ሸኔን ተዋወቁት – የጁዋርና ሸኔ

ሸኔን ተዋወቁት – የጁዋርና ሸኔ Unholy Alliance !
መቅድም!
ሁሉን ኦሮሞን ማብጠልጠል የምትወዱና የምታሳንሱ ትምህርት ይሆናችሁ ዘንድ በጥሞና ተከታተሉ። ዖሮሞ ትላንትም፣ ዛሬም የሚያውቀውና የሚሞትላት ስለ አንዲት ኢትዮጵያ ነው የምንለውም ለዋዛ አልነበረም። ይዋል ይደር እንጅ የተዘጉ አንደበቶች እየተከፈቱ ነው። የብዙሀን ዝምታ ሆነና እንጅ የታዬ ደንደአ አይነቱን ቆፍጣና ቤት ይቁጠረው። ያማ ባይሆን ኖሮ የጁዋር አይነቱ ቆርቆሮ ፉጨት ሚዲያውን ባላጥለቀለቀው ነበር። የጥቂቶች ጩህት የብዙሀን አስመስለውና አንገታችንን አስደፉን። ይሁን። ጁዋር በኦሮምኛና አማርኛ የተለያየ መልእክት የሚያስተላልፍ ፀረ ኢትዮጵያ አንጃ መሪ ነው። አሁን መሬት ያለውም ትግል በኢትዮጵያና በፀረ ኢትዮጵያ መሀል ያለ ፍጥጫ ነው። አራት ነጥብ እስከ ሰረዙ!!
ተራኪው የቱለማው ልጅ በንቲ ፉፋ ይባላል። ኢትዮጵያውያን በተለይም የዖሮሞን ልጅ በሙሉ በግፍ በጅምላ ለምትተቹና ለምትሳደቡ በሙሉ የዚህ የቆፍጣና ልጅ ገለፃ ከሸኔ እስከ ወያኔ ያለውን በግልጽ ያስቀምጣል። በዙህ ቃለመጠይቅ ውስጥ ስለ ገጠሩ ከ አራተኛ ክፍል ማቋረጥ ምክንያት የሆነው ከአብዮቱ በፉት sector review የሚሉት የትምህርት ማሻሻያ አይሉት መግደያ ስልት አብዮቱንም ካቀጣጠለው ቀንደኛው በመሆኑ በተማሪዎቹ ንቅናቄ በመላው አገር ታሪክ ሲያወሳው ይኖራል። ለማንኛውም አድምጡት። እጠራጠር የነበረውን የዳውድ ኢብሳን ማንነት ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የሚያሳዝነው በሰላም የገባውንም ፣ ነውጠኛውንም እኩል ማስገባታቸውን ነው እነ ዶር አቢይ። ልጆቻችንን ሲበላና ሲያስበላ የኖረን የጉዱሩ ሸኔ ምናልባት በለውጥ እሳቤ አይምሮ ይገዙ ይሆናል ብለው ይሆናል በክብር ያስገቧቸው እነ ዳውድን። የዶር አቢይ ትእግስት ህውሀትንስ በልምምጥና ፍቅር  ቢያጅቧት መች የእባብ ማንነቷን ቀየረው ለነገሩ። ወገን በዚህ ቪዲዮ ብዙ ይማማርበታል። የኢሳት ልጆችንም ፈጣሪ ይባርካቸው። ይህ ነው አይተን ያደግነው የመልካም ኢትዮጵያዊነት መገለጫ። ግሩም ቃለመጠይቅ።
እነሆ ሊንኩ።

አባዊርቱ ነኝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.