ ገደል፣ የበደኖ፣ ጉራፈርዳ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣  የሱማሌ ወዘተ ወዘተ የዘር ፍጅት ሁሉ ማስረጃ ተዘጋጅቶል፡፡ የፌዴራል መንግሥትና የክልል ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ሕገ-መንግሥት ላይ የሠፈረው ‹‹በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች›› አንቀፅ  29 መሠረት  ‹‹ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ህጎች ‹‹በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች›› ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅነት ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡ በህግ አውጭው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡›› ሰለሚል መቼም ጊዜ ቢሆን ማስረጃዉን አቅርቦ ወንጀለኛውን ይዞ መፋረድ ይቻላል፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙት ሰዎች ለፍርድ ቀርበው ፍርድ ያገኛሉ ብሎ የጥቃቱ ሰለባዎች መንግስት ላይ እምነት አጥተዋል፡፡

ብሄራዊ ደህንነት National Security

በጅዋር መሃመድ አካውንታቸው የተጠለፈ ባለሥልጣናት ዶክተር አብይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ ዳንኤል ክብረት፣ ዶክተር አለሙ ስሜ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ሺመልስ አብዲሳ፣ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ ኢታማጆር ሸም፣ ምክትላቸው ብርሃኑ ጁላ፣  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ እስክንድር ነጋ፣ እንዲሁም የህወሓት ሹማምንቶችን መረጃዎች በመጥለፍ፣ የስልክ ምልላሳቸውን በማዳመጥ የስለላ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ታውቆል፡፡

የሃገራችን ‹‹የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ›› (Information Network Security Agency) ብሔራዊ ደህንነታችንን ሊያስጠብቅ አልቻለም፡፡

  • አሁንም መቀሌ በመሸገው የህወሓት/ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ የያዙት ኢንሳ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን ዘመናዊ የስለላ መሣሪያዎች ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ወስደው እንደገጠሙ የቅርብ ጊዜ መረጃ ነበር፡፡
  • ሌላው ኦነግ ሸኔ የእራሱ የሆነ የሳተላይት መገናኛ እንዳለው፣ በወለጋ ኢንተርኔትና ስልክ ግንኙነቶች በተቆረጡ ጊዜ ዲሪባ ኩምሳ /ጃል መሮ ለባህር ማዶ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠይቅ ያካሂድ እንደነበረ ማስረጃዎች አሉ፡፡
  • ሌሎች ፅንፈኞችም ከቤታቸው ውስጥ ሆነው የሚጠቀሙበት የሳተላይት መሳተላለፊያ ሊኖር ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡
  • እንዲሁም በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ኢንባሲዎች ለፅንፈኛ ቡድኖች ጥላና ከለላ በመሆን አገልግሎት ሊሰጡ ስለሚችሉ ክትትል በማድረግ መያዝ ይቻላል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=dnJ6b07ToTc/ጥብቅ መረጃ(ምሥጢር)፦ በጃዋር አካውንታቸው የተጠለፈ ባለሥልጣናት እነማናቸው?-”

 

‹‹መርማሪ ቡድኑ እንዳብራራው የድምፃዊው ግድያ ከተፈጸመ በኋላ አቶ ጃዋር ባስተላለፈው ትዕዛዝ በአዲስ አበባ የ14 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን፣ በኦሮሚያ ክልል የወደመውን ንብረት ግምት ገና በመሥራት ላይ ቢሆንም፣ የ167 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በአጠቃላይ የ181 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበሉንም ገልጿል፡፡ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ አመፅና ዕልቂት እንዲፈጠር ጥሪ መተላለፉንና በርካታ ንብረቶች እንዲወድሙ መደረጉን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ፣ ይህንን ድርጊት የሚያረጋግጡለት የ34 ሰዎች የምስክርነት ቃል መቀበሉን፣ 14 የምርመራ ቡድኖች በማዋቀር ከፍተኛ ጉዳት ወደ ተፈጸመባቸው ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ ምሥራቅ ሐረርጌና የተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ለምርመራ መላኩን ጠቁሟል፡፡››

 

‹‹ቡድኑ የታጠቃቸው የጦር መሣሪያዎች ከማንኛውም (ከክልልም ሆነ ከፌዴራል) መንግሥታዊ ተቋም ወይም የሚመለከተው አካል ፈቃድ እንዳልተሰጣቸው ማረጋገጡን መርማሪ ቡድኑ ተናግሮ፣ ይዘዋቸው የነበሩት የጦር መሣሪያዎችም አሥር ክላሽኒኮቭ ጠብመንጃዎች፣ አንድ ቺቺና ዘጠኝ የሬዲዮ መገናኛዎች መሆናቸውን፣ በእነዚህ የጦር መሣሪያዎች ሌላ ወንጀል መሠራት አለመሠራቱን ለማረጋገጥ ለምርመራ መላኩንም አስረድቷል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌና በሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች 181 ሰዎች መሞታቸውንና ጠቅላላ ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙን ጠቁሞ፣ የቡድኑ ዕቅድ የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ለአሥር ቀናት አዲስ አበባ በማቆየት ቀጣይ አመፆችን ለማቀጣጠል እንደነበር የሚያረጋግጡ ምስክሮችን ቃል መቀበሉንም አስረድቷል፡፡››

 

‹‹ወደ ክልል የተላከው መርማሪ ቡድን የሞቱትን፣ የቆሰሉትንና የወደመውን የንብረት ዓይነትና መጠን በማስረጃ መለየት፣ ያልተያዙ ግብረ አበሮችን መያዝ፣ ያስተላለፈውን የአመፅ ቅስቀሳ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሚመለከተው [ከተጠርጣሪው] መቀበል፣ በብርበራ የተገኙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ምርመራ ውጤት ለመቀበል፣ ለተለያዩ ተቋማት የተጻፉ ደብዳቤዎችን ምላሽ ለመጠበቅ፣ የሕክምና ማስረጃዎችን ለመቀበል፣ ከኦኤምኤን ጋር ያለውን ግንኙነት በሚመለከት የሚደረግ ምርመራ፣ በአዲስ አበባ ውጥረት ለመፍጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር ያለውን ግንኙነት መመርመር፣ ቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል፣ በሞባይሎች የተላለፈውን የአመፅና ብጥብጥ ቀስቃሽ ጥሪ መመርመርና የባለሙያ ትንተና ለማሠራት፣ በኦኤምኤን የተላለፈ የአመፅ ጥሪ ከብሮድካስት ባለሥልጣን ለመቀበል ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡››

 

‹‹ማስረጃ ማሰባሰብን በሚመለከት ድምፃዊው እንደ ሞተ ወዲያውኑ በኦኤምኤን በቀጥታ አመፅ ቀስቃሽ መልዕክት ማስተላለፉን፣ በሌላ የምርመራ መዝገብ የተካተተውና ነጋዴ መሆኑ የተገለጸው አቶ ሐምዛ ቦረና  (አዳነ) የተካተተበት ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ሁሉም ሕገወጥ ታጣቂዎች እንደነበሩ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩና ለልዩ ጥበቃ ሥልጠና የወሰዱ መሆናቸውን መርማሪ ቡድኑ ገልጾ፣ ያለ ምንም መልቀቂያ በራሳቸው ፈቃድ ተቋማቸውን ለቀው የአቶ ጃዋር አጃቢ መሆናቸውንም አክሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በሕገወጥ መንገድ በታጠቁት የጦር መሣሪያ በመታገዝ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የድምፃዊ ሃጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ በመሸኘት ላይ እያለ ቡራዩ  ሲደርስ፣ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈትና አስከሬኑን በግዳጅ በማስመለስ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት እንዲገባ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡ በዚህ ወቅት አንድ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባል መገደሉንና ሦስት መቁሰላቸውን፣ በአሥር ምስክሮች ማረጋገጡንና ከላይ በአቶ ጃዋር ምርምራ ላይ የገለጻቸው የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን አስረድቷል፡፡ አብዛኛው የማስረጃ ዝርዝር በፎረንሲክ መረጋገጡን፣ ሁከት፣ ብጥብጥ፣ የሕይወት መጥፋትና ንብረት ውድመትን በሚመለከት በግልና በመንግሥት ተቋማት ላይ በአምስት ክፍላተ ከተሞች (በአዲስ አበባ) ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት መድረሱንም ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉ 43 ተጠርጣሪዎችን ቃል መቀበሉን፣ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ስለሞቱ ሰዎችና ስለወደሙ ተቋማት በደብዳቤ መጠየቁንና በአጠቃላይ ምርመራው ውስብስብና ሰፊ በመሆኑ በላይ ከአቶ ጃዋር ምርመራ ጋር በተያያዘ የተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ በእነዚህ ተጠርጣሪዎችም ላይ ስለሚቀረው፣ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት መርማሪ ቡድኑ ጠይቋል፡፡››

አሁን በተገኘው መረጃ መሠረት ጅዋር መሃመድ ግብፅ እንደጠለፈው አድርጎ እሱ የሳይበር ጥቃት ይፈፅም እንደነበር  https://www.youtube.com/watch?v=dnJ6b07ToTc  ድረ-ገፁ ይጠቁማል ያዳምጡት፡፡

‹‹በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን መንግሥት ገለጸ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው መካከል ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይገኝበታል፡፡ ግብፅ በህዳሴ ግድብና በአጠቃላይ የዓባይ ውኃ ላይ ያላትን ጥቅም አስከብራለሁ የሚል ቡድን በኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ተቋማት ላይ ፈጽሞት የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን፣ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) አስታወቀ። ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች፣ በ13 የመንግሥትና በአራት መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድረ ገጾች ላይ መፈጸማቸውን ኢንሳ አስታውቋል። ጥቃቶቹ በዋናነት የተፈጸሙት ከዓርብ ሰኔ 12 ዓ.ም. ጀምሮ እንደነበር የገለጸው ኢንሳ፣ የጥቃት ሙከራው ያነጣጠረው በአገሪቱ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶችና የግል ድርጅቶች ላይ እንደነበር አስታውቋል፡፡

የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆረስ ግሩፕ (Cyber Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security By Pass) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኢንሳ ጨምሮ ገልጿል፡፡ የሳይበር ጥቃቱን ፈጽመዋል ከተባሉት ቡድንኖች መካከል፣ ሳይበር ሆረስ ግሩፕ (Cyber Horus Group) የተባለው ጥቃቱን በኢትዮጵያ የመንግሥት ተቋማት ላይ መፈጸሙን አል መስሪ አል ዩም በተባለ የዓረብ ሚዲያ ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ አስታውቆ ነበር። ሳይበር ሆረስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከርና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ በማለት ራሳቸውን የሚጠሩት ሦስቱ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ስለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደወሰዱ፣ ኢንሳ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዋና ዓላማቸውም በህዳሴው ግድብ ላይ በተለይም ከግድቡ ውኃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተፅዕኖ በአገሪቱ ላይ ለመፍጠር መሆኑን ቡድኖቹ ራሳቸው መግለጻቸውን ከኢንሳ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኞቹ በድረ ገጽ ግንባታ ሒደት ደኅንነታቸውን ታሳቢ ያላደረጉ፣ እንዲሁም የደኅንነት ፍተሻ ያላደረጉና ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው እንደሆኑ ኢንሳ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡ ኢንሳ አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ምክንያት ይህን መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ባይችል ኖሮ ጥቃቱ በአገሪቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖሊቲካዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር አስታውቋል፡፡ በመከላከሉም ሊደርሱ የሚችሉ ከፍተኛ አደጋዎችን ማስወገድ መቻሉንና ይኼንንም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አረጋግጧል፡፡ ወደፊት መሰል ጥቃቶች በስፋት፣ በረቀቀ መንገድና ከተለያዩ ሥፍራዎች ሊሰነዘር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት “.et domain” ከመጠቀማቸው በፊት የድረ ገጻቸውን ደኅንነት አረጋግጠው እንዲጠቀሙ፣ ራሳቸውን ከሳይበር ደኅንነት ተጋላጭነት ለመከላከል አስፈላጊዎቹን የጥንቃቄ ዕርምጃዎች መውሰድ እንደሚኖርባቸው አሳስቧል። ተቋማት ከኢንሳ ጋር በመተባበር የደኅንነት ተጋላጭነታቸውን መድፈን እንዳለባችው፣ የተለያዩ የሳይበር ደኅንነት ጥቃት ሙከራዎች ሲያጋጥሟቸውም ሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሲያሻቸው ለኢንሳ በማሳወቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉም አስታውቋል።››የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ግብፅን የስለላ ድርጅት አከርካሬውን መታሁ እያለን እንዴት ጅዋር ማሃመድ ወጥ በወጥ አደረጋቸው። የሃገሪቱ ብሄራዊ ደህንነት በሳይበር ጥቃት በተደጋጋሚ የሚፈፀምበት በሃገር ውስጥ መቐለ ከመሸገው ህወሓት/ ኢህአዴግ የቀድሞ የፀጥታና ደህንነት መስሪያ ቤት  ሹማምንትና ኢንሳ ሹም አለመሆኑን በምን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

 

የሃገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ለማስከበር እንታገል!!!

የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ልደቱ አያሌው፣ ምስራቅ ክፍሌ፣ አስቴር ስዩም  ይፈቱ!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!! የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!

 

ምንጭ

 

 

2 Comments

  1. ምኑን አለነው ጁዋርን የመሰለ ተራ ሰው ይምስጢር ቋቱ እጁ ከገባ ለምን አይሳቅብን? ባለ ስልጣናቱ የሚያወሩትን ዳውድ ኢብሳ በቀለ ገርባ ጌታቸው አስፋ እነ ብርሀነ እነ ሻቢያ እየስሙ ይስቁብናል ማለት ነው ምስጢር የሆነው ለዜጎች እንጅ ጠላት የእለት ተለት መረጃ እጁ ላይ ነው ማለት ነው። አይ አገሬ ወደ ቀድሞ ክብርሽ። መች ትመለሽ ይሆን?

  2. No party, individual or group above Ethiopia then, the government should proceed the law enforcement in the country, a tremendous amount of crime committed in the country by racist party,group or individual betraying the country, they all death sentence.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.