ፖፕ ፍራንሲስ በኢትዮጵያ የጅዋር ቄሮ የ86 ሰዎች የዘርና ኃይማኖት ጭፍጨፋን አወገዙ!!! (ክፍል ሁለት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ET21በህወሓት/ኢህአዴግና በኦዴፓ/ብልፅግና መንግስታዊ የጀኖሳይድ ሽብርተኛነት ስፖንሰር ተደርጎል!!!

ለዴንቨር የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረኃይል የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) መፈፀሙን፣ ፖፕ ፍራንሲስ በኢትዮጵያ የጅዋር ቄሮ የሰማንያ ስድስት ሰዎች የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ )ጸሎት አድርሰው በየመገናኛው ብዙሃን ሚዲያዎች አድርገው ነበር፡፡ በ1983 ዓ/ም ህወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከጨበጠ ዘመን ጀምሮና ዛሬም ኦዴፓ/ብልፅግና ዶክተር አብይ አህመድ ግንቦት 2010ዓ/ም በትረ ስልጣን ከጨበጠ ጀምሮም ጀኖሳይድ በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ እንዲሁም በኃይማኖት ተከታዬች ላይ የተፈፀመ የሰዎች ፍጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ጀኖሳይድ ብዙ ጊዜ እንደተካሄደና ጀኖሳይድ አይደለም ግጭት ነው እየተባለ ሲታለፍ ሃያ ዘጠኝ አመታት አልፎታል በዚህም የተነሳ የዘር ፍጅት ወንጀለኞች እንዲበረታቱ፣ ተጠቂዎቹ ከገዳዬቻቸው ጋር እንዲኖሩ ተደርጎል፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግና በኦዴፓ/ብልፅግና መንግስታዊ የጀኖሳይድ ሽብርተኛነት ስፖንሰር ይደረጋል እንላለን!!!

“Genocide is the intentional action to destroy a people—usually defined as an ethnic, national, racial, or religious group—in whole or in part. A term coined by Raphael Lemkin in his 1944 book Axis Rule in Occupied Europe, the hybrid word genocide is a combination of the Greek word γένος and the Latin suffix -caedo.”

መግቢያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ጉብኝታቸው ወቅት ከኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውዲ ኢብሳ ጋር ተገናኘተው ተወያይተዋል።  የግንባሩ ቃል-አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለቢቢሲ እንደገለፁት ”ሁለቱ አካላት ፊት ለፈት ተገናኘተው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ በመርህ ደረጃ ተግባብተዋል” ብለዋል። አቶ ቶሌራ ጨምረው እንደተናገሩት ሁለቱ አካላት ከአገር  ውጭ ውይይታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል። ከቀናት በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ይታወሳል።  በሌላ በኩል በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ከ200 በላይ በሚሆኑ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቡና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ከ348 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት ውድመት መከሰቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዳይሬክተር የፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል በጥናት በማስረጃ አቅርቦል፡፡ በዚህም የተነሳ በአጠቃላይ ክልሎች ለደረሱ የኢንቨስትመንት ውድመቶች መንግሥት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የማገገሚያ ክፍያ ከፍሎል፡፡ ተጎጂ ድርጅቶች ከሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲያስገቡ ስለሚደረግ ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ያደርጋታል፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር የትየለሌ ሆኖ፣ ፋብሪካዎችን፣ እርሻዎች፣ የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች ወዘተ ኢንቨስትመንቶችን እንዳያወድሙ አስፈላጊው ትምህርት ባለማስረፁ ንብረት ማውደም ባህል የሚያገረሽ ዋነኛ ምክንያት ሆኖል፡፡

ጥቅምት 2012 ዓ/ም

በወርሃ ጥቅምት በተለያዩ የኦሮሚያ አካበዘቢዎች በጀዋር መሃመድ የተከብቤለሁ ድረሱልኝ ጥሪ ምክንያት በደሬዳዋ፣ ሀረርጌና ዶዶላ ከተሞች የሚገኙ ፅንፈኛ ቄሮዎች የ86 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዶክተር አብይ መንግሥት አስታውቆል፡፡ ሜንጫ መር ቄሮዎች ብዙ ንብረቶች አውድመዋል፣ 25 ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ 100 የኃይማኖት አባቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ከመቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የዘር ፍጅቱ ያተኮረው በአመዛኙ በአማርኛ ተናጋሪዎች፣ አማሮች ከክልላችን ውጡልን በሚል  ዘረፋ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች በተለይም ለአማራ ያደሩ የተባሉ ምስኪኖችም ተገድለዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቆማት በአገሪቱ ውስጥ ካሉት 45 ዮኒቨርሲቲዎች ውስጥ በ25ቱ ውስጥ የማንነትና የኃይማኖት የ‹ፖለቲካ አጀንዳዎች ማቀንቀኛ እንዲሆኑ ተዳርገዋል፡፡በዚህም የተነሳ ሰላማዊ የመማርና ማስተማር ሂደት መስተጎጎል ገጥሞቸዋል፡፡ ተማሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ለተዘራው የዘር ፖለቲካና የኃይማኖት ሰለባዎች በመሆናቸው የዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች  በአሰቃቂ ሁኔታ መገዳደላቸው የዘር ፖለቲካ አራማጆች ፖለቲከኞች ውጤት ሲሆን የዶክተር አብይ መንግሥት ህግና ሥርዓት እንዲከበር የዘርና ኃይሞኖት ፅንፈኝነት የሬዲዩና ቴሌቪዥን ሥርጭቶች በህግና ደንብ እንዲተዳደሩ ስርዓት  ማውጣት ሲሳናቸው ማየት ሀረጊቱን የወላድ መካን አድርጎታል፡፡

Pope prays for people killed in ethnic, religious clashes in Ethiopia/ In Catholic News Service, Vatican/ Carol Glatz/Nov 4, 2019/ CATHOLIC_NEWS_SERVICE ( / ፂዮን ዘማርያም )

Pope Francis waves during the Angelus noon prayer he delivers from his studio window overlooking St. Peter’s Square at the Vatican, Sunday, Nov. 3, 2019. (Credit: Gregorio Borgia/AP.)

ፖፕ ፍራንሲስ ጆን ፖል ሁለተኛው በኢትዮጵያ በዘርና የሃይማኖት ግጭት ለሞቱ ፀሎት አደረሱ፡፡ በኖቨንበር አራት 2019 እኤአ ካሮል ግሌዝ የቨቲካን የካቶሊክ ዜና አገልግሎት ዘገባ መሠረት፡፡ ፖፕ ፍራንሲስ በኦሮሚያ ክልል በጁሃር መሃመድ ተከብቤላሁ በሚል ጥሪ መሠረት  በአክራሪ ቄሮዎች የተከናወነ በአሰቃቂ ሁኔታ ለሞቱ ሰዎች የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ ተከናውኖል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 86 ሰዎች በግፍ መገደል ሳያወግዙና ትንፍሽ አለማለታቸው ህዝብ አንቅሮ እንዲተፋቸው ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ በመቀጠልም ሞቾችን በብሄራቸው፣በሃይማኖታቸውና በፆታቸው ፈርጀው መግለፃቸው ‹‹ስኖር ኢትዮጵያዊ፣ስንሞት ኢትዮጵያዊ›› ያሉትን ቃላቸውን አጥፈዋል በሚል ተነቅፈው ነበር፡፡ ፖፕ ፍራንሲስ ጆን ፖል ሁለተኛው በኢትዮጵያ በዘርና ሃይማኖት ጭፍጨፋ ለሞቱ  40 ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና 34 ሙስሊሞች ፀሎት ማድረሳቸው ታውቆል፡፡

ROME — “Pope Francis prayed for those killed during violent protests in Ethiopia, which left dozens of people dead. Violence erupted in late October in Oromia — the most populated region of the North African nation. Prime Minister Abiy Ahmed told reporters Nov. 3 that at least 76 people were killed during clashes fueled by ethnic or religious hostilities. The victims include 40 Orthodox Christians and 34 Muslims, he said, according to ezega.com.

The prime minister called for an end to using religion or ethnicity as a reason for conflict and urged young people to avoid religious and ethnic extremism. After praying the Angelus with visitors in St. Peter’s Square Nov. 3, Francis led a prayer for all those affected by the violence, including members of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. “I express my closeness to this church and its patriarch, dear brother Abuna Mathias,” the pope said. “I ask you to pray for all victims of violence in this land,” he said before leading the recitation of a Hail Mary.”

በዚህ የዘር ማጥፋት ምክንያት በመላ ሃገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ፅንፈኛ ቆሮ ባስነሱት ነውጥ የሰው አንገት መቅላት፣ መንገድ መዝጋት፣ ባንክ መዝረፍ፣ ንብረት ማውደም የተነሳ፣  የውጭና የሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ነቅለው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል የውጭ ዜጎች በተደጋጋሚ መገደል የተነሳ ኢንቨስተሮች ኮብልለዋል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ አባል የሆኑ ሹማምንቶች ገደላ ለምሳሌ የነቀምቴ ፖሊስ ምርመራ ካማንደር ጫላ ደጋጋ፣ የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ሹም ቶላ ገዳ፣ የምዕራብ ኦሮሚያ ሸዋ ጀልዱ አስተዳዳሪ ረጋኔ ከበደና ተስፋዬ ገረመው፣ የቴሌካምኒኬሽን ሹም ገመቺስ ታደሰ በግፍ ተገድለዋል፡፡ አባ ቶርቤ (ማነው ባለሣምንት) በኦሮሞ ልጆች ላይ ተጭኖል፡፡ የኦሮሞ የስልጣን ጥመኛ ፖለቲከኞች ኦሮሞ ኦሮሞን አይገልም ሲሉ ሌላውን ዘር መግደል ግን ተፈቅዶል ማለት አይደለምን!!!  ‹‹ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ!!!›› ኦሮሞ ኦሮሞን አይገልም!!! ብለው የተፈራረሙት ለማ መገርሳ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ከማል ገልቹ ፊርማቸው ሳይደርቅ ‹‹ሜንጫው ሰው በላ!!!››  በኦሮሚያ ከተሞች ከ10 ሚሊዩን በላይ ሥራ አጥ ወጣቶች ይገኛሉ፣  ጁሀር መሃመድ አባ ሜንጫ ቆሮ ካዘዘ ሰው ይታረዳል፣ መንገድ ይዘጋል፣ ኢንቨስተሮችና ባለሆቴሎች ግብር ለአባ ሜንጫ ቄሮ ግብር ገብራሉ፣ የትራንስፖርት ተጠቃሚ ተላላፊ የመኪና ተጎዦች የመተላለፍያ የኮቴ ይከፍላሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ተቆማት እንደሌሉ ይቆጠራል ኦነግ ሾኔና አባ ሜንጫ ቄሮ ተቆጣጥረውታል፡፡ የጦር መሣሪያ ዝውውር፣የህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ የክልሉን ኢኮኖሚ አሽመድምዶታል፡፡ በኦሮሚያ ህዝቡ ኦነግ ሾኔና አባ ሜንጫ ቄሮ ‹ቀይ ሽብር›› በአንድ በኩል በፌዴራል መከላከያ ጦር በሌላ በኩል እንደ ድፎ ዳቦ እየተለበለበ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ብሶቱን የሚጮሁለት ልጆቹ በፍርሃት ተውጠዋል፡፡ ደም የጠማቸው ፖለቲከኞች የዘር ፍጅት፣ የሃይማኖት እልቂት ደግሰውለታል፡፡ እነዚህን ፅንፈኛ ፖለቲከኞች የኦሮሞ ህዝብ ቆርጦ መታገል ይጠበቅበታል እንላለን፡፡ (ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም በኖቨንበር አራት 2019 እኤአ ዘ-ሐበሻ ድረ-ገፅ ላይ ዘግባ ነበር፡፡)

 

ሰኔ 23 ቀን 2012ዓ/ም፡-

የህወሓት፣የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!!  የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማጋለጡ መንፈቅ ሳይሞላው በወያኔ፣ በኦነግ፣ በኦነግ ሸኔ፣ በኦፌኮ የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የሠላሣ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  መኖር አለበት እንላለን፡፡

  • በሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌና፣ በዝዋይ ከተሞች

የህወሓት፣የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!!  የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወንጀል መንፈቅ ሳይሞላው በወያኔ፣ በኦነግ፣ በኦነግ ሸኔ፣ በኦፌኮ የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የሠላሣ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው አይሲሲ እና ኤችአር 128 እንዲቀጥል በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን ያሳዘነው ኢትዮጵያን የማፍረሱ ውጥን አሳዛኝና አንገት አስደፊ ክስተቶችን ትቶ አልፏልJuly 13, 2020

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን የሴራ ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ አንድ ከተሞች ላይ እንኳንስ ለወዳጅ ለጠላትም የማይመኙት አይነት ውድመት በጸረ ሰላም ሀይሎች የተቀናጀ ሴራ ተፈጽሟል። ጉዳት በደረሰባቸው ከተሞች ላይ ጉብኘት እያደረገ ያለው የድርጅታችን ፎቶ ጋዜጠኛ ዳኜ አበራ በአርሲ ነገሌ፣ በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች የደረሰውን የንብረት ውድመት በካሜራው እንዲህ አስቀርቶታል።

 

  • በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ 38 የመንግሥት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል (July 13, 2020)

አጋርፋ፡- ሰኔ 23 በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት የድጋፍ ሰልፍ እንወጣለን በሚል በተፈጠረው ሁከት በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን እንዲሁም ሰላሳ ስምንት  የመንግሥት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ፣ በዚህ ድርጊትም ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ሲቀሩ የወረዳው የመንግሥት መሥሪያ ቤት መውደማቸውን በንብረት ላይ የደረሰው ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት እንደሆነም፣ከሁከቱ ጋር በተያያዘ በተከሰተው ዝርፊያና ቃጠሎ ምክንያት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን  የባሌ ዞን ፖሊስ ምርመራ ዲቪዚዎን ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ከበደ አስታወቁ፡፡ ።

በወቅቱም በርካታ ቁሳቁሶች መያዛቸውን ጠቁመው ዘጠኝ ሽጉጥ፣ አራት ክላሽንኮቭ እንዲሁም ቤቶችንና ድልድዮችን ለማፍረስ የሚውሉ አራት መቶ ሰላሳ አራት ተቀጣጣይ ፈንጅ ግማሽ አካል መገኘቱንም አመልክተዋል። ይህ ተቀጣጣይ ፈንጅ አንዱ በፖሊስ ጣቢያ አንዱ በድልድይ ላይ ተጠምዶ የተገኘ ሲሆን ከአጠማመድ ችግር የተነሳ የታለመለትን አላማ ሳያሳካ መቅረቱን አመልክተው፣ በተደረገው ክትትልም የተቀጣጣይ ፈንጅ ግማሽ አካሎቹ በአንድ ግለሰብ ቤት መገኘታቸውን፤ ግለሰቡም ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል። ከመንግሥት መሥሪያ ቤት የተዘረፉ አንድ መቶ አስር የጦር መሣሪያዎች መመለሳቸውን አመልክተው፤ ድርጊቱ የተፈፀመው በተወሰኑ የተደራጁ ቡድኖች ነው። የኦነግ ሸኔ አባላትም በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።

ከሁከቱ በኋላ የወረዳው አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ አብዱቃድር ኡስማን በበኩላቸው፤ የተፈጠረው ድርጊት በተደራጀ የጠላት ሴራ መሆኑን አስታውቀው፣ አለማውም ብሔር ብሔረሰቦችን አጣልቶ አገር ማፍረስና በአቋራጭ ወደ ሥልጣን የመምጣት ህልማቸውን እውን ማድረግ ነው ብለዋል። የአርሶ አደሩ ንብረት የሆኑ ከብቶችና ሌሎች ንብረቶች ሳይቀር የተዘረፉና የወደሙ መሆናቸውን አመልክተው፣ የደረሰው አጠቃላይ ጉዳት እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል። አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል። ከጉዳቱ ጋር በተያያዘም የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ ሦስት የወረዳው የካቢኔ አባላት እንዲሁም ዘጠኝ የፖሊስ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

 

መደምደሚያ

የህወሓት፣የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ  ድርጅታዊ ሽብርተኛነት የዘርና የሃይማኖት ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ቀርበው በግፍ ለተገደሉ ሞቶች ፍርድ እንዲሰጥ ህዝብ ለመጨረሻ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል  ለደረሱ የኢንቨስትመንት ውድመቶች የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና እነዚህ ድርጅቶች ተጣርቶ ወንጀለኛ  ከሆኑ ንብረታቸው ተሸጦ ካሳ እንዲሆንና የማገገሚያ ክፍያ እንዲሠጣቸው ያስፈልጋል፡፡ ለተጎጂ ድርጅቶች ከሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲያስገቡ በማድረግ ዳግም ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማድረግ ያሻል፡፡ የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሤ በዘዋይና ሻሸመኔ የገነባው ሦስት ኮከብ ሆቴል  እንደወደመበትና  የጠፋው ንብረት 300 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚገመትና 400 ሠራተኞች እንደነበሩት ገልፆል፡፡  በጅማ የአቶ ፀሐይ 100 ሚሊዮን ብር የገነቡት ሆቴል እንደወደመባቸውና 400 ሠራተኞች እንደነበሮቸው ገልፀዋል፡፡ መንግሥት ሃቀኛ ፍርድ ካልሠጠ ወደፊት በኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት እንደማይኖርና በባህር ማዶ ሃገራት አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ‹‹ኢትዮጵያ ትውደም!!!›› እያሉ የኦሮሞ ህዝብን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን የፖለቲካ ሴራ የኦሮሞ ልጆች መመከት ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ በክልሉ የኢንቨስትመን ፍስት እንደቀነሰና የስራ አጥ ቁጥርም እንደጨመረ፣ የትራንስፖርት መኪኖች በፍርሃት እንደሌሉ፣ ንግድ መቀዛቀዙ ታውቆል፡፡  ኦነጎች የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ተይዞ ለሞት፣ ለእስራትና ስደት ተዳርጎል፡፡

‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ15

አንድ እናት ዶክተር አብይን የጠየቁት ‹‹ልጄን ነው ያረዱት፣ ፍየል ያረዱ መሰላቸው ወይ! ፍርድህን ስጠኝ፡፡››

የህወሓት፣የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ አንድም ሁለትም ሦስትም ናቸው!!!

በኢትዮጵያ የህግ ሉዓላዊነት ይከበር!!! የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!! እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩም፣ኢንጅነር ይልቃል፣ ልደቱ አያሌው ከጅዋር መሃመድና በቀለ ገርባ የጀኖሳይድ አቀናባሪዎች ጋር ቀላቅሎ ማሰር የተንሸዋረረ ፍርድ ነው፡፡

 

ምንጭ

(1) Pope prays for people killed in ethnic, religious clashes in Ethiopia/ In Catholic News Service, Vatican/ Carol Glatz/Nov 4, 2019/ CATHOLIC_NEWS_SERVICE

(2) ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን ያሳዘነው ኢትዮጵያን የማፍረሱ ውጥን አሳዛኝና አንገት አስደፊ ክስተቶችን ትቶ አልፏል July 13, 2020

(3) በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ 38 የመንግሥት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል July 13, 2020

 

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.