የተባበሩት መንግስታት የስብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን፣ ነፃና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ይቌቌም!!! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

UNCHRየተባበሩት መንግስታት የስብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሮበርት ኮልቪል፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሣ መገደል በኃላ የተፈጠረው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል፡፡  የሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያ በሃገሪቱ ውስጥ ተቃውሞ ቀስቅሶል አንደኛው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሆን ሌላው ነውጠኛ  ነበር፡፡ በኦሮሚያ ክልል አውራ መንገዶች ተዘግተዋል፣ ፎቅ ህንጻዎች ተሰባብረው ተቃጥለዋል፣ የመሣሪ ድምፅ ተስተጋብቶልበአዲስ አበባ ቦንብ ፍንድቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የህዝቡን አመጽ ለመግታት መንግሥት በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ የኢንተርኔት ግንኙነት በመዝጋት  መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖል፡፡ መንግሥት 50 ሰዎች ሞተዋል ሲል ሌሎች ሚዲያዎች የሞች ቁጥርን 80 ሲያደርሱት  ሦስቱ የፖሊስ አባሎች እንደሆኑ ዘግበዋል፡፡

Press briefing note on Ethiopia  Spokesperson for the UN High Commissioner for Human Rights:  Rupert Colville

Location: Geneva/Date: 3 July 2020 Subject: Ethiopia

“We are deeply concerned at violent events in Ethiopia this week where a prominent singer and activist from Oromia Region, Hachalu Hundessa, was shot and killed in the capital, Addis Ababa on Monday. The killing of Hundessa sparked protests across the country, including in the capital and in Oromia Region. While some of the protests were peaceful, a number were violent from the outset. According to information we have received, roads were reported to be blocked in most parts of Oromia Region and buildings vandalised and burnt, while there was gunfire and bomb explosions in Addis Ababa. The authorities responded to the spread of the protests by shutting down the Internet in Oromia Region, as well as in Addis Ababa, making it extremely difficult to verify reports about the number of people killed and injured. According to the Government, around 50 people were killed, while media sources indicated some 80 people had died, including three members of the security forces.”

ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኃላ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ  ወደ ዘር ግጭት እያደገ መምጣቱ ና መሰፋፋቱ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች ከዘረኛ ቅስቀሳና  ጥቃት   እራሳችሁን በማግለልና ከኃይል እርምጃና የአመፃዊ ነውጠኛ  ድርጊቶች  አለመሳተፍ  ያስፈልጋል፡፡  በሌላም በኩል መንግሥታዊ መከላከያ ኃይል በነውጠኞች ላይ ተመጣጣኝ  እርምጃ ብቻ እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡ በሃጫሉ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ የረበሹ 35 ሰዎች በፖሊስ ተይዘዋል ምክንያቱም አጫሉ አዲስ አበባ ነው መቀበር ያለበት በማለት ወላጆቹን በመረበሻቸው ነበር፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በአጫሉ ግድያ ምክንያት ወጣቶች ወደ ዘርና ኃይማኖት ፍጅት እንዳያመሩ እናሳስባለን፡፡ እንዲሁም መንግሥት ኃይል ተመጣጣን እርምጃ ብቻ እንዲወስዱ መክረዋል፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት ህዝቡን ነፃነትና መብት እንደሚጋፋ እንዲሁም  የህዝቡን የማወቅ ፍላጎት፣ መረጃ የማግኘት መብትና መረጃ የመለዋወጥ መብት ይገድባል በዚህም ምክንያት  መረጃ እጦት የተነሳ ውጥረት ይከሰታል፡፡ ስለዚህ መንግሥት የኢንተርኔት አገልግሎት በአስቸኮይ በመጀመር የመረጃ ፍስት ነጻነት እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል፣ መዘግየት አያሻም ፡፡ “We note with concern that the protests following Hundessa’s killing have increasingly taken on an ethnic undertone. We therefore call on all, including young people, to stop carrying out ethnically-motivated attacks and to stop inciting to violence, acts that only serve to exacerbate underlying tensions.We also urge the security forces to exercise restraint when managing protests and to refrain from using unnecessary or disproportionate force. Thirty-five people were reported to have been arrested by security forces on Tuesday evening during a protest over the location of Hundessa’s funeral. According to the police, the protesters, who wanted the singer to be buried in Addis Ababa, unsuccessfully tried to prevent his body being taken to his hometown of Ambo. His funeral went ahead in Ambo on Thursday. The shutting down of Internet services is of particular concern as it disproportionately restricts the enjoyment of the right to freedom of expression, including freedom to seek, receive and impart information and risks further exacerbating tensions. We urge the authorities to restore Internet access without further delay.”

መንግሥት የአጫሉ ሁንዴሳን ተጠርጣሪ ገዳዬች መያዙን አስታውቆል፡፡  ነፃ፣  ገለልተኛና ግልፅነት ያለው መርማሪና  አጣሪ ኮሚሽን በማቆቆም የሃጫሉን ሁንዴሣን አሞሞት ማጣራትና ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቤተሰቦቹ ፍትህ የማግኘት መብት አላቸው፣ እውነቱ መውጣት አለበት እንላለን፡፡  እኛም ለኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን  ለሚደረገው ምርመራ  ድጋፍ ማድረግና በዚህ አመፃዊ ድርጊት ሁኔታ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት    በነፃ፣ ገለልተኛና ግልፅ መርማሪና  አጣሪ ኮሚሽን ማቆቆም አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡  “The authorities have announced that suspects in Hachalu Hundessa’s murder have been arrested. It is essential that there is a prompt, thorough, independent, impartial and transparent investigation into his death to ensure those responsible are held accountable. The victims and their families have the right to justice, the truth and reparations. We also stand ready to provide support to the Ethiopian Human Rights Commission in its investigation of potential human rights violations during these violent events.”

ENDS፡- For more information and media requests, please contact: Rupert Colville – + 41 22 917 9767 / [email protected] or Liz Throssell – + 41 22 917 9296 / [email protected]  or Marta Hurtado – + 41 22 917 9466 / [email protected]

Tag and share – Twitter: @UNHumanRights and Facebook: unitednationshumanrights

ማጠቃለያ ገንቢ ምክር

{1} የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት በሃገሪቱ ውስጥ የተፈፀመውን  በአቆራጭ ሥልጣን ለመንጠቅ የተጠነሠሠ የፖለቲካ ሴራ በነፃ፣ ገለልተኛና ግልፅ መርማሪና  አጣሪ ኮሚሽን በአገር ውስጥና በባህር ማዶ ሙያተኞች በማሳተፍ ሁኔታው ቢጣራ  የሃጫሉ ግድያ ውስጥ የተሣተፉ ወንጀለኞችን በእውነት፣ ያለአድሎ፣  ያለወገናዊነት ሁሉን አሳታፊ ታማኝና በሳይንሳዊ ማስረጃ  ወንጀለኞቹን ማግኘትና ማረጋገጥ ይቻላል እንላለን፡፡

{2} የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ የነበራቸውን ህዝባዊ ድጋፋ መልሰው ለማግኘት በዚህ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁሉ  ኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮና በኦዴፓ ብልጽግና የውስጥ አርበኞች የተጠነሰሰ የፖለቲካ ሴራ በእውነት፣ በግልፅነትና በተጠያቂነት እንዲጣራ በማድረግ ታሪክ ይስሩ እንላለን፡፡

{3} ክብርት አቃቢት ጄኔራል አዳነች አቤቤ ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጡ ጊዜ ስለሚሳሳቱ በንባብ መግለጫ ቢሰጡ የተሸለ ይሆናል እንላለን፡፡ ተጠርጣሪዎቹን እንደ ወንጀለኛ አድርጎ ማቅረብ አንደኛው ስህተታቸው ሲሆን፣ ‹‹ጁሃር መሃመድና እስክንድር ነጋ ተናበው እየሠሩ ነበር›› በማለታቸው ደግሞ በህዝብ ዘንድ  በፖለቲካ ካድሬነታቸው ጎልቶ እንደወጣና የህግ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ  እውቀት፣ ታማኝነት፣ ብቃትና ችሎታ  የላቸውም እንላለን፡፡ አዳነች አቤቤን በሌላ ችሎታ ባለው ሰው መተካት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡  የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት  የህግ የበላይነትን ለማስከበር ጠንካራ ሰው በመመደብ ፍትህ መስጠት ላይ ማተኮር ከህዝብ ጋር ያስታርቃቸዋል እንላለን፡

Source:-

(1) https://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=26034&LangID=E

(2) https://www.youtube.com/watch?v=tTlPMcJZ-9cEthiopia: ሰበር ዜና – የኢትዮታይምስ የዕለቱ ዜና | Daily Ethiopian News | ሰበር መረጃ/27,487 views/•Jul 9, 2020

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.