አቶ ልደቱ አያሌው በፖሊስ ተይዘው ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ተወሰዱ

Lidetuየኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፖለቲካኛው አቶ ልደቱ አያሌው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ።

አቶ ልደቱን ፖሊስ የያዛቸው በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በማስተባበርና በመደገፍ እንደሆነ አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ዛሬ አርብ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መኖሪያቸው ወደሚገኝበት የቢሾፍቱ ከተማ እንደተወሰዱ ተገልጿል።

የፕርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ እንደተናገሩት ፖሊስ አቶ ልደቱን ለመያዝ የመያዣ ትዕዛዝ ያወጣው ሐምሌ 03/2012 ዓ.ም እንደሆነና እስከ ዛሬ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ ተገልጿል።

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ባቀረበው ክስ ምክንያት በአቶ ልደቱ ላይ የእስር ማዘዣው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወጣ እንደሆነ አቶ አዳነ ገልጸዋል።

አቶ ልደቱ ነዋሪነታቸው ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ያዋለቸው የፌደራል ፖሊስ ለሚፈልጋቸው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ለማስረከብ እንደወሰዳቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል።

አቶ ልደቱ የኢዴፓ መስራችና አባል አመራር ሆነው ለረጅም ዓመታት የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የድርጅቱ የብሔራዊ ምክር ቤት አባልና አብሮነት በሚባለው የፓርቲዎች ጥምረት ውስጥ የኢዴፓ አስተባባሪ ተወካይ ናቸው።

አቶ ልደቱ በአወዛጋቢው የ1997 ምርጫ ላይ ተሳትፈው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን በእራሳቸው ፖለቲካዊ ህይወትና በአገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ መጽሐፍትን ጽፈዋል።

BBC Amharic

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.