ዘር ማጥፋትን ካዱ! – በላይነህ አባተ

stop the amhar Genocideዓይን በጨው ታጥበው እጅግ እየዋሹ፣
የዘር ፍጅት የለም ሐሰት ነው እያሉ፣
ደሞ እንደ ቋሚዎች ሙታንንም ካዱ፡፡

ናዚዎች አይሁድን መደዳ ሲፈጁ፣
ብዙዎች ነበሩ ዘር ማጥፋት የካዱ፡፡

የናዚ ሸፋኞች ጪፍጨፋን ያፈኑ፣
እንዳለመታደል በኢትዮጵያም ታዩ፡፡

ነፍጠኛው አማራ ተዚህ ውጣ እያሉ፣
ሽማግሌ አሮጊት ሲገሉ እንዳላዩ፣
የዘር ፍጅት የለም አሉንና አረፉ፡፡

ዘርን እየጠሩ ሰው እንዳልሰቀሉ፣
ዘር ማጥፋት አይደለም ብለውን ቁጭ አሉ፡፡

የዘር ሐረግ ቆጥረው ገጀራ እንዳልሳሉ፣
ዘር ማጥፋት አንልም ብለው ግጥጥ አሉ፡፡

ሰውን በዘር ገድለው እንዳልቆራረጡ፣
አስከሬንን አስረው ሜዳ እንዳልጎተቱ፣
አጋሰስ ምሁራን ኃጥያትን ሸፈኑ፣
የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም እያሉ፡፡

ዘራቸው ተቆጥሮ ሰማእት የሆኑ
ተሰማዩ ሆነው ዝቅዝቅ ምድርን ቢያዩ፣
በትዝብት ተውጠው ከሃዲን ምን ይሉ፣
ዘር ማጥፋት የለምን ሲዋሹ ሲቀጥፉ፡፡

በሰማእታት ደም ገንፎ ሊያገነፉ፣
አስመሳይ ሆዳሞች ወገንን የከዱ፣
ስንቱ ንፁህ ታርዶ የዘር ፍጅት ካዱ፡፡

የዘር ሐረግ ቆጥረው አማራን ሲገድሉ፣
አብሮ የቆመውን ጉራጌን ሲቀሉ፣
እነ ህሊና ቢስ ተእውነት የተጣሉ፣
ዘር ማጥፋት አይደለም ሲሉ ሕዝብን ካዱ፡፡

እንደ ጅረት ፈሳሽ ደምን ሳያቆሙ፣
በዘር የተቀላን አስከሬን ሳይቀብሩ፣
በአባዩ ጎርፍ አብደው እልልታን ጨፈሩ፡፡

ጆሯቸውን ቀርቶ ዓይንን ያላመኑ፣
ሰማዩ ያየውን ዘር ፍጅት የካዱ፣
ተመለኮት ታሪክ ተሙታን ተጣሉ!

በላይነህ አባተ ([email protected])
ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.