ጃሮ = የጃዋር ቄሮ – አሁንገና ዓለማየሁ

Jawar ጃሮ = የጃዋር ቄሮ     አሁንገና ዓለማየሁየዛሬ ወር ነበር
ያየና ያላየ
ተመኝተው ወንበር
የዛሬ ወር ነበር
በየዋሆቹ ደም በጎርፍ እየዋኙ
የተቀጣጠሩት ማልደው ሊገናኙ።
ሥላሴ አጠገብ ከምኒልክ ግቢ
ቄሮ ፈረስ ሆኖ
ሃጫሉ ኮርቻ እነሱ ጋላቢ።
የዛሬ ወር ነበር
የዘር ፍጅት ድግስ
የእልቂት ፍትፍት ግብዣው ጮማውና ጠጁ
የተመተሩበት አባት፣ እናት፣ ልጁ
የአርሲ ዝዋይ እጣ የነሻሸመኔ
ሸገር አዲሳባ በራራ ፊንፊኔ።
የዛሬ ወር ነበር፣
የሲዖል ሠራዊት በአለቃ በአለቃው
ያዲሳባን ክርስትያን ሊያጭድና ሊወቃው
በውድቅቱ ሌሊት ጥሪ ያስተጋባ
መቶ ሻሸመኔን ልትሆን አዲሳባ
የዛሬ ወር ነበር።
የዛሬ ወር ነበር የጊዮርጊስ እለት
ቆንጨራ ገጀራ ሌላም ሁሉ ስለት
ለምኒልክ ጠላት ኪዳን የገቡለት
ያድዋውን ሽንፈቱን ሊበቃቀሉለት።
የዛሬ ወር ነበር
ፖሊስ እጅ አጣጥፎ
ዜጋ እሪ እያለ የሞተው ተከትፎ።
ዛሬ ልክ አንድ ወሩ
ግብጽን መጣንልሽ ብለው የፎከሩ
የሀገር ሠራዊት፣ ተከላካይ ጦሩ
ከሚሊዮን ጥይት ያልተኮሱት አንድም
ሙሉ ሻሸመኔ በጃሮ* ስትወድም።
የዛሬ ወር ነበር ማተብ እየታየ
የዘላለም ጥሪት በእቶን የተጋየ።
የዛሬ ወር ነበር
የሕዝብም ተወካይ
የግብጽም ተከፋይ
ተጠቃስወውበት በየዋህ ወገኔ
ጃዋር ኦነግ ሸኔ
ዲጂታል ወያኔ
በፋሽስት ጭካኔ
ያማራ ወላይታ ጋሞና ክስታኔ
ኦርቶዶክስ ኦሮሞም እያሉ መጠኔ
ሬሳ ያስጎተቱት አርሲ ሻሸመኔ።
*ጃሮ = የጃዋር ቄሮ

አሁንገና ዓለማየሁ
ሐምሌ 23፣ 2012

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.