“በግድብ የተያዘው ውሃ በመጪው አመት ኃይል ማመንጨት ያስችላል” – ኢ/ር ስለሺ በቀለ

sileshiአዲስ አበባ፦ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የተያዘው ውሃ በመጪው አመት በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት እንደሚያስችል የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።
ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሐምሌ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አመት ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አመልክተው፤ ግድቡ የሚያስፈልገውን የመጀመሪያ ዙር 4 ነጥብ 9 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመያዝ ከግድቡ አናት ላይ ፈሷል ብለዋል ። ይህም የተከናወነው ወደታችኛው ተፋሰስ የሚሄደው ውሃ ሳይቋረጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ውጤቱ የግንባታው ዋነኛ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸው፤ በግድቡ የተያዘው ውሃ በመጪው አመት በ2 ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት እንደሚያስችል ጠቁመዋል። ግንባታው እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012

1 Comment

  1. እንኳዋን ደስ አላችሁ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በተለይ መጪው ዘመናት ጥሩ እንዲሆንላቸው ለምንመኘው ምስኪን የአገራችን ህዝቦችና ታዳጊ ህፃናት፡፡
    አሁንም በቀጣይ የቴክኒክ ድርድር ላይ በኛ አገር በኩል ብልጠት ያስፈልጋል፡፡ አጠቃላይ የሙሊት ጊዜው በግብፅ በኩል እነደሚፈለገው እንዳይራዘም ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በ2 ዓመት ውስጥ ግድቡ እንደተጠናቀቀ ሙሉ ለሙሉ ተሞልቶ በሙሉ አቅም ኃይል ማምረት እንዲጀምር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ አሁን የተጀመረው የዲፕሎማቲክና የሚዲያ ፕሮግራም በስፋት ኢትዮጵያውያ ውስጥና በውጪ ዲያስፖራ አካላት Aggressively መከናወን አለበት፡፡ የቲቪ ፕሮግራሞች ላይ የአገራችን የደሃው ገፅታ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ ወዘተ ምን ያህል እጥረት እንዳለ ቀጣይ በዶክመንተሪ ፊልም ታግዞ መሰራት አለበት፡፡ ልክ ፋና ቲቪ ላይ ስለአባይ እንደተላለፈው፡፡ በስፋት የሙሁራን ውይይትና አስተያየት በማከል ፕሮግራሙ ላይ የቢቢሲ፣ አልጀዚራና ሌሎችም ዘጋቢዎች እንዲኖሩ በማድረግ በውጪ እንዲተላለፍ ማድረግ ያፈልጋል፡፡ ስለአባይ ፍትሓዊ አጠቃቀም ሙሁራን ለነዚህ አለማቀፍ ሚዲያዎች ሃሳብና ፅሑፍ መስጠት አለባቸው እንዲዘግቡ፡፡ ሁሉም ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ አባይ የሁሉም ኢትዮጵያውያ ደም ነውና፡፡
    ግብፅ ስለችግር በማሰብ እንቅፋት ከመሆን የአባይ ውሃ እንዲህ እየሞላ በበረሃ ላይ ከሚባክን ትርፍ ውሃ በአገሯ ውስጥ በመያዝ ለችግር ጊዜ በመጠቀም ቀና ቀናውን ብታስብ ይሻላታል፡፡ ምቀኝነት የትም አያደርስም፡፡

    ኢትዮጵያውያ ለዘላለም ትኑር፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.