“ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም” – የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

ጄኔራል አደም መሐመድ Adem Mohammed 300x282 1ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደሌላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ።የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመለከቱ።
ጄኔራል አደም መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከህግ ውጪ ሆኖ፤ በተለይ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ በመፍጠር፤ ግጭት በመፍጠር፤ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች እየተፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደማይኖራቸው አስታውቀዋል።
ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል ።
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መንግስት እርምጃ መውሰድ ካልቻለ የመንግስትነት ተልዕኮው ምን ሊሆን ይችላል? እንደዚህ አይነት ጥፋቶች አድገው እንደ ሩዋንዳና ሌሎች አገሮች እንደሆኑት የሚጠብቅ ከሆነ ሕገመንግስታዊነቱ በምን ይገለጻል ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡
“ግልጽ መሆን ያለበት መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ይህን ማስቆም በህገመንግስቱ የተሰጠው ኃላፊነት ነው ። የሰራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ፤ ግዴታም አለበት” ብለዋል ፡፡
የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያውያን ሰራዊት ነው ፤ተልእኮውም የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ እንደሆነ ያመለከቱት ጄኔራል አደም ፣ ህገ መንግስቱ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣል ለዚህም ዝግጁ ነው ብለዋል ።የሰራዊቱ ተልእኮ የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ በመሆኑም ተልእኮውን ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ጋር አይይዞ ማየት እንደማያስፈልግ ገልጸዋል ።

3 Comments

  1. Let’s see if you can prevent the next round of genocide. Talk only doesn’t help the poor women and children who are being slaughtered by Al Querro Terrorists. Where were the Oromia special force when all this happened? You should remember that one day you will be responsible for the genocide under your watch.

  2. “የሰራዊቱ ተልእኮ የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ ” ከሆነ፣ ህገመንግስቱ ከሚሰጠው ሥልጣን ዉጪ (ያለፓርላማው ዉሳኔ፣ ያለ ሚኒስትሮች ምክርቤት እውቅና) ኮሎኔል አቢይ ቀጥታ ባወጀው ጦርነት፣ የኦሮሞን ህዝብ የምትጨፈጭፉት ለምንድር ነው??? ወይስ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በወረራ የያዛችሁት የባዕድ ሃገር እና ህዝብ ነው?? ኦ ገባኝ፣ መሬቱን ኢንጂ ህዝቡን አትፈልጉትም፣ ልክ እንዴኤርትራ እንደነበረው!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.