ዖሮማራ የኢትዮጵያ ዋርካ ነው – ከአባዊርቱ

 መግቢያ!
images“ዖሮሞዎች”  ብለን  በጥቅሉ ሁሉን ትውልደ ዖሮሞ አድሬስ ማድረግ  እራሱ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነው። ሁሉን በዘውግ  አመለካከት ከፅንፈኞች ጋር በመደመር የፖለቲካ ሂሳብ የምናወራርድ ከሆነ  ለሀገራችን ሀገረ መንግስት ግንባታ እንቅፋት ከመሆን ውጪ እንጮህለታለን  ለምንለው ማህበረሰብ የምናተርፍለት ነገር አይኖርም። ትናንት ኢትዮጵያን የገነቡት እነ ራስ ጎበና ዳጪ ፣  ሀብተጊዮርጊስ ቢነግዴ ከኦሮሞነታቸው በላይ በኢትዮጵያዊነታቸው ደምቀው ነበር ኢትዮጵያን ወዲህ ወደኛው ዘመን ያሻገሩልን። ገናናው ራስ አበበ አረጋይ የሸዋ አርበኛ እናታቸው የጎበና ዳጪ ሴት ልጅ ናቸው:: የሸዋ ሀገር ገንቢዎች የዛሬይቱ ዘመናዊ ኢትዮጵያ መስራቾችም ማለት ይቻላል -ዖሮማራዎች – ነበሩ::አብዛኛው  ሸዋ ዖሮሞም አማራም ነው:: ይህ በታሪክ ሳይሆን ዛሬም በህዝብ ውስጥ ያለ የማይሸሽ  ሀቅ ነው። የአቢይም መንግስት የማይነቃነቅ ግድግዳ የማይመዘዝ ሀረግ የሚሆነው ልክ እንደ ቀዳማዊ ሀይለስላሴና ዳግማዊ ምኒልክ በጥበብ ይህን የዖሮማራ ሀይል ስለሚመራ ነው:: ለፅንፈኞች ኢትዮጵያዊነቱ  ይጎረብጣቸዋል:: አይምሰላችሁ የእነሱ ትግል ከአማራው ህዝብ ጋር አይደለም:: ይህ ስትራቴጂያቸው  ነው። ለነሱ ትግሉ ከሀገረ ኢትዮጵያ ህልውና ጋር ነው። አቢቹ የማይመችና የማይደረመስ ምሽግ ስለሆነባቸው ዖሮሞነቱን እስከመካድ ደርሰዋል ከቁብ አልቆጠራቸውም እንጅ።
ዖሮሞን በጅምላ የምትወንጅሉ የአማራ እክራሪዎች (በተለየ መንገድ የአቶ አቻምየለህ ከአክራሪዎች ጋር እሰጥአገባህ ለሁላችንም የተረፈ ውግዘትና ስም ማጥፋት ስለሆነ ምን ጥቅም አለው? )  የእስክንድር ነጋ አዲስ አበቤዎች፣ የጌታቸው ሽፈራው በረራ አማሮች …..እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ቆም ብላችሁ አስተውሉ። የበረከት ስምኦንና መለስ ዜናዊ የ27 አመት ጥበብ ዋናው የኦሮማራን ጥምረትና መስተጋብር የመበጣጠስ ችሎታቸው ነው። ሌላ ምንም አይነት ሳይንሳዊ የሆነ መሰረት አልነበራቸውም። መስተጋብሩን ለመበጣጠስ ደግሞ ከጫካ ጀምረው በልጅነታቸው ተማምለውበት ስለነበረና እቅድ በመያዛቸውም ነበር። ይህን በጭራሽ መርሳት ማለት የኡትዮጵያን መሰረት እንደመክዳት ነው። በየሚዲያው ሺህ  የፅልመት ዲጂታሎች ምን ቢናኙ የምናውቃቸውና በእጅ የምንዳስሳቸው ኢትዮጵያውያን የተባሉት መላልሰው የሚሰሩት ስህተት ህዝብን በጥቅሉ ከጥቂት ከሀድያን መለየት አቅቷቸው ሲዋትቱ ማየትን ያህል ደግሞ የሚያም ነገር የለም። እስቲ በምሳሌ እና በግልፅ እንነጋገረው።
ከሀጫሉ በግፍ መገደል በሁዋላ በውጭው አለም ጁዋርና ዖነግ ክፉኛ አይምሯቸውን የሰረቋቸው ህጻናትና የአዋቂ ነፈዞች ፣ በቁጥር እዚህ ግቡ የማይባሉ እየተቧደኑ አገራችንን አውግዘዋል፣ ትሁቱና ቀናውን አቢይ ረግመዋል። ኢትዮጵያን በመርገማቸው የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ልብ እንደሰበሩ ይሰማኛል – ከተሰባሪዎቹ አንዱ ነኝና። ሆኖም በአፀፋው የሚሰጠው ምላሽ ዖሮሞን እንደ ህዝብ የሚያጣጥል በጭራሽ መሆን የለበትም። ከመሀላችን ሆነው የዚህን ጩኸትና ዋይታ ከፍ የሚያደርጉት ገዳዮቻችን እራሳቸው መሆናቸውን የማይጠፋችሁ ሁላችሁም ናችሁ እንግዲህ ዋይታውን ዖሮሞን በማውገዝ ከምትተባበሩ በዖሮማራና ሌሎች ወገኖች በአንድነትና ባንዲራ ደምቃችሁ በህብረት እንደማሳፈር ጭራሽ ለአቢይ ሰርግ ጥሪ የደረሳችሁ ይመስል የአንድነቱንም ሰልፍ የምታወግዙ ኢትዮጵያውያን ነን ባዮችን አስተውለናል። ለዚህም ይሆናል ፅልመትና ከሀድያን የሚፈነጩብን። እየተስተዋለ እንጅ ። እኛ የአንድነት ሀይል ተብዬዎች እጅ ለእጅ ሳንያያዝ ቀርተን አክራሪ ” ቹ”  ብሎ የላከብንን ደናቁርት ከልጆቻችንና ወንድሞቻችን ለመከላከልና በብቃት ለመመከት ሳንችል ቀርተን ጣታችንን ወደ ህውሀትና አክራሪ ወይም አለመታደል ሆኖ ወደአቢይ መቀሰሩ ሶሉሽን አይሆነንም ።
 በተንኮልና ጥላቻ  የተገመደው ለዘረፋ ብቻ በስልት የተነደፈው የፌክ ፌዴራሌ የህውሀት  27 ምናምን አመታት መጫኛ በኦሮማራ ልጆች በለማ፣ አቢይ፣  ደመቀና ገዱ ተበጣጠሰ::  ካለፈ በሁዋላ መቼስ ይረሳል እንጅ ዛሬ ሁሉም የድል አጥቢያ አርበኛው የዳውድ ኢብሳው አይነቱ መሀል ሸገር ላይ ሲሻው ሸኔ ሆኖ ሲበርድለትም ጨዋ ተቃዋሚ ሆኖ ክራቫቱን አሳምሮ የሚንጎማለለው እነዚሁ የለውጥ ደቀመዛምርት በመሩት ታላቅ ተጋድሎ ነው። አንዳንዶችማ ዘግይተን እንደሰማነው ህይወታቸውን ሁሉ አስይዘው ነበር ለዚህ ያበቁን:: ዶር አቢይ ምናልባት ለዖሮሞም ህዝብ ባልተናነሰ ከሆነ ከዳውድ ቢጤው የአስመራ ሽፍታ በወያኔ መዳፍ እጅ ሆኖ ለዖነግ ውለታ ሰርቶለታል። እናም  ለውጡን አሻግሮ  በብልሀት የሚመራውና የሚያስተጋብረው  ይህ የሀገር አደራ ያለበት ኦሮማራ እንጅ የዳውዱ ዖነግ፣ የመረራው ኦፌኮ፣ ወይም የጁዋሩ ተወርዋሪ የፅልመት ወታደር አይደለም:: የኛን ዘመን  ዖሮማራ ልዩ የሚያደርገው ግን  ሶማሌውን፣  ደቡቡን አፋርና ጋምቤላውን በእኩልነት  አስተናግዶ በቅኝት አገሪቱን በብልጽግና ጎዳና ሲመራ ለማየት በመታደላችን ነው:: ማን ያውቃል የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሶማሌ ክልልም ሊሆን ይችላል:: ደግሞም የሙስጠፌን አይነት አለምአቀፍ ተሞክሮ ያለው በአገሩ ጉዳይ ፍንክች የማይል ቢሆን ወይም ምክትልና ዋናው ሆነው ከአቢይ ጋር አብረው ቢያስተዳድሩ ኢትዮጵያ ወደ ጠፈር እንደመጠቀች ነው የምቆጥረው።
ውድ ኢትዮጵያውያን!
Oromara zehabesha 1 የህውሀትን ተንኮል ለመበጣጠስና ዖሮማራን እንደአባቶቻችንና አያቶቻችን ዘመን ለማጠንከርና ለማጎልበት የሚከተሉትን እንደ መፍትሄ በትህትና አቀርባለሁ።
፩) የዖሮምያ አስተዳዳሪዎች ከ አማራዎቹ በአደባባይ የጋራ መርሀ ግብር ፍጠሩ። የዛሬ አመት በነገር የተጎሻሸማችሁት ታዬ ደንደአና የአማራው አቻህ በአማራ ቲቪ ይቅር ለግዜር ተባባሉ። እንደ ቀላል አትዩት። ሽመልስ አብዲሣም የአምናውን ስህተት ይቅርታ ብትጠይቅበት በሆነ አጋጣሚ ተጠቅመህ የሻከረውን ልብ ያሳሳል፣ ሞራልም ያሰንቃል። እንዲህ በማድረግህ ህዝባችንን ታኮራ እንደሆነ እንጅ እንደ ውርደት የሚያዩት ፅንፈኞቹና ህውሀት ብቻ ናቸው። ቀላል ሊመስል ይችላል ግን የሁለቱን ህዝቦች አንድነት ያጠናክራል። የሰው ልጅ በተለያየ መንገድ ስህተት ይሰራል። በአገር የሚሰራ ስህተት ዘመናትን ሰለሚሻገር ለልጆቻንና ልጅ ልጆቻችን፣ ለእናት አገር ሲባል እራስን ዝቅ ማድረግ ቀናነት ብቻ ሳይሆን እውቀትም ነው። በፈጣሪም ዘንድ መልካምን ያጎናፅፋል።ትህትና ከዚያ ይጀምራልና።
፪) በየሚዲያው የምትፅፉና የምትናገሩ፣ ወይም የተነገሩትን ይሁን የተፃፉትን በሚዲያ የምትገመግሙ ወገኖች – በተለይም ምሁራን፣ የታሪክ ሰዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች! እባካችሁ መላልሳችሁ ቃኙት የምታደርጉትን። ኣንዱ የሌላውን ቁስል ይመልከት። የተዛቡብን እጅግ ብዙ ነገሮች ናቸው። እነዚህ ህውሀቶች እውነትም የመቶ አመታት ሆምዎርክ ነው ይዘውብን ነው ሳጥናዔል ወደ ህዝባችን ፈቶ የለቀቀብን። ቀላል ባላንጣዎች አይደሉም። በቀላሉም አይጠፉም። እንደ ዖሮማራው በቁጥር ያልደመቁ በልባቸው ግን የኢትዮጵያን አንፀባራቂ ክታብ በልባቸው ያሰሩትን ሌሎች ጎሳዎች መቀናጀት በአንድነት መቆም ምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ከልብ ከሆነ ለአገራችን ያለን ምኞት ማ ምን እንደሆነ መለየት አያዳግትም። መልስ ስንሰጥ ጥንቃቄ ይኑረን። በቅርብ በፅሁፍዋ የማደንቃት በቲዎሪም በምግባርም የዖሮማራ መልካም ውጤት የሆነችው መስከረም አበራ እንኳ የአቢይን ጠለቅ ያለ ችግር የተረዳች አልመስልህ አለኝ። የአቢይ መንግስት የዘር ማጥፋት ነው ለማለት እኮ ብዙ የተምታቱ እውነታዎች ስላሉም ነው። የዘር እንዳይመስል ጁዋርና ቡችሎቹ፣ ሸኔና አለቆቹ ብዙ ማይልስ ሄደው ሀይማኖታዊም ጠረን እንዲኖረው አድርገውታል እኮ። how about ሁለቱንስ ቢሆን? ደግሞስ የዳንኤል በቀለ ሰዎች አነፍንፈው ይድረሱበት እንጅ አቢይ እንዲህ በክፉ አራዊት ተከቦና ጭንቅ ውስጥ ሆኖ የንዲህ አይነቱን ዲዳክሺን ለማድረግ “የደላው” አልመስልህ ብሎኛል። ለማንኛውም አንድነታችኑ ላይ መድከሙ ይሻለናል እንደ ህዝብ።
፫) የዖሮማራው ዝምታ ያክትም!
ይህ ብዙሀንን ኢትዮጵያውያንን ይመለከታል። በተለይም ሀቀኞቹ ፣ እውነተኞቹ የቱለማ ልጆች ፣ እኔ እንኳ የማውቃችሁ እንዴት አስቻላችሁ? ከዚህ በላይ ምን ይምጣ? ምንድነው ዝምታው? እንዴት ስንት ሊቃውንት እያላችሁ ኢትዮጵያ በተወናበዱ የፌስቡክ ህፃናት ህልውናዋ ይፈተን? የናንተ ዝምታም አይደል የጁዋርን አይነት ፣ የፀጋዬ አራርሣን አይነት፣ በትምህርት ሳይሆን በጫት የመረቀነው የህዝቅኤል ገቢሣ አይነት፣ ከጥላው የተጣላው የ”ምሁር ቦዘኔው” ብርሀነመስቀል ሰኚው አይነት መፈንጫ የሆነችው አገራችን? የዖሮሞ እናት የወለደቺው ነው የዖሮሞን ቡቃያ ለ 27 አመታት ሲበላና ሲያጠፋ ከኖረ ተምች የሚወዳጅ ?? ምንድነው ዝምታው? የ OSA ስ ዝምታ በዚህ ጉዳይ ለምን ይሆን? ማን ይሙት እንደዛ አምሮብን አምና በሸገር እንደዛ አይነት ምሁራዊ ስብሰባ በኢትዮጵያ ምድር በዘመነ ህውሀት አድርገን ነበር? ከአቢይ በላይ ዖሮሞነትን ብሎም ኢትዮጵያዊነትን ማማ ላይ ዬትኛው የዖሮሞ ታጋይ ነው ያበቃው? የአሥመራን  ቢሬታ  ሲቆጥር የከረመ ሁሉ ዛሬ ድልአድራጊ ሆነና  ሌላው ቢቀር የገዛ ዖሮሞ ወገኑን ከህውሀት ተጣምሮ ሸኔ በጥይት ሲለቅም መተንፈስ ነበረባችሁ። በአገር ውስጥም ያላችሁ የዖሮሞ ልጆች ይህን ታሪክ የማይረሳውን ቦታችሁን መረከቢያው አሁን ነው። እንደ ታዬ ደንደአ አይነት ሳተናና ለኢትዮጵያ ከሌላው ህዝብ ጋር አብሮነት የምትሰለፉ ብዙ ናችሁ። ሆኖም ትግሉን ሰው እንዲያደርግላችሁ እንጅ እራሳችሁ እጃችሁ እንዲጨቀይ  አትፈልጉም። ይህ ማብቃት አለበት። ድሮስ ህውሀትን “ፍራቻ ” ነበር ለቤተሰብና ለግል ህይወት ሲባል። በአቢይ መንግስት ስር ተሁኖ አሁንም ሊፈሩ ነው? መሞት አይሻልም ከዚህ? አለበለዚያ እንደ ቁጥራችን ልክ ዝም ባልተባለ እላለሁ።
፬) ዖሮሞው ላማራ፣ ጎረቤት ለጎረቤት ይጠባበቅ!
አንዱ ሌላውን ይጠብቅ ። የተሸረበው ብዙ ነው፣ ገናም ይሞከራል። በየሰፈሩ የምታውቁትን ፖሊስ በደንብ መለየት። ለህዝብ ያለው አቋምን ጎረቤት ያውቀዋል። ያ ከሆነ በየሰፈሩ እየተደራጁ ከፀጥታው መቀናጀት። የ እስክንድር አይነቱ የቪጄላንቴ ጎበዝ አለቆች ሳይሆን ከመንግስት ፖሊሶች ጋር የተቀናጅ የህዝብ ደህንነት ጥበቃ ማለቴም ነው። የእስክንድርም ደጋፊዎች ህግ ማስከበሩን ከመንግስት አከላት በመቀናጀት ቢያደርጉት እንዴት ባማረ። ይህ መንግስት አላሰራንም ወይም የአዲሳቤዎቹን ስሜት አልተጋራም ከንቲባው አይነት ክስ እውነት ከንቲባው ሁሉን አይነት ስሞታ  አውቆት እንዳልሆነ ምሳሌ ላቅርብ። በቅርብ አንድ በእስርና እንግልት ፍዳውን ያየ የወለጋ የዖሮሞ ልጅ ኢንጅነር እንዳለ አበበ እንዳስደመጠን ከሆነ  (አሳዛኝ ታሪኩን ቪዲዮውን ፈልጋችሁ እዩት)ያውም ዖሮሞ ሆኖ  መንግስት የፈቀደለትን ኮንዶ እንኳ የሚሰጠው አጥቶ ስንት በእስር ቤት በሽታ የተለከፈውና የገዛ ልጁ በህውሀት ሰዎች የተደፈረችበት  ሰው  ውጭ አዳር ሆኖበታል። ይህ የሚያሳየን የ ሸገሩ አስተዳደር ይሁን የአቢይ መንግስት አሁንም ከውስጣቸው በነ ህውሀትና አክራሪያን ሲምፓታይዘርስ መታጠራቸውንና ሁሉንም የህዝብ ብሶትና እንግልት ለማወቅና ለመዳኘት አለመቻላቸውን ነው። የ 27 አመታት ነቀርሳ እንዲህ በቀላሉ የሚሽር ነገር ባለመሆኑ አንዱ ለሌላው ተገን እየሆነና እየተረዳዳ ቢሆን ፅልመት ባልፈነጨብንም ነበር። ስንቱን በጋሬጣ ጋዜጣው ህውሀትን የወጋው እስክንድር እንኳ ይህን ማገናዘብና እንዴት መረዳት እንዳልቻለና ቀረብ ብሎ ለታከለም ይሁን ለአቢይ ትህትናና አለኝታኘነትን እንደማሳየት የትእቢት “ታያላችሁ ከመስከረም ሰላሳ በሁዋላ” አይነት  የነ ልደቱን አይነት ዶርሲሣ ከሱ አልጠበኩም ነበር።
፭) የዖሮማራን ጉዳይ ካነሳን ማንም ከኢትዮጵያ በላይ አይደለምም ተብሏል እኔም ከልቤ አምንበታለሁ። የፈለገው ግለሰብ ወይም ቡድን ሊሆን ይችላል። ችግር ካለ በጊዜ በአደባባይ ነገርዬውን አለማውጣት መዘዙ ብዙ ነው። የዖነግ ጥጋብ ኦቦ ዳውድ በቪኦኤ  መንግስትን ያስፈራሩ ጊዜ ይጀምራል ፣ የጁዋር እብሪት እየሳቀ ሁለተኛውን  መንግስት በአደባባይ በንቀት የነገረን ጊዜና በአልጀዚራ ወገኖች በሱ ዳፋ አልቀውም እንደ ዌስተርን ሊበራል የፎለለብን ጊዜ ይጀምራል ። ከዛ በሁዋላ የሆነው  እልቂት ሆነ ውድመት በሙሉ የዛ ጥጋብ የስራ ውጤቶች ናቸው። እንዲህ አይነቱ ትእግስት  የዖሮማራን አለመናበብን ስለሚያስከትል በአስቸኳይ እንደተከሰተ መጥራት አለበት። መንግስት ከባለፈው የትእግስት የስራ ውጤት ብዙ ተምሯል ብዬ እጠብቃለሁና አሁኑኑ በትኩሱ እነዚህ ከሀዲዎች የምርጫ ተብዬ ድራማቸውን ሳይከውኑብን በፊት   በደንብ ተዘጋጁላቸው።  ለአገር ሲባል ምንም በምስጢር መያዝ የለበትም። የህውሀትን በአማራው ድንበሮች ማንዣበብ የሁለቱም ክልሎችን ትብብርና ጥምረትን ስለሚፈልግ በጥንቃቄና ንቃት መጠበቅ ግድ ነውና።
በመጨረሻም!
የዖሮማራ ልጆች በመንግስት እዝ ስር ያላችሁ። ይህ ለናንተ ነው። ግልፁን ነው የምነግራችሁ። እስካሁን የጠፋው ጥፋት እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይነት በቅርብ ጠ/ሚሩን የምታውቁ ሰዎች አንደበታችሁን ምን ዘጋው? በዚህ ሰውዬ ላይ እንዲህ አይነት የኢትዮጵያና ኡትዮጵያዊነት ልቡ የነደደን ሰው አምባቸውን የመሰለ ገራገር ኢትዮጵያዊ የገደለው አቢይ ነው ተብሎ የገለማ አፋቸውን እስከሚያሟሹበት ድረስ እንዴት አስቻላችሁ? አንዳንዶች ውስጡን ሳናውቅ እንደው በሚሰራው ስራ በመገመት ከርቀት ስንከላከል፣ የዳንኤል ክብረትና አቶ ንጉሱ አይነቶች በአደባባይ ብትሟገቱለት ኖሮ ብዙ ፈተናዎችን ባላሳለፍን ነበር ብዬ አስባለሁ። ይህን የምለው የትላንትናውን የ ዲ ዳንኤልን ለዶር አቢይ ምስክርነት ሰምቼ ነው።  አሁንም አልመሸም። አንዱ ለሌላው መልካም ወንድሙ ምስክርነት ቢሰጥ ኢትዮጵያን ያጠነክራታል። የዖሮሞና አማራው የጠለቀ ማንነትም መገለጫ ነው። አገራችንን መልሶም በእግሯ አስቁሞ ወደፊት የሚያንደረድራት የዚሁ ጥምረት ልጆቻችን ከሌሎች የማቀናጀትና ለኢትዮጵያ ዘብ መቆምን ይሆናል። ወጣቱ ትውልድ ባሁኑ ጊዜ  ተምታቶበታል ወገኖች። የዋቆ ጉቱን ገድል ወጣቱ የሚያውቀው ልክ እንደ ጄኔራል ጃገማ ለኢትዮጵያ አርበኝነት ለዖሮሞ ክብር የተሰዋ አይነት አርበኛ አድርገው ነው። ይህን ስሙን በዘፈን ያጦዙለትን “ጀግና” የ ዶር መኮንን ብሩ አይነት የቱለማ አንበሣ ወደ መድረክ እየቀረበ ታሪኩን በትክክል የወንበዴ አለቃ እንደሆነ  ቢያማምረን (በሳተናው እንደወጣው) ወጣቱ  የቅድመ አያቶቹን ታሪካዊ ቦታ ለመረከብ ገደል አይሆንበትም። ላሁኑ  አንድ ትውልድን ብናጣም – በሚያሳዝን መንገድ – ሁለተኛውን አይናችን እያየ በነፈዝነታችን ብቻ እንዳናጣው በተለይ የዖሮማራ ኢትዮጵያ ልጆች ታሪካዊ ስርፋችሁን ውሰዱ። በነገራችን ላይ ያሁኖቹ  የኦሮማራ መሪዎች 70% የሀገሪትዋን ወጣት ህዝብ ይመስላሉ:: ልክ እንደ ህውሀትና ሸኔ መሪዎች ያረጁና ያፈጁ፣  ዘመኑ ያለፋቸው ፖለቲካው የከሸፈባቸውና  ሁለነገሩ የተምታታባቸው አይደሉም። እጅግ ሁዋላቀርነታቸው የነፃ አውጪ ምናምንቴ ድርጅቶቻቸውን እንኳ በትኩስ ሀይል ሳይፐውዙ ኢትዮጵያን የምታክል ብርቅዬ አገር ለማስተዳደር ህይወትን ለማጥፋትና ንብረት ለማውደም ሲወራጩ ነው። የዶር አቢይ አይነት ብልህ መሪ ጦርነት ከህዝቤ አልገጥምም ብትፈልግ ምርጫ አድርግ ፣ ከደብረፅዮንና ጓደኞቹ በቀር እንደ ባይቶኔ አይነት አዲስ ፓርቲ ወደ አስተዳደር ብቅ ካለ ብቻ አለርት አርጉኝ የሚል ጀግና መሪ እኮ ነው ያለን?እንዲህ ነው የወጣትነት ዘመኑን ጠብቆ የሚሄድ አስተዳደር። ነፃአውጪ የተባለ ድርጅት በሙሉ ሙዚየም መግባት ነው ያለበት። ይህው ነው!!!
ልኡል እግዚአብሄር ኢትዮጵያን አንድነቷን ጠብቆ ያቆያት!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኛ ሐዋርያት …በቀራንዮ መንገድ ላይ! - ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ - አሜሪካ)

5 Comments

 1. Well it has been sometime you guys remove the mara from oromara and replaced it with kegna. Now it is about kegna, orokegna. Finefine kegna, arat kello kegna, wollo kegna, metekel kegna, Ethiopia kegna, every open yards kegna, condominium kegna, broze horse kegna, that house kegna, these houses kegna, this girl kegna, that man kegna, this church kegna, this street kegna, this town kegna, this city kegna, the schools kegna, the army kegna, police kegna, all public office jobs kegna, your store kegna, your wife kegna, belay zeleke kegna, harer kegna, dire dawa kegna, gedeo kegna…..
  Yea this unfortunate country and unfortunate people are in the hand of individuals who can not see beyond their nose and can not think beyond their village tribesmen.
  Lord have mercy.

 2. አባዊርቱ

  እንደዚህ ያለ አርቲክል ስታቀርብ በደንብ ለኔም ይስማማኛል፡፡ very constructive and balanced article indeed. You see I am fair and I try to criticize you on your previous article, because you wrote a biased article praising the wrong people as Ethiopian savers while so many of us know exactly how evil those people are. That is why I was trying to tell you that the previous article you wrote was out of the ordinary. But this article is completely different form the previous one in it’s context and usefulness. When it comes to Ethiopia, we all have our solution even though sometimes we go out of the way to appease some one. Please understand that nothing is personal and I truly welcome this kind of article. As I said before I read a lot of good articles from different writers. Again this one is very good indeed. Thank you.
  Good day

 3. ይህ ጸሐፊ ዶክተር አብይን እንደ መልአክ አምላኪ ፤ ዶክተር አብይን በምክንያት የሚተቹትን ሁሉ እንደ ሰይጣን የሚያይ ፤ እርሱ ብዕሩን በየቀኑ ከወረቀት አገናኝቶ አብይን በጭፍን ካልካበው ከምድር የሚጠፉ የሚመስለው ግለሰብ ነው ። አቶ ዮሴፍ በጣም የገረመኝ ዛሬ እንደት እንደቀደሙት አለውቅም ይህ ጸሐፊ ጽሁፉን እንደለቀቀ ለመደገፍ ሰው የማይቀድመው ዜጋ( እንደ ዜጋ ) ብሎ የሚጽፍ አለ ምናልባትም ራሱ በሁለት ስም ተጠቅሞም ሊሆን ይችላል ። እንዳሉትም ኦሮማራ ብሎ ነገር የለም ሁሉም ኬኛ ነው ።

  • ትክክልነህ ተጋዳላይ፣ የተለጠፈውን ሁሉ ኣላነብም ፣ እመርጣለ ሁ ፣ የመንጋ ኣስተሳሰብ የለኝም።
   የኦሮማራ ሚና ወያኔን መቀሌ እንዲሸጎጥ ማድረጉ ወደ ፊት ታሪክ ጸሃፊዎች የሚተነትኑት ይሆናል።ይህ ጥምረት ሀገረ ኢትዩጵያን ምስረታ ለማይሹ መጥፊያቸው መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁታል።
   ይልቅስ የኦሮሞ ወይም የኣማራ ስም ኣጥልቀህ መርዝ ህን ከመርጨት ቢያንስ ስምህን መደበቅህ ወደ ህሊናህ ለመመለስ የመጀመሪያው baby step ነው።

 4. አባዊርቱ ለእርስዎ መልካም አስተያየቶች ትልቅ አክብሮት አለኝ። ይህቺን መጠነኛ ግን በኔ እምነት ወሳኝ ጉዳይ በሚቀጥለው አስተያትዎ እንደሚመለሱባት ተስፋ በማድረግ እንድሚከተለው አቀርባለሁ።
  ኦሮማራ ራሱ የሁለት ብሄሮች ስብስብ ነው ። በአንድ ወቅት የተወሰኑ ተቸካይ ወያኔዎችን ከያዙት ስልጣን ( ከአራት ኪሎ) ዞር ለማድረግ አገልግሎት ስጥቶ ይሆናል፣ ይህም ምንም ነውር የለውም፣ እንደ ፖለቲካ ስልት። አሁን ግን ትግሉ የሚጠይቀው የመላ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ የጠነከረ ህብረትና በአንድነት መቆም ነው። አለበለዚያ የሌሎች ማህበረስብ አባላት የሆኑ ጀግና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችንና የለውጡን ሃይሎች (ሙስጣፌ መሀመድ፣ ኦባንግ ሚኤቶ፣አብረሃ ደስታን፣) ፣በእነርሱም በኩል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቻቸውን ፣ የመሳስሉትንና ሌሎችን ብዙዎችን ሳናውቀው ማግለል እንዳይሆንብን ከፍ ያለ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። የትግል ጎራው አሁን ባለንበት ደረጃ፣ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ካላቀፈና ካላስተባበረ፣ ተመልስን እዚያው የተረኛነት የዘር አዙሪት ውስጥ ገብተን፣ ነገራችን ሁሉ መልሶ፣ :መልሶ’ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ እንዳይሆን’ እባካችሁ ጥንቃቄ ይደረግ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.