የኖቤል ሰላም ሽልማት መልስ! – ኤልያስ መሰረት

119496 nobel11ሰሞኑን ኖርዌይ ለሚገኘው የኖቤል ሰላም ሽልማት ተቋም በርካታ ኢትዮጵያውያን ደብዳቤ እየላኩ ነበር። እነዚህ ደብዳቤዎች ጠ/ሚሩን የሚደግፉ እንዲሁም ተቃውመው ሽልማቱ እንዲሰረዝ የሚጠይቁ ነበር።
የተቋሙ የክርክር ሰሚ እና አጣሪ ቡድን መሪ (እንዲሁም ሽልማቱን በሚድያ ይፋ ያደረጉት) በሪት ሪስ-አንደርሰን ዛሬ በፃፉት ኢሜይል የተቃውሞ ድምፆች ሽልማቱ ይፋ በተደረገ ግዜም፣ አሁንም እንዳሉ ገልፀው ተቋሙ ግን በፍፁም የሰጠውን ሽልማት እንደማይሰርዝ አሳውቀዋል።
ሽልማቱን መሰረዝ ማለት ከኖቤል ፋውንዴሽን መመስረቻ ህግ ጋር የሚጋጭ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
በቅርብ ሳምንታት የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ስዩም መስፍን የኖቤል የሰላም ሽልማትን አስመልክተው “የኖርዌይ የሰላም ሽልማት… እያሰቡበት ነው። ልክ ነበርን ወይ፣ አይደለም ወይ (ብለው) እየታመሱበት ነው” ብለው ተናግረው የነበረ ቢሆንም የሽልማቱ ኮሚቴ ዳይሬክተር ኦላቭ ኖልስታድ በኢሜይል በሰጡኝ መልስ “ይህ መሰረት የሌለው ነገር ነው፣ እውነታ የሌለው አባባል ነው” ብለው ነበር።
116261925 876484039549307 5674656199956174925 n
116582476 876483996215978 3080557730841146120 o

1 Comment

  1. Shame on You Ethiopian Those who sent return mail!! If you have a brain to think the Prize represents not only the respected winner Prime Minister Dr.Abiy but also to the people of Ethiopia.
    What kind of weed generation we are observing?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.