የተሳሳትሁ አልመሰለኝም ኦሮሞ የሚባል ቃል አልነበረም – ሰርፀ ደስታ

Oromo 2

እኔ ለአስተያየት ሰጭዎቼ ብዙም መልስ መስጠት አልፈልግም፡፡ ሆኖም ጉዳዩ በወሳኝነት የአለመረዳት ችግር ከሆነ ለእኔም ጥሩ እውቀት ሊሆነኝ ይችላል፡፡ አባዊርቱና ተሰማ የተባሌ አስተያየት ሰጭዎች ትላንት በጻፍኩት የኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያው ፍጥረት ኦሮሞ የሆነበትን ትንታኔ የታዘብንበት ላይ ባነሳሁት ኦሮሞ የሚባል ቃል የቅርብ ጊዜ እንጂ ሩቅ እድሜ የለውም ያልኩትን ተሳስተሀል ይሉኛል፡፡ አባዊሪቱ እንደውም የሆነ ሕጻን ነገር አድርጎኝ ቆጭ ብሏል የኃይለሥላሴን ዘመን አለማወቄን፡፡ አባዊርቱ ያላስተዋሉት የኃይለሥላሴ ዘመን 50 ዓመት እየተጠጋው መሆኑን ነው፡፡ ሌላው እኔ የታሪክ ሰው ነኝ ብዬ አላውቅም፡፡ አይደለሁማ፡፡ ሆኖም ግን ታሪክ እናውቃለን የሚሉት እንደፈለጋቸው የሚነግሩኝን ከመቀበል የታቀብኩ ነኝ፡፡ አነባለሁ ነገሮችን በደንብ እመረምራለሁ፡፡

ኦሮሞ የሚለው ቃል በእርግጥም መጀመሪያ በጽሁፍ የወጣው በሁለት ፈረንሳዊ ወንደማማቾች ወለጋን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ይመሰለኛል፡፡ አዎ እኔ የታሪክ ተመራማሪ ስላልሆንኩ ይመስለኛል ብዬ ለአንባቢ ሁኔታዎችን በመጠቆም እንዲያጣራ መጋበዜ ነው፡፡ አውቃለሁ ብል እስታለሁምና፡፡ አማራው አባቴ ነገሩን ያለው ተሰማም ሆነ ራሱ የኖረበት አባዊርቱ ግን እርግጠኞች ናቸው፡፡ ተሰማ አፋን ኦሮሞ የሚባል ነገር በቀጥታ የኦነጋውያን ሴራ እንደሆነ እንኳን አያውቅም፡፡ አፋን ኦሮሞ ከመባሉ በፊት ኦሮሚፋ (ኦሮምኛ) ነበር፡፡ አፋን ኦሮሞ ማለት ኦሮሚፋ ሳይሆን የኦሮሞ ቋንቋ ማለት ነው፡፡ ይሄን ደግሞ ሆን ብለው ኦነጋውያን ናቸው የሰየሙት ምክነያታቸውም የኦሮምኛ ቋንቋ በሌሎች መነገሩንም ስለማይደፈቅዱ፡፡ ቋንቋው በእነሱ መስፈርት ለኦሮሞ ብቻ የተሰጠ ነው፡፡ ለዛ ነው ኦሮሚፋ ከማለት ይልቅ አፋን ኦሮሞ (የኦሮሞ ቋንቋ) ያሉት፡፡ ኦሮሚፋ ማለት ግን ኦሮሚኛ (ሁሉም ሊያወራው የሚችል) ማለት እንጂ የኦሮሞ ብቻ ተብሎ የሚወሰን አደለም፡፡ ይሄን ካላወቅህ የኦነጋውያንን ሴራ መርምር፡፡ በእርግጥም ቀደም ባሉት ዜናዎች ሳይቀር ኦሮሚፋ ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ ኦነጋውያን ናቸው ይሄን የቀየሩት፡፡ እንግዲህ አንድህ ባለ ሁኔታ ደብዛቸው የጣፋ እውነታዎችንማ እንዴት አድርገን ለሰዎች ማስረዳት እንችላለን? ስለ ኦሮሞ አባ ጅፋር ያሉትን አንብብ ወይም ጠይቅ፡፡ ይሄን እውነት ለታሪክ ተመራማሪዎች እተወዋለሁ፡፡ እንዴት ግን በዚህ አጭር ጊዜ ትውልድ ሙሉ በሙሉ አስተሳሰቡ እንደሚቀየርና በአልሆነ ትርክት እንደሚጠፋ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ እውነታው ኦሮሞ (ሥያሜው) ከወለጋ ወደሌሎች የተዛመተው በአንድ ሰው እድሜ ነው፡፡ ተሰማ አባትህን መልሰህ ጠይቃቸው ይነግሩሀል፡፡

ለማንኛውም የኬንያ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ስለኦሮሞ የሰጡትን ትንተና ከዚህ በታች አድምጡት፡፡ እነዚህ የኦሮምኛ ተናጋሪዎች ራሳቸውን ኦሮሞ ብለው አይጠሩም፡፡ ግን ለሥያሜው መነሻ ትርክት አላቸው፡፡ እንግዲህ እውነት ይሁን ወይም እነሱም የመሰላቸውን ይሁን ታሪክ ተመራማሪዎች ይሞክሩት፡፡ በእርግጥም የቃሉ መነሻ እኔ ትላንት እንደጠቀስኩት ኦርማ (ባዕድ/ሌላ/እንግዳ) ማለት ነው ይሉናል የኬንያዎቹ ወርደዴዎች (ኦሮምኛ ተናጋሪዎቹ)፡፡ እስኪ ወደ ቦረናም ሂዱና ሽማግሌዎችን ጠይቁ ኦሮም የሚለው ቃል ከመቼ ጀምሮ ቦረና እንደገባ ይነግሯችሁ ይሆናል፡፡ ኬንያዎቹ ግን እንዲህ ሞክረውታል ስርወ ቃሉንና አመጣጡን!

https://www.youtube.com/watch?v=Ga37OmwPBpU

ሌላው ሁለታችሁም ለኦሮሞ ሕዝብ ያለህ ንቀት ስትሉ ያው የተለመደ መርዛችሁን ልትረጩ ሞክራችኋል፡፡ እኔ እንደናንተ ለማሰብ የሚያስችለኝ ደረጃ ላይ አደለሁም፡፡ ያንን ደረጃ በርቀት አልፌዋለሁ፡፡ ዛሬ ኦሮሞ እየተባለ የሚጠራውን ሕዝብ ማን እንደሆነ አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ የሸዋ ኦሮሞ የሸዋ ነገስታት ዘር እንጂ ከመዳ ወላቡ የመጣ ነው ብለህ ካሰብክ እሱ ጋር ነው ስህተቱ፡፡ ይሄን የማረጋግጥልህ ራሴው ሰርቼ ባየሁት የዲኤንኤ መረጃ ነው፡፡ በቅርቡ ጠብቀኝ፡፡ አማራ ያልከው ሸዋ ኦሮሞ ካልከው ሰው ይቅርና መናገሻ ሱባ ላይ ያለው ጽድ ደብረሲና ካላ ጽድ እንድ ናቸው፡፡ ወፍዘራሽ ሆነው ሳይሆን በሌቤቶቹ የሸዋ ነገስታት ስለነበሩ፡፡ ታሪክ አንብብ ተጽፏል እኮ ግን ማን ያንብበው? ወዳጄ ዘሬ ዛሬ እንደተሸነሸነው ሳይሆን ዘሬ ሁሉም ነው፡፡ ሁሉምነው ስል በዘልማድ ተዋልደናል ተዛምደናል እንደሚሉት ሳይሆን መሠረቴም ዛሬ ባንዋለድም በቋንቋ እንጂ በደም እንደማይለያይ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ፡፡ ይሄ የራሴ የምርምር ውጤት ነውና፡፡ ስለዚህ ተሴና አባዊርቱ ይችን የጠነዛች ንግግራችሁን እዛው ሰፈራችሁ፡፡ እኔ ሲጀምር ማንም በማንነቱ አልንቅም፡፡ በአስተሳሰቡ ካልሆነ፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ያላችሁት አብዛኛው ሕዝብ ደግሞ ከገባሕ እኔም ነኝ፡፡ ከእንደናንት ያለ የአስተሳሰብ ባርነት እንዲወጣ ነው ሕዝቤን እውነቱን እንዲያውቀው የምፈልገው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለ50ዓመት ከእነ ዋለልኝ ከተባሉ ነቀርሳዎች ጀምሮ የተጫነበት የአስተሳሰብ ባርነት ነጻ ይወጣል፡፡

ሸዋ ወደነበረበት ሁሉን ያቀፈ ማዕከልነቱና የሕዝባችን ሁሉ መተሳሰሪያ ማሳያ ሆነ ኢትዮጵያን ዳግም እንድትመሠርት፡፡ ክልል የሚባል እንዲፈርስ ሁሉም መሥራት አለበት፡፡ ያኔ የማንም ወሮበላ እየተነሳ ሕዝብን አያመስም፡፡ 50 የባከነ ዓመት፡፡ ያ የ60ዎቹ ትውልድ ያመጣብን ልክፍት፡፡ የት በደረስን ነበር፡፡ አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

11 Comments

 1. አቶ ሰርፀ እንዴት ነው ነገሩ? ከ 30-50 አመታት በፊት ዖሮሞ የሚባል የለም ባለው አንደበትህ አሁን ደሞ ማጠፊያው ሲቸግር አስራስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገብተህ አረፍከው? እኔ የምልህ ያለው ከ ሀምሳ አመታት በፊት በትክክል እስከ መቶ ምናምን አመት ኖሬበትም ፣ ሲወርድ ሲዋረድም በቃል ትምህርትም የማውቀው ዖሮሞ ዖሮሞ ሆኖ እንጅ በሌላ አይደለም። የdna ሣይንሱን አንተ ልትቀኝበት ትችላለህ እናም ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ለመሆናችን ፕሮ ፍቅሬ ቶለሣም ነግሮናል። ስለ ኢስት አፍሪካም ነገዶች ለኔ ምኔም አይደሉም፣ የምናወራው ባገራችን ስለ በኛ እድሜ ዖሮሞ የለም ብለህ በስህተት ስላልከው ብቻ ነው። እኔ ስለ ሁላችን ውህድነት ከዚያ ችግር የለብኝም። አምንበታለሁም። ብንታደለው ኖሮማ ሁላችንስ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች አይደለን እንዴ? ዋናው ቁምነገር በድፍረት አሁንም እደግመዋለሁ ከ 30-50 አመታት በፊት ዖሮሞ የለም ብለህ ያልከው በጣም ስህተት ከመሆኑም አልፎ የወረደ አስተያይ ነው። ዖሮሞ የሚባል ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአነጋገር ዘይቤው ፣ ከጠላው እስከ ዜማው፣ አዝእርትና ተረትና ምሳሌው ድረስ በርግጠኝነት ነው የምነግርህ አለ፣ ነበረም። በሀይለስላሴ ዘመን ልትፈጠር ትችላለህ ህዝበ ዖሮሞን ግን በወሬና ትምህርት ካልሆነ አታውቀውም ዖሮሞ ሆኖ ተፈጥሮ እንደጎለመሰ ። እስቲ የዖሮሞነት ስያሜ ለመኖሩ መገለጫዎችን ላጣቅስልህ በጥቂቱ:

  የዖሮሞ አባቶች፣ ጫወታ አዋቂዎቹ ተረብ ሲጀምሩ እንዲህ ይላሉ ” ያ ጃራና ዖሮሞን ቴኛ አካና ጄ’ዴ—-” ትርጉም ” ወዳጆቼ፣ የኛ ዖሮሞ ልጆች እንዲህ ብለው—”

  ፋርሦ ዖሮሞ = የዖሮሞ ለየት ያለ ጠላ
  ቆቾ ዖሮሞ = የዖሮሞ ለየት ያለ ድንች

  እንኳንስ ህዝቡ እራሱን ቀርቶ ለአነጋገር ስልቱና የሚበላውንና የሚጠጣውን ሳይቀር ከዖሮሞ አጣቅሶ የኖረና እየኖረ ያለ ህዝብ ነው። ስህተትህን ማረም ከቶ ስድብ ሊሆን አይችልም። ስድቡስ አንድን ታላቅ ህዝብ በኔ እድሜ የማውቀውንና የኖርኩበትን ዖሮሞ የለም ስትል እውነትም የለንም አስብሎኛል። የለንም ያስባለኝ ግን የህውሀት ዲጂታል መናፍስቶችን እንደ ዖሮሞ ስለማልቆጥራቸው በዝምታ ይህን ጉድ እያነበቡ ስህተት መሆኑን ሁሉ እያወቁ እንደ በድን ዝም የሚሉትን ብዙሀን ትውልደ ዖሮሞን ነው። ለዚህም ነው አቶ ሰርፀ ለንዲህ አይነት ድፍረት የበቃኸው። አዲስ አጀንዳ አስከፍቶ ከድጡ ወደማጡ እስኪያስገባ ድረስ። በኔ ቤት ብቻ ወደ መቶ አመት የምናውቀውን (በቃል የተላለፈው ሳይቆጠር) የዖሮሞን ስመ መጠርያ ወደ 30 ና 50 አውርደህ የማይገናኘውን DNA የምርምር ውጤትህን ብትለጥፍልኝ የማውቀውን እንዳልነበረ ሊያሳምነኝ ከቶ አይችልም። የምናወራው ስለ DNA አይደለም ፕሊስ። እኔ አንተን ብሆን እኔን ሆነ ትውልደ ዖሮሞን ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ግድ የለህም ተሳስተሀል። በነገራችን ላይ ሌላው ስህተትህን ልንገርህ ፣ ዖነግ ሳይፀነስ አለም ላይ ሳይከሰት በፊት ዖሮሞ መግቢያያ ቋንቋውን “አፋን ዖሮሞ” እንጅ ከ 40 አመታት በፊት “ዖሮሚፋ” የሚባል ዘይቤ አልሰማሁም። አፋን ዖሮሞ ከአብዮቱ (66ቱ) በሁዋላ እየዳበረ መጣና ወደ ዖሮሚፋ ተቀየረ። ደርግ እንደ ጀመረ በፊት በግእዝ ፊደል የሚታተም “በሪሣ” የሚባል ጋዜጣ ነበር። የአፋን ዖሮሞም ሬዲዮ ፕሮግራም ሲጀምር እንዲህ ይል ነበር

  ” ኩን ራዲዮኒ ኢትዮጵያ ኮጺ አፋን ዖሮሞቲ” ኮጲ ዖሮሚፋቲ አልነበረም።
  አዝናለሁ ምድረ እራሱን ፣ ታሪኩን የማያውቅ ነሆለል አክራሪ የምንደኞች አልቅላቂ በዛና ማንስ ስለ ዖሮሞ ማንነትና ምንነት ይናገር። የጠቃቀስካቸው የጫቱ ልሂቅ ይሁን የአዋቂ ገልቱዎች ዖሮሞ የለም ቢሉኝ እራሱ አይገርመኝም። እንኳንስ ሊያውቁት። እራሳቸውን የካዱ በመሆናቸውም አይደል ኢትዮጵያን ክደው መነጋገርያ አጀንዳ ጠፍቶ እርሶም ከነጭርሱ ከ 30-50 አመታት በፊት ዖሮሞ የለም እስከማለት ያደረስዎ? ግድየሎትም አቶ ቡልቻ ጋ ደውለው ይጠይቋቸው እስቲ ። ወይም ብጄ ካሳዬ ጨመዳን። አበቃሁ በዚህ ጉዳይ! ለጉድ አስቀምጦ ይህንን ሰማን። በዚህ አጋጣሚ አቶ ተሰማ በትክክል ሰምተዋል። ብዙ አይጠፉም በየቤቱ።

  • Obbo Abbaweretu; the Amhara monk Abba Bahrey used the words ‘Galla’ and ‘Weromo’ interchangeably in his manuscript ostensibly written in 1593! Your knowledge-free Habeshi friends have no mental faculty to read outside what their debteras wrote and write, and do not think beyond praising king Minilik. You think you can educate those that vehemntly resist to know truth?? Itti jabaadhu!

   • Aba Bahrey was a debtera you tree worshiping savage. Now you want to educate the debteras what? your migration history or Ethiopian history? We are in the end of days for sure.

 2. የሰርፀ ችግር ጥላቻና ድንቊርና ነው። ቀደም ሲል የጻፈውን ፍሬ ቢስ ሐተታ ሳይወጣ፣ በትልቊ “ኦሮሞ” ብሎ ደግሞታል። እስቲ ምን ትሆኑ ነው ጒዳዩ! ለነገሩ አንተ ታመምክ እንጂ ምንም አንሆንም፤ አገራችንም ይህን አንተና መሰሎችህ የምትፈጽሙባትን አሳር ታልፈዋለች!!

  ውድ ሰርፀ፣ አንድ ነገር ልምከርህ፣ ምክር ከገባህ። በአደባባይ ራስህን ከምታዋርድና አንባቢውን ከምታወናብድ አስቀድመህ መረጃዎችህን አጣራ። ለምሳሌ፣ ባለፈው ጽሑፍህ ላይ “ሰሞኑን መሣይ አንድ የሜጫ ቱለማ ሰው ስለ ኦነግ ሸኔ ሲጠይቅ ሰማሁ፡፡ ተጠያቂው በኃይለሥላሴ ጊዜ የገበሬ ልጅ ከ4ኛ ክፍል በላይ አይማርም ነበር ሲል ሰማሁ፡፡ እንግዲህ ነገ ጠዋት አንዱ ይሄን የሰማ ዋይመ ተናጋሪው ራሱ ታሪክ ጸሐፊ ሆኖ ብቅ ይልና ይሄንኑ ስህተት የዘራል፡፡” ስላልከው ፍንጭ ልስጥህና አጣርተህ በቅንነት ተመልሰህ አስታውቀን። ፍንጩ፦ “ሴክተር ሪቭዩ” ነው። አንተ ካላወቅህ ሌሎች አያውቁም ማለት አይደለም። ጓደኛህን “ተመራማሪውን” አቻምየለህንም ምከረው። በተረፈ፣ አንተ ሆንክ (ጽንፈኛው) እስክንድር ወይም (ትምክህተኛው) ፕሮፌሰር ጌታቸው አማራን እንደማትወክሉ ሁሉ (የሥልጣን ጥመኛው) ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ወይም (ጯሂ/ረብሻ ፈጣሪው) ጀዋር ራሳቸውን እንጂ ኦሮሞን ሆነ አማራን ወይም አገራችንን አይወክሉም!!!

  ከሁሉ ከሁሉ የሚያሳዝነኝ፣ ይኸ ከንቱ ከፋፋይ ተግባር የህወሓትን እኲይ ዓላማ ማራዘሙ ነው።

 3. የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን እንደሚወናበድና እንደሚጨካከን የማየው እንዳንተ ያለ የኖርንበትና ያየነውን ካዱ የሚል አይናውጣዎች ስለበዙ ነው:: ጃዋር ለአዲስ አበቤው እናቴ ኦርቶዶክስ ሚስቴ ፕሮቴስታንት ናት እያለ ዘመናዊነቱን ይነግዳል:: በአፋን ኦሮሞ ደግሞ አማራን ነፍጠኛን ኦርቶዶክስን አፅዱ ብሎ የዘር ፍጅት ያውጃል:: ብዙ ወገኖችንንም አሳረደ::

  እኔ ኮሜንት ያደረኩት –

  “ዛሬ ማመን ሊያስቸግር ይችላል ከዛሬ 30 ዓመት በፊት አብዛኛው ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞ ተብሎ አይጠራም ነበር:: “

  ኦሮሞ ተብሎ አይጠራም ያልከውን ደረቅ ውሸት ነው የነገርኩህ :: እንኳን 30 አመት ከ40 አመታት በፊትም ኦሮሞና አፋን ኦሮሞ እንደነበረ ነው የመሰከርኩት አመንክ አላመንክ በብዙ ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ያለውን ሀቅ አይለውጥም::እኔ ጉራጌ ወይንም አማራ ሆነ ኦሮሞ መቼ ይህን መጠሪያ እንዳገኙ አላውቅም:: I care less በቀላሉ የገለፅኩት እንኳን 30 አመት ቀርቶ አማራው አባቴ እንኳን ከ80 አመታትም በፊት ኦሮሞና ቋንቋውን አፋንኦሮሞ በአማርኛ ፊደል ይፅፍ እንደነበረ ነው ይመስከርኩት:: በኦሮሚያ አዲስ ቃል የተፈጠረው “ፊንፊኔና ኦሮሚያ ” የሚለው የክልል አጠራር ነው::ኦሮሚፋም አዲስ ዘመናዊ አጠራር ነው ህዝብ አሁንም ገጠር አፋን ኦሮሞ ነው የሚለው :: ማንም የሸዋ ኦሮሞ አዲስ አበባን ከሸገር ውጪ ሌላ ስም ሲጠራ አልሰማሁም:: I honestly fail to understand what are you trying to prove? ጊዜዬን ማባከኔ ይቆጨኛል::ባለፈውም ጊዜ አብን እንደተቋቋሙ ስታብጠለጥላቸውና ጥላሸት ስትቀባ ተቃውሜሀለሁ::አማራ ያለ ኦሮሞ ያለ አማራ ኢትዮጵያ ሰላም አይኖራትም:: ህዝብን ለፖለቲካ ንግዳቸው የሚከፋፍሉ ህዝብ የሚያሳንሱን አይቼ ዝም አልልም:: ያንተ ፅሁፎች ለፅንፈኞቹ ማቀጣጠያ ቤንዚን ከመሆን ውጪ በኦሮሚያ ተበትኖ ለሚኖረው አማራ የህይወት ዋስትና አይሰጥም:: የግጭትና ጀብደኝነት ፖለቲካ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ሂሳብ ማወራረጃ ሊጠቅም ይችል ይሆናል::የማውቀውን ሀቅ ግን አልገባህም አትበለኝ::

  በቀጥተኛ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊነቱ የሚደነቀው ታዬ ደንደአ “የኦሮሞ ህዝብ የተለየ ጥያቄ እንዳለው እና ኦሮሞ ከኢትዮጵያ የተለየ እንደሆነ እንጂ፤ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ ያለ እና ተመሳሳይ ጥያቄና ችግር ነው ያለን፣ መፍትሄውም በጋራ ብንታገልና በጋራ ብንሰራ ነው የምናገኘው፤ የሚል አስተሳሰብ እንዲመጣ አይፈልግም ”

  ትርኪምርኪ አጀንዳዎችንና የፈጠራ ድርሰቶችን እየቀረፃችሁ ከወያኔ ባላነሰ ኦሮሞንና አማራን ለመለያየት የምትጠቀሙበትን ሸር አይቼም ዝም አልልም::

 4. ከዚህ በላይ የተቀመጡት አሥተያየቶች በጣም አሥተማሪ ናቸው። ለመማር ግን ቅንነትና ክፍት አእምሮ ያሥፈልጋል።
  ሠርፀ ላገሩ ብዙ እንደሚለፋ አውቃለሁ፤ ብዙ የሚሠራ ደሞ ሊሣሣት እንደሚችል ማመን ይገባዋል። “እኔ ፍጹም ነኝ፤ስህተት ሲያልፍ አይነካኝም…” የሚል ሰው ካለ ራሱን መፈተሽ አለበት።
  ጭቅጭቃችንና ንትርካችን ለአንድ ዓላማ ከሆነ በባሌም ሄድን በቦሌ ዞረን ዞረን መገናኘታችን አይቀርም፤ ዓላማችን ከተለያዬ ግን ‘አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም’ እንዲሉ ነውና መቼም አንገናኝም። ይልቁንም “እንካ ሥላንትያ በብጣሽ” ሥንባል “ምናለ በድሪቶ” እየተባባልን ነገራችን ሁሉ የተፈናጅራ እንደሆነ የምፅዓት ቀን ይደርሣል።
  ዙሪያ ጥምጥሙ ይብቃ(ኝ)። ከ30 ዓመት በፊት ማለት የደርግ መንግሥትና በእግረ መንገድም ኢትዮጵያ የወደቁበት የቅርብ ጊዜ ትውሥታችን ነው። በዚያን ጊዜ ይባል የነበረው ብሔሩ ኦሮሞ፣ ቋንቋው አፋን ኦሮሞ ነው። በተጓዳኝ ኦሮሚፋ ይባል እንደነበርም አስታውሣለሁ ፥ በየትኛውም ቢጠራ ደግሞ ችግር አይደለም። አፋን ኦሮሞ ማለት የኦሮሞ አፍ(ቋንቋ) ለማለት መሆኑ ግልጽ ነው። ያማርኛው “ኛ” በኦሮምኛ “ፋ” ናት። ሥለዚህ ኦሮሚፋ እንደሚባል ሁሉ አማሪፋ፣ ትግሪፋ፣ ሀደሪፋ… እያለ የሚቀጥል ይመሥለኛል – ይህም አያጨቃጭቅም። ግን ዘመኑ የንትርክ ሆነና በረባ ባ’ረባው እንድንወዛገብ መጥፎ ዕድል ገጠመን።
  በዚህ አጋጣሚ መርሣት የሌለብኝ ዋና ነገር አለ። እሱም ደርግ ወደ ሥልጣን እንደመጣ ከታዩ ለውጦች አንዱ በአንዳንድ የቦታና የብሔር/ብሔረሰብ ሥሞች ላይ የተደረገ ለውጥ ነው። ለምሣሌ በፊት ምናልባት ኦሮሞ ከሚለው መጠሪያ በተጓዳኝ – ወይም አላውቅም – “ጋላ” የሚል ሥያሜ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበርና በዐዋጅ (ይመሥለኛል) እንደቀረ ከሰው መሥማቴ ትዝ ይለኛል። የቀረበትም ምክንያት ጋላ ማለት ጨካኝ ማለት ሥለሆነ … ይባል ነበር። ይህን አጠራር የሚወዱትና አዲሱን ለመቀበል የሚቸገሩ የዘውጉ አባላት እንደነበሩም ሠምቻለሁ።
  በተረፈ አሩሲ ወደ አርሲ፤ በጌምድር ወደ ጎንደር፤ ወላሞ ወደ ወላይታ፤ ጉዴላ ወደ ከምባታ፤ ጋሙጎፋ ወደ ጋሞ ጎፋ … እንደተለወጡ ትዝ ይለኛል።
  ይህ ሁሉ ግን ለኔ ብዙም ችግር አይደለም። መለወጥ ያለበት የሰው ል አስተሣሰብ ነው። ትልቁ የጋራ ሀብታችን ሰውነት ነው። በቃላት ለውጥና በአነጋገር መሽሞንሞን የትም አልደረሥንም። ለምን ቢባል አለባብሰው ቢያርሱ ባረም መመለሥ አለና መሠረታዊ የአስተሣሰብና የአመለካከት ለውጥ ካላመጣን ነገረ ሥራችን ሁሉ የእምቧይ ካብ እንደሆነ ይቀራል።

 5. I read your opinion regarding Oromo ethnic. However some of the readers did not comprehend in the way of your thinking. As to my understanding Ethiopia before Woyane regime, none of Ethiopia boundaries called Oromo, but it named as Wellega, Illubabor, … No one is born as Oromo, Tigray, Amhara. .. .It is not inborn process but it is you choose to be any one of ethnic group.

 6. ይገርማል ስድብና ማሸማቀቅ እንደ ትግል ስልት ተወሰደ ማለት ነው? አቻምየለህ ይሄ ነገራችሁ ስለሚገባው ማስረጃው ባብዛኛው እናንተ ከምታመልኳቸው ጸሀፊዎች ነው የሚጠቅሰው ጭቅ ቅ እንዳታበዙ። ሰርጸ የጻፈው ትክክል ካልሆነ ሰነድና ማስረጃን ጠቅሶ ጽሁፉን ዋጋ ማሳጣት ነው ባላችሁበት አገር አጠና ቢኖር እድሜያችሁ ጣራ ስለነካ ነው እንጅ እናንተም ከሻሸመኔ ቄሮ አትሻሉም ነበር።
  ለማንኛውም ባለንበት ዘመን ማንም ከማንም አያንስም አይበልጥም ያለን አንድ አገር ስለሆነ እንደ እንቁላል እንጠብቃት። ያች አገር ፈርሳ ተጠቃሚ እሆናለሁ የሚል አካል ካለ የምዘና ችግር ያለበት ነው በዚህ አይነት ግንዛቤ መንጋውን ሀይ የሚለው ማነው?

  ሮዲንን ነጮች ሲገድሉት በጥቁሮች ድብደባ የደረሰበትን ነጭ በመኪናዋ ወስዳ ህይወቱን ያተረፈችው እኮ ጥቁር ነች። እንዲህ ያለ መንጋ አስተሳሰብ በሰብአዉነትና በዩኒቨርሳሉቲ አስተሳሰብ የሚሞረደው መች ነው? የሚገርመው ጠማማ ሀሳባችሁን መሞገት ኦሮሞ ህዝብ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ታደርጉታላችሁ። 300 ሰብአዊ ፍጡር ከጠላት ጠብቆ ባቆያት አገር ሲታረድ ትንፍሽ አትሉም አምላክ የስራችሁን ይስጣችሁ።

 7. In my opinion the writer and all the commentaries are right based on their own personal experience. Nobody was doing statistics 50 years ago going around to the remote areas of Ethiopia asking the so-called Oromos what they call themselves and their language. In my birth area, Amara means Christian and that was the case based on my coworker from Arsi. He told me he was surprised to learn that there are Muslim Amaras and Christian Oromos. That is why the Arsi, bali and harerghe Muslims are slaughtering every Christian regardless of the language they speak.

 8. To add to Tserse”s point. The name oromo was bestowed and imposed on others when he made it illegal not to call these people oromo. A crime pünishable by six months in jail literally making him the father of oromo. We all know whst the real name was before that. It seems the name oromo is derived from the amharic word aremenei which means ruthless and inhuman and perfectly describes oromo at the present. The facr that afan oromo does not have an alphabet is not Amaregans fault and proves Amaregna to be a superioe means of communication. Yes oromo is new and it was as old as melesses legal enforcement. The old history belongs to the galla and no oromo has a right to it. On edoucation during the regiem of Atse Hsiledelassie; parents in rural areas were given 25 birr to send their children to schools at no cost to them. Free education, closing , school supplies and free boarding was provided. The inrent was to make education accessible to all. The story that oromo was not allowed to go past grade four is a complete lie adapted from what the itslians did to the people in current dav eritrea when it was occupied by them. Oromo lies never end what s disgrace. Even lencho letta got free clothing even when he was at Haile Selassie University as well as free föod, lodging snd ofcourse free education. I think he might lie as usual.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.