አብይን መደገፍ ኢትዮጵያዊነት ነው  – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

abiy w አብይን መደገፍ ኢትዮጵያዊነት ነው    ዶ/ር ዘላለም እሸቴሲጀመር ሁላችንም የአብይን ንግግር ወደን አብይን ደገፍን።  አሁን ደግሞ ሁላችንም ኢትዮጵያን ወደን አብይን የምንደግፍበት ጊዜ ነው።  ኢትዮጵያ መጨረሻዋ ምን ይሆን ብለን ስንሰጋ መንታው መንገድ ላይ ደረስን።  አንደኛው ኢትዮጵያ የምትቀጥልበት አቀበት ሲሆን፥ ሌላኛው ሞቷ የታወጅበት ቁልቁለት ነው።  መሀል ሰፋሪ መሆን ከእንግዲህ አይቻልም። ፖለቲካ አያገባኝም ማለት ዘበት ነው። የምንደግፈውን ፓርቲ ወደ ስልጣን እንዲመጣ የምንሮጥበት ጊዜ አሁን አይደለም። የዛሬው ምርጫ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ላይ የሚወስን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያን ሊያጠፋ ከመጣ እኩይ ተንኮል፥ ወጥመዱ ተሰብሮ ኢትዮጵያ የምታመልጥበት ወሳኝ ሰዐት ነው።  ስለዚህም ዶ/ር አብይን መደገፍ ኢትዮጵያን ማሻገር ነው። ሳይበላ እያበላን ያስተማረንን ድሀ ባለ አገሩን እናስብና ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም። ሀገር ከሌለ፥ እንዳለን አይቆጠርም። ስለዚህ በቃል በፀሎትና በሥራ ከጎኑ እንቁም።

ኢያሪኮን ያፈረሰው ድምፅ ነው። ምክንያቱም ከድምፁ ጀርባ ፈጣሪ ነበርና። ለዶ/ር አብይ አጋርነታችንን ስናሳውቅ፥ ፍቅርን አብሮነትንና ቤተሰብነትን መምረጣችን ነው። ይህም ድምፅ ብርሀን የሆነ ነው።  ጨለማ የሆነው የአጥፊውን ሴራ ስፍራውን የሚያስለቅቀው የብርሃን ድምፅ ነው። እኛ ተነስተን ድርሻችንን እንወጣ፥ ማዳን ከፈጣሪ ይሆንልናል። የሚንጫጫው የጥቂት ፅንፈኞች ድምፅ ፀጥ ይላል ብለን አንጠብቅ።  ይልቁንስ አድፍጦ የተኛው ብዙሃኑ ዝምተኛ ድምፁ ይሰማ። አንበሳው ሕዝብ ያግሳ። ያ ጥቂት አጥፊ ድምፅ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስብዕና እንደማይወክል ይታወቅ። በቃ! ይሁን አሜን።

ከሁሉ በላይ ፈጣሪ በኢትዮጵያ ላይ ያሳረፈውን እጅ በዚህ ቪዲዮ ተመልክተን ለበጎ ሥራ እንነሳሳ!

2 Comments

  1. ትክክል ነው ዶክተር ዘላለም
    ሽፋኑ ማታገያው አማራ ይሁን እንጂ የፅንፈኞቹ ዋናው ቁምነገር ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ ነው:: ነፍጠኛ ስርአት የለም:: አማራም ነፍጠኛ እንዳልሆነ በደንብ ያውቃሉ:: ያለውን መራራ ሀቅ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያገናዝብ እላለሁ::

    ዛሬ ኦሮሞ ነፃ ነው በራሱ ልጆች ይተዳደራል :: ፅንፈኞቹ የሚያልሙት ኢትዮጵያ ፈርሳ ልክ እንደ ኤርትራ አዲስ ሀገር ለመመስረት ነው::ነፃዋ ኦሮሚያ ደግሞ ለሁለት ትከፈላለች ምስራቁ የጃዋር ኢስላሚክ ኦሮሚያ ሬፑብሊክ እራሱን ችሎ ይሄዳል:: ወያኔም ይህን አመቻችቶ የራሱን ሬፐብሊክ መስርቶ ጎረቤት ይሆናሉ:: ይህ ነው የትግሉ መጨረሻ ግብ:: ወቅቱ የፖለቲካ ትግል ሳይሆን የሀገርን ህልውና ማዳን ነው:: ኢትዮጵያዊ በሙሉ ከዐቢይ ጋር የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠብቅበት ወቅት ላይ ደርሰናል::

  2. በሥራው በበጎ ምግባሩ ጠላት ባይበዛበት ነበር የሚገርመው ለኔ መሪያችን ነው .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.